Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከላይ ነው ትእዛዙ!!



“ከላይ ነው ትእዛዙ!!”

ንፁህ እና ጥብቅ የሆነችን ሴት በዝሙት መወንጀል ከሰባት ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች አንዱ እንደሆነ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሣቸው ገልፀዋል፡፡ ከታላቁ ሶሐባህ አቡ ሁረይራህ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!!”
ሶሐቦች “ምንድን ናቸው እነሱ? የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” ሲሉ ጊዜ እንዲህ አሉ፡-
1. በአላህ ላይ ማጋራት
2. ድግምት
3. አላህ በሐቅ (አግባብ ሆኖ ሲገኝ) ካልሆነ እንጂ እንዳትገደል እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል
4. ወለድ መብላት
5. የየቲምን ገንዘብ መብላት
6. (በሙስሊሞችና በከሃዲዎች መካከል) ጦርነት በሚካሄድበት ጊዜ መሸሽ
7. ጥብቅ የሆኑና የዘነጉ (የሚወነጀሉበትን ነገር የማያውቁ) ሴቶችን በዝሙት መወንጀል!! [ቡኻሪና ሙስሊም]
ሰባቱንም በሚገባ እናጢናቸው፡፡ ለጊዜው ግን ሰባተኛው ላይ እናነጣጥርማ፡፡ እህቶቻችንን ወንድሞቻችንን ባላዩት ባልሰሙት ባልጠረጠሩት በዝሙት የምንወነጅላቸው ስንቶቻችን ነን?!! ልብ በሉ! ዝሙት ከባድ ወንጀል መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በከባድ ወንጀል ሰዎችን መወንጀል ደግሞ የከበደ ነው፡፡ አንዲትን ሴት ወይም አንድን ወንድ በዝሙት የወነጀለ ሰው “ፈፃሚዎቹ መርፌና ክር ሆነው ድርጊቱ በተጨባጭ ሲፈፀም አይቻለሁ” የሚሉ አራት አስተማማኝ ምስክር ሊያቀርብ የግድ ይለዋል፡፡ “ተቃቅፈው አይቻለሁ” “አንድ ላይ ነበሩ” “ሲስማት አይቻለሁ” … አይሰራም፡፡ “በአይኔ በብረቱ ዝሙቱ ሲፈፀም አይቻለሁ” የሚሉ አራት ምስክር ካልተሟላ ወንጃዮቹ እያንዳንዱ ሰማንያ ሰማንያ ጅራፍ ይጠብቃቸዋል!!!! ሌላም አለባቸው፡፡ ሀያሉ ጌታ እንዲህ ይላል፡-
))وَالَّذِينَ يَرْمُونَ الْمُحْصَنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَأْتُوا بِأَرْبَعَةِ شُهَدَاءَ فَاجْلِدُوهُمْ ثَمَانِينَ جَلْدَةً وَلَا تَقْبَلُوا لَهُمْ شَهَادَةً أَبَدًا ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ((
((እነዚያም ጥብቆችን ሴቶች (በዝሙት) የሚሰድቡ ከዚያም አራትን ምስክሮች ያላመጡ፡
ሰማኒያ ግርፋትን ግረፏቸው፡፡
ከነርሱም ምስክርነትን ሁል ጊዜ አትቀበሉ!!
እነዚያም እነሱ አመፀኞች ናቸው።)) [አንኑር፡ 3]
እስኪ ለአፍታ እንቁምና ወደ ኋላ እንመልከት፡፡ ስንቱን በዝሙት ወንጅለናል፡፡ የስንቱን ክብር አጉድፈናል? ጌታዬ ሆይ! ያለፈውን ይቅር በለን፡፡ በቀሪው ህይወታችንም ጠብቀን!!
ይህ በንዲህ እንዳለ … ዛሬ ቀኑ ዓሹራ ነው። አላህ ሙሳ ዐለይሂሰላምን ከፊርዓውን መንጋጋ ነፃ ያወጣበት ቀን። እኛ ሙስሊሞች ይህን ቀን በሱናው መሰረት በፆም እናሳልፈዋለን። ሺዓዎችስ? ከስር ያለውን ምስል ተመልከቱ፡፡ በዚህ መልኩ ነው የሚያሳልፉት፡፡ “ምነው? ጤናም አይደሉ?” ካላችሁ መልሱ አጭር ነው፡፡ “ከላይ ነው ትእዛዙ!!!”
ዓኢሻህ የምንኮራባት እናታችን ናት!! ጌታችን ((ሚስቶቹም (ለአማኞቹ) እናቶቻቸው ናቸው!!)) ይላል፡፡ [አልአሕዛብ፡ 6] ይሄ የጌታችን ችሮታ ነው፡፡
ሺዓዎች የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ባለቤት እናታችን ዓኢሻን በዝሙት ይወነጅሏታል። ዝሙተኛ ናት ብለው ስለሚያምኑ እናትነቷን ክደዋል። ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ አንድ ጊዜ የሆነ ሰው ይመጣና “አንዳንድ ሰዎች እናታችን አይደለሽም እያሉ ነው” ይላታል፡፡ አንበሳዋ ምን ብትል ጥሩ ነው? “እውነት ተናግረዋል! እኔ የአማኞች እንጂ የመናፍቃን እናት አይደለሁም!!” ልክ ብለሻል የኔ እናት!! ልክ ብለሻል የኔ ጀግና!! የማን ሚስት ነሽና! የማን ልጅ ነሽና!
ዓኢሻዬ የኔ እናት
ጀግና የጀግና ልጅ ናት …. ባለ ብሩህ ህሊና
በሐያእ በሱና የታነፀች …. ገና እድሜዋ ሳይጠና
ቆንጆ የቆንጆዎች አለቃ
አስተዋይ ህሊናዋ የነቃ
አንደበተ ርቱእ ናት …. ምላሷ ማር የሚተፋ
እሷን እናቴ ያረገ …. ሀያል ጌታዬ ክብሩ ይስፋ!!
መናፍቃን በክፉ ቢወነጅሏት ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታ ከሰማያት በላይ ሆኖ ንፁህ መሆኗን ዘላለም የሚቀራ አንቀፅ አወረደ፡፡ ግና ዛሬም እነዚያን መናፍቃን ተምሳሌት ያደረጉ ቂሎች ከጥፋታቸው ሊመለሱ ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ “ጂልና ወረቀት የያዘውን አይለቅም” ነው ነገሩ፡፡ ውስጥ አዋቂው ጌታ ንፁህነቷን ቢያውጅም ሰማያዊውን አዋጅ “አሻፈረን” እንዳሉ ናቸው፡፡ እነሱም ቆሻሻዎቹ ራፊዷዎች (ሺዐዎች) ናቸው፡፡ አዎ ቆሻሻ ናቸው!! ለዚያም ነው እነሱን አብጠርጥሮ የሚያውቃቸው ከቀደምት አበው አንዱ የሆነው ዓሚር አሽሸዕቢይ ረሒመሁላህ (104 ሂ.) “እንስሳ ቢሆኑ ኖሮ አህዮች ነበር የሚሆኑት!! የወፍ ዘር ቢሆኑ ጥንብ አንሳ ነበር የሚሆኑት፡፡” ብሎ በሚሰቀጥጥ መልኩ የገለፃቸው፡፡ [መጅሙዑልፈታዋ፡ 4/472]
እናም እነዚህ ቆሻሻዎች ዛሬም ድረስ ምላሳቸውን ሊሰበስቡ አልፈቀዱም፡፡ ዛሬም ድረስ እናታችንን በዝሙት እየወነጀሏት ነው፡፡ ዛሬም ድረስ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ክብር ላይ እየተረማመዱ ነው፡፡ ጠቢቡ ጌታ ግን ድንቅ ፍርዱን በነሱ ላይ እያሳየን ነው፡፡ ((አላህ ከነዚያ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል” አይደል ያለው? [አልሐጅ፡ 38] ከላይ ባሳለፍነው የቁርኣን አንቀፅ መሰረት ንፁሃንን በዝሙት የሚወነጅል 80 ጂራፍ ይገረፋል፡፡ ይሄው ሺዐዎች በያመቱ ሙሐረም 10 ላይ እራሳቸውን በስለት እንዲገርፉ የአላህ ውሳኔ ሆኗል፡፡ የሰው ልጅ ህሊናው እያለ ያደርገዋል ተብሎ በማይታሰብ መልኩ እራሳቸውን በደም እያጨቀዩ እራሳቸውን እየገረፉ እራሳቸው እንዲያለቅሱ ወሰነባቸው፡፡ ታዲያ ((አላህ ከፈራጆች ሁሉ የበለጠ ፈራጅ አይደለምን?!))[አትቲን፡ 8] እንዴታ!! ((እርግጠኛ ሆነው ለሚያምኑ ሰዎች ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው?!!)) [አልማኢዳህ፡ 50]
ምን ይሄ ብቻ!! እሷን በዝሙት ሲወነጅሉ እራሳቸው በዝሙት መጨማለቅ መታወቂያቸው ሆነ እንጂ!! “ምን ማስረጃ አለህ? ይሄስ ዞሮ በዝሙት መወንጀል አይደለም ወይ?” የሚል ይኖር ይሆናል፡፡ አንድ ሰው እራሱ ካመነ ምስክር አያስፈልግም፡፡ “አልኢዕቲራፉ ሰይዪዱል አዲልላህ!” ይባላል፡፡ “በራስ ላይ መመስከር (ማመን) የማስረጃዎች ሁሉ ቁንጮ ነው” እንደማለት፡፡ እናም እራሳቸው ሺዐዎቹ የኮንትራት ወይም “የሙትዐህ ጋብቻ” ከመፈፀምም በላይ “ይህን ያልተቀበለ ከኛ አይደለም” ብለው ዝሙትን ከመፈፀምም በላይ ዲን አድርገውት አረፉ፡፡ [ወሳኢሉሽሺዐህ፡ 4/438] ሌሎችም ብዙ ኪታቦቻቸውን መዘርዘር ይቻላል፡፡ አዑዙ ቢላህ!! እነዚህ ናቸው እንግዲህ ዓኢሻን በዝሙት የሚወነጅሉት!!

(ተፃፈ፡ በአቡበክር ሲራጅ እና ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 13/2008

Post a Comment

0 Comments