Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሃቅ መንገድ አንድ ብቻ ናት ሲባል ‹‹ስለ ፊርቃ እንዳይነሳ፣ ሙስሊሙን አትበታትኑት›› ይሉናል የስሜት ተከታዬች

የሃቅ መንገድ አንድ ብቻ ናት ሲባል
‹‹ስለ ፊርቃ እንዳይነሳ፣ ሙስሊሙን አትበታትኑት›› ይሉናል የስሜት ተከታዬች
ኢኽዋኖች የሸርክ፣ የቢድዐና የሸር ጠበቃዎች ይህን አባባል ሲሉት ይሰማሉ፡፡ የተውሂድና ሱና ትምህርት ሲሰጥ ሽርክና ቢድዐ ከነባለቤቶቻቸው ሲጋለጡ ‹‹የኡማው አንድነት አያሳስባችሁም›› ሲሉ እራሳቸውን የአንድነት ጠበቃ ሌላውን የአንድነት ፀር አድርገው ያቀርባሉ፡፡
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡
ንግግራቸው ስሜትን ከመከተል የመጣ ስለሆነ ያስቡ ዘንድና በነሱ የታለለ ካለ ይነቃ ዘንድ የሚከተሉትን ነጥቦች በአላህ ፍቃድ አስቀምጣለሁ
1) ‹‹ስለ ፊርቃ አታንሱ ሲሉ›› ምን ማለት ፈልገው ነው?
ኢኽዋኖች ዘንድ እነሱን ያልተቃወመ ከአላህ ሌላ ያለን ቢጠራም ‹‹ሱፍያን፣ ሺዐን›› ይመስል ፣ ሰሃባን ቢሳደቡም ‹‹ሺዐዎችን›› ይመስል ችግር የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት ላይ ማንነቱ የማይታወቀው ሙስሊሙን ለእልቂት የሚዳርገው ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የሚሉት አካላቸው እንዲህ ሲል ፅፋል March 29, 2012
‹‹የኢትዬጵያ ሙስሊም አንድ ሆኗል ስንል የተለያዩ የዳእዋ አካሄድ መስመሮች የሉም ማለታችን አይደለም፡፡ ተብሊግ፣ ሰለፊያ፣ ሱፍያ (አሽዓሪያ)…. ከዚህ ቀደምም የነበሩና አሁንም ያሉ፣ ምን ላይ ትኩረት ሰጥተን ነው ዳዕዋ ማድረግ ያለብን የሚለው ነጥብ የተለያየ አስተያየት ያላቸው የዳዕዋ መስመሮች ናቸው፡፡ ሁሉም ግን ኢስላምን ለማገልገል ነው ደፋቀና የሚሉት፡፡››
እንግዲህ እንዴት ሰው እንደሚያታሉ እስቲ ነጥብ በነጥብ ውሸታቸውን እናጋልጥ
1.1) ‹‹ሱፍያና፣ ተብሊግ›› ከሰለፍያ እኩል ነበሩን ወይንስ መጤዎች ናቸው?
መልሱም መጤዎች ናቸው ነው የሚሆነው፡፡ ታድያ መጤዎቹን የጥመት ቡድኖች ከጥንት ከጠዋቷ ብቸኛ ከሆነችው አንድ ሀቅ ሰለፍያ ጋር አንድ አድርገውና የነበሩ አድርገው ማቅረብ አስፈለጋቸው? ይህ ግልፅ ማጭበርበር አይደለምን? እንደ ሱፍያና ተብሊግ አይነቱ መጤ የጥመት ቡድን ምን ላይ ትኩረት ሰጥተው ዳዕዋ ማድረግ እንዳለባቸው መቼ ከጥንት ከጠዋቷ ሰለፍያ ወሰዱ ይልቁንስ ከትክክለኛው አስተምሮት የሚጋጭ የራሳቸውን የጥመት አካሄድ ፈበረኩ ይህንንም በማድረጋቸው ሃቋን አንድ መንገድ ለይተው የጥመት ቡድኖችን አበዙ፡፡
ሙስሊሞች ሁሉንም የጥመት ቡድኖች ርቀው ወደ አንዷ ሃቅ እስካልመጡ ድረስ ተበታትነዋል፡፡ አላህ ያዘዘን በሃቅ ላይ እንድንሰባሰብ እንጂ መጤውን ሁሉ በዲን ስም እንድናስተናግድ አይደለም፡፡
1.2) ደግሞ በሰለፍያና በሱፍያ ብሎም በተብሊግ መሃል ያለው ልዩነት እውነት ኢኽዋኒው እንደሚለው ‹‹ምን ላይ ትኩረት ሰጥተን ነው ዳዕዋ ማድረግ ያለብን የሚለው ነጥብ የተለያየ አስተያየት ያላቸው የዳዕዋ መስመሮች ናቸው፡፡›› ነውን?
በፍፁም ከሙሀጂርና ከአንሳሮች በኋላ የመጣን ሁሉ ሙሀጂርና አንሳርን በበጎ መከተል ብቻ ነው ያለን አማራጭ እውነት የአላህን ውዴታ ከፈለግን፡፡ ከዛ ውጭ ቁጥር ለማብዛት ተብሎ ሁሉንም የጥመት ቡድን ‹‹አንድ ነን›› እያሉ ሁለት ሃቅ ያለ ይመስል መነገዱ ዋጋ የለውም ዉርደት አንጂ፡፡
1.3) እንዴት ነው ‹‹ስለ ፊርቃ አታንሱ የሚሉን›› ታድያ ስለ ጠማማው የአህባሽ ፊርቃ (ቡድን) ለምን ያወራሉ? መጅሊሱን ስለያዘባቸው?
1.4) ግብፅ ውስጥ የተመሰረተው ይህ የጥመት ቡድን ከአላህ ውጭ ‹‹ያ አልይ እርዳታህን ለግሰን፣ ያ ሁሴን እርዳን….. ሰሃባዎችን የሚሳደቡትን›› ሺዐዎች ‹‹አንድ ነን›› ሲሉ ነበር፡፡
1.5) አገራችንም ላይም የሽርክና ኩፍር መናሃርያ የሆነውን መውሊድ ከሱፍዮች ጋር እንዲህ ሲሉ ተስማምተው ፈርመዋል
‹‹የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መውሊድ አከባበር ሥነ-ሥርዐት ብሔራዊ በዐልነቱ ታውቆ ይከበራል፡፡ ስለ በዓሉም ሆነ የነብዩን ሲራ አስመልክቶ የሚሰጡ ትምህርቶች በሁሉም ወገኖች ያለተብዲዕ፣ ያለተፍሲቅ፣ ያለተሸሪክና፣ ያለተክፊር እንዲከናወን ለማድረግ በጋራ እንሰራለን፡፡››
እንዲህ እያደረጉ ነው በዲን ስም ዲንን የሚያወድሙት፡፡ አላህ ይምራቸውና፡፡
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡
1.6) ግን እውነት ቁጥር መደመር እንኳን ይችላሉን?
ሱፊ + አሽዐሪ + ቀብር አምላኪ + ሺዐ + ተብሊግ + ተክፊር + …… እንዴት ብለው ነው አንድ የሚሆኑት?
ኡማው ተለያይቶ የነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና የሰሃባዎቻቸውን መንገድ ትቶ ሁሉም የራሱን አዲስ የጥመት መንገድ እየተከተለ ሀቁ ሲነገርና ትክክለኛው መንገድ አንድ ብቻ ነው ሲባል ‹‹አንድ ነን እኛ ማንም አይለየን›› እያሉ የጥመት ሁሉ ከለላ ይሆናሉ፡፡ በጣም አሳዛኙ ጉዳይ ደግሞ እነዚህ ዲንን አበላሾች አሳማሪ ነን ብለው ፍጥጥ ማለታቸውና ህዝቡም አላህ ካዘነለት ውጭ ተንኮላቸውን አለመረዳቱ ነው፡፡ አላህ እኛንም እነሱንም ይምራን፡፡
አዳዲስ የጥመት ቡድኖች መኖራቸውንና መከሰታቸውን ባለመቃወም እኮ ነው አላህ የጠላው ልዩነት የሚከሰተው፡፡ የጥመት ቡድኖች በተከሰቱ ቁጥር የጥንት የጠዋቷን ሃቅ ይዞ ሙጭጭ በማለትና መጤዎቹን በጠቅላላ በመራቅና ከነሱም በማስጠንቀቅ ብቻ ነው ስኬት የሚገኘው፡፡
1.7) ሌላው ከመሪዎቻቸው አንዱ ቻግኒ (ጎጃም) ላይ ሄዶ ከቲጃኒ ሱፍዬች ጋር ባደረገው ስምምነት እንዲህ ሲል ተናገረ
‹‹ዲናችን አንድ ነው፣ መዝሃባችን አንድ ነው፡፡ የአህለሱና ወል ጀመዐ መዝሀብ ነው፡፡ እኛ ዘንድ ሺዐ የለም፣ ኢስማኢልያ የለም፣ ዲንን የሚያጠፋ ቡድን የለም››
ሱብሀነላህ አይ ቅጥፈት፡፡ ኢትዬጵያ ውስጥ በግልፅ ስለማይንቀሳቀሱ እንጂ ሺዐም አለ፡፡ በነገራችን ላይ ይህን ንግግር በተናገሩበት ወቅት ኢትዬጵያ ውስጥ አህባሽ ነበር ግን የመጅሊሱን ስልጣን አልያዘም ነበር፡፡ ያኔ የሱና ወንድሞች አህባሽን ሲያስጠነቅቁ ‹‹ስለ ፊርቃ አታንሱ›› ይሉ ነበር፡፡
ዋናው ነጥብ ‹‹ዲንን የሚያጠፋ ቡድን የለም›› ብሏል ሸሃቸው ሱብሃነላህ፡፡ ከሽርክ የበለጠ ዲንን የሚያጠፋ ምን አለ?
ሽርክ ደግሞ ሊስማሙ የሄዱበት ቲጃኒ ሱፍያ ላይ አለ? ታድያ እንዲህ አይነት መሰል የጥመት ቡድኖች ያሉበትን አገር፣ የኢትዬጵያ ሙስሊም ሁሉ ‹‹አህለሱና ወል ጀመዐ ነው›› እያሉ ማታለል ለምን አስፈለገ? እንደ ኢኽዋኖች አካሄድ ከቲጃኒ ሱፍዬች ጋር የሚጣሉት መጅሊሱን ሲይዙባቸው ነውን? አላህ ይምራቸው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ማናችንም ልናውቅ የሚገባው ሃቅ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነች ነው፡፡ መጤ የጥመት ቡድኖችን ከጥንት ከጠዋቷ ሰለፊያ ጋር አንድ ናቸው ብሎ የሚሞግታችሁ ሰው ወደ እሳት እየጠራችሁ ነው፡፡ ለነፍሳችን እንዘንላት አንዷን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) ሰሃባዎቻቸው፣ ታቢኢኖች፣ አትባኡታቢኢን እነሱን በበጎ የተከተሏቸው የነበሩባትን መንገድ በመከተልና፣ መጤ ከተባሉ (ኸዋሪጅ፣ ቀደርያ፣ ጀበርያ፣ ሺዐ፣ ሙዕተዚላ፣ ማትሩድያ፣ ኩላቢያ፣ አሽዐርያ፣ ሱፍያ፣ ………. ኢኽዋን፣ ተብሊግ፣ ተክፊር፣ ቁጥብያ፣ ሱሩርያ፣ አህባሽ …….) የጥመት ቡድኖች ሁሉ እንራቅ፡፡
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://telegram.me/SadatKemalAbuMeryem