Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እፍረትም የኢማንሽ መለኪያ ነው

እፍረትም የኢማንሽ መለኪያ ነው
፨ --------------- ፠ -------------- ፨
ገላሽ ነውና ክቡር
መታየቱም ስለሆነ ነውር
ከተፈቀደላቸው ውጪ
ለማንም እይታ አታጋልጪ

ቦታውን ስቶ አለባበስሽ
ለባልሽ ብቻ ማድረግ ሲገባሽ
ለማንም ግሃድ ሆኖ መስህብሽ
ወንድ የሆነን እንዳይጠራብሽ
ክፉውን መዘዝ እንዳይስብብሽ
ሸይጣን እንዳይጋልብሽ
እንዳያስጠይቅሽ በጌታሽ
ለቁጣው እንዳይዳርግሽ
ጠንቀቅ በይ ለኣኺራሽ
ትኩረት ስጪ ለክብርሽ

ሴቶች አጫጭር ቀሚሶችን መልበስን በተመለከተ ለታላቁ ፈቂህ አል-አል'ላማህ ሸይኽ ሙሀመድ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ጥያቄ ቀረበላቸውና በጥበባዊው ምላሻቸው እንዲህ መከሩሽ።
1ሴቶች እቤታቸው ውስጥ አጫጭር ልብሶችን መልበስ ይፈቀድላቸዋልን ?
“ በቤቷ ከሆነና ከባሏ ውጭ ሌላ ወንድ የሌለ ካልሆነ በስተቀር አጭር ልብስ መልበስ አይገባትም። (ባሏ) ከሌላ ሰው ጋር ባለበት ሁኔታ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ እንዲሁም ገላዋን የሚያሳይ ስስ የሆነ ልብስ መልበስ አይፈቀድላትም።
ነቢዩ ﷺ "የእሳት ሰዎች የሆኑ ሁለት አይነት ሰዎች ካሉ በኋላ ለብሰው ያልለበሱ ሴቶች …፣ ጀነትን አይገቧትም። ሽታዋንም አያገኟትም።” ብለዋልና።
በመሆኑም ሴት ልጅ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ ወይም ከውስጡ ቆዳን የሚያሳይ ስስ ልብስ ከለበሰች በትክክልም ይህች ሴት "ለብሰው ያልለበሱት ሴቶች" ከተባሉት ትመደባለች።
በላይዋ ላይ ልብስ ስላለ ለብሳለች ይባላል። ልብሱ ግን (ገላዋን ለመደበቅ) ምንም ስለማይጠቅማት አልለበሰችም።”
ምንጭ☞⇘⇘
مجموع فتاوى ابن عثيمين (12/268)
2ሴቶች ለሴቶችስ እንዴት ይልበሱ?
አሁንም ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ሷሊህ አልዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ቀጣዩን ያስገነዝቡናል።
“ ሴት ልጅ ሴቶች ዘንድ መሸፈን የሚገባት የሰውነቷ ክፍል ከመዳፎቿ ማብቂያ እስከ ተረከዟ የሆነውን ክፍል ነው። የተደነገገውም ይኸው ነው። ነገር ግን በቤት ውስጥ ሴቶች ዘንድ ለስራና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ከዚህ በላይ መግለጥ ካስፈለጋት ቀሚሷን እስከ ጉልበቷ ብትሰበስብ እንዲሁም ለእጆቿም እጅጌዋን እስከ ክርኗ ብትሰበስብ ላስፈላጊ ጉዳይ ብቻ እስከሆነ ድረስ ይፈቀድላታል።
ይሁንና ይህንን አለባበስ (ሴቶች ዘንድ ብቻ ቢሆንም) የሁል ግዜ ባህሏ አድርጋ መልበሱ ግን አይሆንም።”
ምንጭ ☞⇘⇘
فتاوى الشيخ محمد بن صالح العثيمين لمجلة الدعوة " العدد 1765 / 55.
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
muharram 26/1437
Nov 11/11/2015
www.fb.com/tenbihat
ተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ