Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እህቴ... ትግስት መለያሽ ይሁን!

እህቴ... ትግስት መለያሽ ይሁን!
ኒዕመት ቢንት ሰለፊያህ

እንዲህ ዓይነት መካሪ እህቶቻችንን አላህ ይጠብቃቸው ስራቸውም አላህ ይቀብላቸው በኢኽላስ የአላህ ፊት ብቻ ተፈልጎበት የተስራ ስራ ያድርግገላቸው! አላህ ይጠብቃቸው ይጠብቀን! ውድ እህቶች አንበቡት አላህ በተግባረ ከሚያሳዩት ያደረገን!

«እህቴ ትግስት መለያሽ ይሁን»
ይህች አለም የስራ የልፍትና የፈተናም ናት! ወደ ሰዎች የተላኩት መልዕክተኞች ሁሉ ያገኙት ምላሽ በማመን እና በክህደት መካከል ነው። ሁሉም አልተቀበላቸውም፤ ከፊሎቹ አምነናል ሲሉ ከፊሎች ደግሞ ክደዋቸወዋል።

አምነናል የሚሉት ሁሉ ደግሞ በእርግጥም ይፈተናሉ። አላህም እንዲህ ይላናል፦

أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُتْرَكُوا أَن يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ
«ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን?»

ፈተና የሙኡሚኖች ናት! ወደ እዚህ ምድርም የመጣነው ለፈተና ነው። እዚህ ፈተና ነው አኼራ ደግሞ ውጤት ነው።

الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ
{ያ!የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ የማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው።እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው።}

አላህ ባሮቹን በችግር ይፈትናቸዋል። ከዱኒያችግር በባሰ በቀልብ ላይ በሽታን የሚያመጡ፣ ወደ ወንጀል የሚያበረታቱ፣ ወደ ኒፋቅ፣ ወደኩፉር በዲናችን ላይ ፈተና የሚሆኑ ሰዎችም ይገጥሙናል። መታገስና በዲናችን ላይ መፅናት ከእኛ ይጠበቃል። አላህ እንዲህ ብሏል፦
{وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ}
{ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል። ትታገሳላችሁን ጌታህም ተመልካች ነው።}

በፈተናዎች መወዛወዝ የለብንም በዲናችን ላይ መፅናት እና ትግስት ማድረግ ግዴታችን ነው። እህቴ፣ ልጅ እንቢ ቢልሽ፣ ትዳር ቢዘገይብሽ፣ ባልሽ አዛ ቢያደርግሽ፣ ልጅ ቢሞትበሽ፣ ድህነት ቢፈራረቅብሽ፣ በሽታም ቢነካሽ፣ ጎረቤት አዛ ቢያደርግሽ፣ በሂጃብሽ ቢያሳንሱሽ...ታገሽ!

አላህ በፈተነን ጊዜ ፈተናውን ከጠላንና ከአላህ ተስፋን ከቆረጥን ፈተናው ይጨምራል በመከራ ላይ መከራ በፈተና ላይ ፈተና ይፈራረቅብናል።
የአላህ መልዕክተኛ {ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም} እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ አንድን ባሪያውን በወደደው ጊዜ ይፈትነዋል ፈተናውን የወደደ አላህ ይወደዋል፤ ፈተናውንም የጠላ አላህ ይጠላዋል።»

አላህ ፈተናን ለሰዎች አድርጎዋል። አላህ የወደደውን የማይፈትንና ድሎትን ብቻ የሚያደርግለት ቢሆን ኖሮ፤
መልዕክተኞች ምንም አይነት ፊትና እና ችግር ባነካቸው ነበር። እነሱ ግን ከማንም በላይ ተፈትነዋል።

እንዲሁም እኛ ተደላድለን ኪታባቸውን እያማረጥን የምንቀራቸው ታላላቅ አሊሞች እንደኛ ተደላድለው አልፃፉትም። ከሃገራቸው ተሰደዋል፣ ተርበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታሰረዋል... በፈተናቸው ለታገሱትና በዲናቸው ላይ ለፀኑት በአላህ መንገድ ላይ ለታገሉት አላህ ቃል የገባውን ይፈፅማልና ካሰቡበት አድርሷቸዋል።
አስተውሉ!!

وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا. وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ
{እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን። አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው።}

አማኝ በፈተና ጊዜ ይታገሳል። እምነቱም ይጨምራል!!


( وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُواْ إِنَّا لِلّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعونَ )

{እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን ታጋሾች "አበስር"}

በመቀጠልም አላህ እንዲህ በማለት ያበስራቸዋል፦

(أولئك عليهم صلوات من ربهم ورحمة وأولئك هم المهتدون)
{እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾኑ ምሕረቶች ችሮታም አልሉ። እነርሱም (ወደ እውነት) ተመሪዎች እነርሱ ናቸው።}

ሙናፊቅ በፈተና ጊዜ ማንነቱ ይጋለጣን ልቡ ላይ የነበረው ክህደት በአንደበቱ ይመሰክራል። እነሱ አላህ በእርግጥ እንዳላቸው ናቸው።

አላህም እንዲህ ይላል፦
وَمِنَ النَّاسِ مَن يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَى حَرْفٍ

{ከሰዎችም "ከሃይማኖት"በጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አልለ።}

የዚህ የሙናፊቅ ባህሪውና ውጤቱም አላህ እንዳለው ነው።
فَإِنْ أَصَابَهُ خَيْرٌ اطْمَأَنَّ بِهِ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ انقَلَبَ عَلَى وَجْهِهِ خَسِرَ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةَ ذَلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ
{መልካም ነገር ቢያገኘው በእርሱ ይረጋል
መከራም ብታገኘው በፊቱ ላይ ይገለበጣል። የቅርቢቱን ዓለምም የመጨረሻይቱንም ከሰረ። ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው።}

ያ! አላህ ከሙኡሚኖች አድርገን በደስታ ጊዜ አመስጋኝ፣ በችግር ጊዜ ታጋሽ ያድርገን። ቀልባችንን ከኒፋቅ ጠብቅልን

ባረከላሁፊኪ!!

© ተንቢሀት

Post a Comment

0 Comments