Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማረኝ ጌታዬ ሆይ Gtm



ማረኝ ጌታዬ ሆይ 
ያምና የካቻምና ክምሩን ወንጀሌ
የዛሬን የትላንት የከፋው አመሌ
ሳስታውስ በዛብኝ በረታ ለቀልቤ
አልዘለቅ አለኝ ቆጥሬና አስቤ

የጄን ወንጀል ሳስብ ምላሴ እየመጣ
ያይኔ ሲያቃጥለኝ ደግሞ የግሬ ጣጣ
እጅግ ያስፈራኛል ህልፈቴ እንዳይመጣ 
በድፍርስ ተግባሬ በጨቀየ ስራ 
ቀብሬን ብጎበኘው ደርሶ የኔ ተራ 
ምን ይሆን እጣዬ 
የቀብሩ ድርሻዬ 
ብዬ ሳሰላስል እጅጉን ጨነቀኝ
ክምሩ ወንጀሌ አሳሞ አማቀቀኝ
አዛኙ ጌታዬ በዝነትህ ጠብቀኝ
አምናለሁ ጌታዬ ባርያህ ነኝ ርካሹ
ስራው ያላማረ ደም ስጋው ብልሹ
…… ባመጽ የቆሸሹ!!
ባበዛሁት ወንጀል ቀልቤ የቆሸሸ
አልጸዳም እያለኝ እየጠቀረሸ
ነኝና ጌታዬ ………
በሰፊው እዝነትህ አውጣኝ ከወንጀሌ 
ቀብሩን ሳልገናኝ ሳይነዳኝ አጀሌ
አንተንም ስገናኝ ማረኝ የኔ ጌታ
ተስፋ አይቆረጥም በራሕማን ችሮታ
አቋድሰኝ በዝነትህ ከጀነት ገበታ

በሙሓመድ አቡ ዒምራን

Post a Comment

0 Comments