Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቂዳዊ ጥያቄና ምላሽ ከሸይኽ ሷሊህ ቢን ዐብዱረህማን ቢን ዐብደላህ አልአጥረም ረሂመሁላህ



🌐ዓቂዳዊ ጥያቄና ምላሽ
الأسئلة والأجوبة في العقيدة

ከሸይኽ ሷሊህ ቢን ዐብዱረህማን ቢን ዐብደላህ አልአጥረም ረሂመሁላህ
بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن اهتدى بهداه. وبعد:

س1/ عرف العقيدة والمعتقد ولم سيمت بذلك؟!
ዐቂዳ ወይም ሙዕተቀድ ምንድነው [እምነት] ለምንስ በዚህ ቃል ተሰየመ ?

«'ዐቂዳ' የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ ማመን ማለትም "ኢዕቲቃድالاعتقاد" ከሚለው ቃል የተወሰደ ነው። 'ዐቂዳ' ሲባል የተፈለገው ትርጉም ከልብ ያረጋገጡት፣ ያመኑት፣ የቋጠሩት እንደማለት ነው።
"ሙዕተቀድ" ሲባልም ትርጉሙ የአላህን በአምላክነቱ፣ በጌትነቱ ብቸኛ መሆኑን እንዲሁም አምልኮት የግድ ለሱ ብቻ የሚገባ መሆኑንና መልካም የሆኑ ስሞችና የላቁ ባህርያት እንዳለው ቁርጥ ባለ ሁኔታ ማመን (በልብ መቋጠር) ማለት ነው።
ከዚህ መነሻም ነው ስለ እምነት የተፃፉ የአላህን ብቸኛ አምላክ መሆን የሚዘክሩ መፅሀፍቶች
[ኩቱቡል ኢዕቲቃድ كتب الإعتقاد]
ማለትም የእምነት መፅሀፍት በሚል የተሰየሙት።

ኢማም አጥጠሃዊ [ረሂመሁላህ] እንዳሉትም “ የአላህ ብቸኛ ተመላኪነትን በተመለከተ አላህ ብቸኛና ምንም አጋር የሌለው መሆኑን በአላህ ፈቃድ የምናምን "معتقدين" (በልባችን አጥብቀን የምንቋጥር) ነን።” ብለዋል።
እምነት ዐቂዳ በሚል በዚህ ስያሜ የተሰየመችው ቁርጥ ያለ እምነትን፣ እውነተኛ የሆነ እርግጠኝነትን የምታመላክት በመሆኗ ነው። ጠበቅ ተደርጎ የተቋጠረን ነገር መፍታት ከባድ እንደሆነ ይታወቃልና።
አላህ እንዳለውም
{وَلَكِنْ يُؤَاخِذُكُمْ بِمَا عَقَّدْتُمُ الْأَيْمَانَ}.
«ግን መሐላዎችን (ባሰባችሁት) ይይዛችኋል፡፡»
【አልማዒዳ: 89】

[አላህ ስለ መሃላ ደንብ ሲገልፅልንና አስጠያቂ የሆነውን የመሃላ አይነት ሲያስረዳን "ዐቀድትቱምعَقَّدْتُمُ" የሚለው ቃል የሚሰጠው ትርጉም አምናችሁበት በማላችሁት፣ ሆን ብላችሁ በማላችሁት፣ ኣስባችሁበት በማላችሁት ነው የሚል ነው፡፡ ስለሆነም "ዐቀደ" ሲባል ቋጠረ፣ አጥብቆ አሰረ፣ እንደማለትና ከልብ አመነ የሚለውን ትርጓሜ ይሰጣል። ስለሆነም ከጥንት ጀምሮ ሊቃውንቶቻችን ይህንን ቃል እምነትን የሚያስረዳ ርእስ አድርገው ይገለገሉበታል።]
ኢብኑ ተይሚያም ረሂመሁላህ ዐቂዳ የሚለው ቃልን እምነት ለማለት እንደተጠቀሙበት በየንግግራቸው ማወቅ ይቻላል። ለምሳሌም
«በማስከተል ይህ የምትድነዋ የተራፊዋ፣ የምትረዳዋ ቡድን የአህሉ ሱንና ወልጀማዓ ኢዕቲቃድ (እምነት) ነው።» ብለዋል።
🌴 🌴
ስለዚህም ዐቂዳ ወይም ኢዕቲቃድ ማለት ቁርጥ ያለ በልብ የተቋጠረ እምነት ማለት ነው።
በመጨረሻም የዚህ ትምህርት አስፈላጊነት
①ኛ/ አንድ ዳዒ ወይም ሸይኽ በየትምህርቱ ዐቂዳ፣ ዐቂዳችን እያለ ሲናገር ስለ እምነት፣ ስለ እምነታችን፣ ስምናምንበት ጉዳይ እየተናገረ መሆኑን እንድንገነዘብ

②ኛ/ የኢስላም ሊቃውንቶች ለአንድ ትምህርት ወይም ርእስ ስያሜ ሲሰጡ በተለይ የዒባዳ (የአምልኮ) ጉዳይ ከሆነ ቃላዊ ፍቺውን እንኳን ከቁርኣን፣ ከሀዲስ እና ከሌሎች መሰረታዊ የመረጃ ምንጮች የሚወስዱ መሆኑንና በዘፈቀደ ይኸ ይኸ ነው እያሉ የራሳቸውን ራእይ ብቻ እንደማይሰጡ እንድንረዳ በማሰብ ነው።
س2/ هل يوجد إنسان بلا معتقد؟
س 3/ ما المعتقد الحق ... ؟
ለመሆኑ ያለ እምነት የሚኖር ሰው አለን ? ትክክለኛው እምነትስ ምንድነው ? …

---------------※ --------------
09 ሰፈር 1437/ 22 Nov 15
©ከተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ
≈>>>