Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ምኑን ተ ፈ ተ ን ክ ና



ምኑን ተ ፈ ተ ን ክ ና

ትድረስ ለውድ ዳዒያን

የቆምከው ለተውሂድ ከሆነ ለሱና
ምኑን ተፈትነህ ምኑን አየህና
ተበደልኩ አትበል ይቀረሃል ገና
ሂደትህን አርመህ በአቋምህ ፅና
ከአላህ ተሳሰብ በሱ ተመካና

🌴 🌴

የአላህ መልእክተኛ፣ የሰው ልጆች አለቃ፣ የመልእክተኞች መሪና የነቢያት መደምደሚያ የሆኑት ሙሐመድ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ተጋርጦባቸው የነበሩት ፈተናዎችና አስቸጋሪ መከራዎች ሁሉ ምክንያታቸው ይዘውት የመጡትን ዲን ለመመከትና ከመነሻው ለማጥፋት ሲሉ በተለይ የመካ ቁረይሾች በተለያዩ ዘዴዎች ሲያራምዱት የነበረው የጥፋት ስልቶች ውጤት ናቸው።

ሲራ ኢብኑ ሂሻም 1/328 ላይ ቀጣዩ ሰፍሯል።

«የመካ ቁረይሾች የነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ዳዕዋን ተፅዕኖ አሳዳሪነት ሲመለከቱና ከነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] በፊት እንደ ዘይድ ቢን አምር ቢን ኑፈይልና እንደ ወረቃ ያሉ ወደ ጣዖት አምልኮ የሚጣሩ የነበሩት ሰዎች ስኬታቸው ወይም ጉዟቸው ግዜያዊና የተገደበ እንደነበረው ኣለመሆኑን ሲመለከቱ ሙሀመድንና [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] የተከተሏቸውን በመቃረን ተጋፈጧቸው።

ቁረይሾች የተከበረው ካዕባ (ሃረም) በአካባቢያቸው ስላለ ብቻ ሲያገኙበት የነበረውን ጥቅማጥቅሞች የገደበባቸውን፤ ራሳቸውን ከፍ በማድረግ በሌሎች ላይ ሲኩራሩበት የነበረውን ሲንድባቸውና ሃጢኣቶችንና አጥፊ የሆኑ ነገሮችን እንዳይፈፅሙ ስሜታቸውን በመገደብ ፊትለፊት ሲጋፈጣቸው ይህንን ዲን ለመዋጋት የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ በነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ላይ የማባበያና የመስፈራርያ መዳረሻዎችን መፈፀም ተያያዙ።

ዋና ዋና ከሚባሉት ከነዚህ ስልቶች መካከል

የመጀመርያው ስልት:- መለማመጥ

የነቢዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዳእዋ ለማስቆም የተጠቀሙት የመጀመርያው ሙከራ አጎታቸው አቡ ጣሊብ ላይ ጫና መፍጠር ነበር። በዚህም ከአጠገባቸው እንዲያባርሯቸው ለነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሚሰጡትን ከለላ እንዲያቆሙ የቁረይሽ ታላላቅ ሰዎች ወደ አቡጣሊብ ሄደው "የወንድምህ ልጅ አማልክቶቻችን ይሰድባል፣ ሃይማኖታችንም ያነውራልና ወይ ከኛ ላይ ዝም አሰኝልን። ወይም በመሃከላችን አትግባ" ሲሏቸው አቡጣሊብም ርህራሄ በተሞላበት ለስላሳ ቃላት በጥሩ ሁኔታ ሹማምንቱን መለሷቸው። እነሱም ትተዋቸው ሄዱ።»
【ኢብኑ ሂሻም ከኢብኑ ኢስሃቅ ዘገባ ወስደው በሲራ ኪታባቸው 1/328 ላይ ካሰፈሩት】

ሁለተኛው ስልት:-

የአላህ መልእክተኛን [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] እና አጎታቸው አቡጣሊብን ከአቋማቸው እንዲያፈገግፍጉ በማስጠንቀቅ ስለ ማስፈራራታቸው።

« ነቢዩ [የአላህ ሰላምና እዝነት ይስፈንባቸውና] ባሉበት ዳዕዋ ላይ ገፍተውበት ወደ አላህ ዲን ጥሪ በማድረግ በይፋ ሰብከው የበላይ ሲያደርጉ ቁረይሾች ተቆጡባቸው፣ በመመቅኘትም ጠላት ሁኑባቸው። ለሁለተኛ ግዜ ወደ አጎታቸው አቡጣሊብ ሄደው “አቡጣሊብ ሆይ! አንተ በኛ መሃል በእድሜህ ከፍ ያልክ፣ ክብርና ቦታ ያለህ ሆነህ ሳለ የወንድምህን ልጅ ከልክልልን ብለንህ ነበር፤ ነገር ግን ከኛ ላይ አልከለከልከውም፣ አላስቆምክልንም።” ኣሉትና የነቢዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዳዕዋና የአቡጣሊብን ሽፋን በትእግስት ማለፍ እንደማይችሉና እስኪያስቆሙላቸውም ግፊት እንደሚያደርጉ ካልሆነም ከሁለት አንዳቸው እስኪጠፉ ድረስ እንደሚታገሏቸው ምለው ተናገሯቸው። አቢጣሊብ ይህ የህብረተሰቡ እሳቸውን በማግለል ለይተው ጠላት የማድረግን ቆራጥ የሆነ ማስፈራርያ እንደታዘቡ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን አሳልፎ ለመስጠትም ሆነ ደጋፊ አጥተው የጠላት መጫወቻ በመሆን እንዲዋረዱ አልፈቀዱም ነበር።

ለዚህም ቁረይሾች ከሳቸውና ከነቢዩ አንፃር ያላቸውን አቋምና የተናገሯቸውን የማስፈራርያ ቃላት ሁሉ አደረሷቸው። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በጀመሩት ጉዳይ ላይ እንዲፀኑና እንዲገፉበት፣ ራሳቸውንም እንዲጠብቁ ገልፀውላቸው፤ በበኩላቸው ነቢዩን በማይቋቋሙት ነገር ላይ እንደማይተዉዋቸው ያቅማቸውንም ሁሉ ድጋፍ ከመስጠት ወደ ኋላ እንደማይሉም ቃል ገቡላቸው።»

【ሲራ ኢብኑ ኢስሃቅ ገፅ145ላይ እንደሰፈረው】

ሶስተኛው ስልት:-
~> 🌴 🌴

ስምህን ቢያጠፉ
ዝናህን ቢያጎድፉ
በሀሰት ቢከስሱህ
ያላልከውን ቢሉህ
ቢመኙ ሊያስቆሙህ
ከሰዉም ሊለዩህ
ከዳዕዋህ ሊገቱህ
ቢያሴሩ ሊጥሉህ
ቢያስቡ ሊያጠፉህ
ብዙም አትገረም
ለዚህ አትታመም
ፈለጉን እስከያዝክ
ከዚህ አታመልጥም።
※:::::::::::※::::::::::::※::::::::::※
10 ሰፈር 1437 ፠ 23/11/15