Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

«የዉበት መለኪያው ምን ይሆን» ?

«የዉበት መለኪያው ምን ይሆን» ?
〰〰〰〰〰〰〰
ልክ እንደተመልካቹ ትሉኝ ይሆናል ፣ እኔ ግን የምለው አለኝ:-
"ዉበት እንደ መነፅር ነው"!
ለአይነ ስውር መነፅር እንደማይጠቅመው ሁሉ ፣ ውጫዊ ዉበትም ብዙም አይጠቅመውም።
«መነፅር» የሚጠቅመው የአይኑ ብርሃን ላለ ሰው ወይም ማየት ለሚችል ሰው ብቻ ነው ። !
«የውስጥ ውበትም» ከላይ የሚታየውን ውበት በደንብ አድርጎ ያጎላዋል ልክ
እንደ መነፅሩ !
ያለዚያ የሚሆነው ልክ እንደ አይነ ስውሩ መነፅር አይነት ነው።
ተመልከቱ! ውስጣችን በወንጀል እንደብረት ዝጎ ላያችን (ውጫዊ ክፍላችን) በጣም ከምናስበው በላይ ተውቦ አምሮ ዋጋ ይኖረዋልን? እኛን ከእኛ በላይ የሚያውቅ አምላካችን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ውስጣችንን ያውቀዋል ። በል እንዲያውም ነፍስህ ምን እንዳቀደችና ምን እንዳለመች ጠንቅቆ የሚያውቅ የአለማት ብቸኛ ጌታ ፈጣሪ ነው! ታድያ ለሰው የማይታየው ውስጣዊ አስተሳሰብህ እንደ ብረት ዝጎ ያንተ ከላይ ብቻ ማማር ምን ሊጠቅመህ? ለሰው የሚታየው አካልህ ብቻ ማማሩና መዋቡ ዋጋ እንደሌለው አውቀህ ለሰው የማይታየውን ያ! ጌታህ ብቻ! አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የሚያውቀውን ውስጥህን ይበልጥ አሳምር!
«ውስጣዊ ውበት ከላይ የሚታየውን ውበት በደንብ ያጎላዋልና ለውስጣዊ ውበታችን እንጨነቅ»!
«ልጆችን ሳንወልድ» በጥሩ ተርቢያ ማሳደግ እንችላለን እንዴ ?
ጥሩ ትምህርት ቤት ፣ ጥሩ እናት በውስጣዊ ውበት የተሞላችዋን ፣ የዲን ባለቤት የሆነችዋን ደጓን እናት በመምረጥ ! በዱንያም በአኺራም እንጠቅማቸዋለን!
አላህ ያግዘን። አላሁመ አሚን !