Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እናታችን አዒሻ(ረዲየሏሁ ዓንሃ)ምሁር ነበረች ዛሬም ለኛ አርዓያች ነች!

እናታችን አዒሻ(ረዲየሏሁ ዓንሃ)ምሁር ነበረች ዛሬም ለኛ አርዓያች ነች!
--------- - - - - - - - - - - - - - - -
ስለ እናታችን አዒሻ(ረዲየሏሁ ዓንሃ)
በጣም የሚገርመው ካፊሮች እድሜዋ ትንሽ ሆኖ ነው ለትዳር የታጨጭው እያሉ ይወነጅላሉ። ሺኣዎች በዝሙት ይወነጅሏታል። እንደው"ከሳሽ ክስ አያጣም!"ከደረሰችበት ደርሶ የሷን አንድ ተግባር የሚፈፅም ይኖር ይሆን በአሁን ዘመን በእውነት አለን? እንጃ! ምንአልባት የእሷን ተምሳሌት ሊሆን የፈለገ አላህ ያዘነለት ካልሆነ በቀር የት ይገኛል ምን እሱም አልባትም የሚንደረደር ካልሆነ በቀር…
እናታችን አዒሻን የሚወነጅሉት ውስጣችሁ የተጠናወታቸው ቅናት እንጂ ሌላ አይደለም። አላህ ከሰባት ሰማያት ባላይ የቁርአን አቀፅ በማውረድ ንፁህነቷን አረጋግጦዋል። ከታላቋ ኸዲጃና ከፍጢመቱ ዘህራእ‘አንፀባራቂዋ ’(ረዲየሏሁ ዓንሁማ)ቀጥሎ ዓኢሻ በኢስላም ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣት ድንቅ ሴት ናት። እናታችን ምሁር ነች አዒሻ "2210"ሃዲሶችን አስተላልፋለች፡፡ እርሷ በትዳሯ ደስተኛ ጠንካራና ጥንቅቁ ሴት ነበረች። የኢስላም ጠላቶች እንደሚሉት አይደለም ነቢዩ(ﷺ) አዒሻን ማግባታቸዉ የስነልቦናም ይሁን ሌላ ጥቃት በአዒሻ ላይ አልደረሰም። እርሷም ለነብዩ(ﷺ) ጋብቻውና በትዳር ህይወቷ እጅግ ደስተኛ እንደነበረች ነው የገለፀችው፡፡ ነቢዩ(ﷺ) አዒሻ ሲያገቧት አልፈራችም አላዘነችም ለመሸሽም ሆነ ወደ ኋላ ለማለት አልሞከረችም፡፡ ደስተኛ ነበረች! አዎን አዒሻ በጋብቻዋ በጣም ደስተኛ ነበረች፡፡
☞እጅግ ብዙ የነቢዩ(ﷺ)አባባሎችን ድርጊቶችን ባህሪያቸውን መመዝገብ ችላለች፡፡
✍ከርሳቸው ሃዲሶችንን ማስተላለፍ አስችሏታል፡፡
✍ከሴቶች ሁሉ ግንባር ቀደም ምሁር መሆን ችላለች፡፡
✍ለበርካታ ሰሃቦች መምህርት መሆን ችላለች፡፡
✍ከነቢዩ ሞት በኋላ(ለ48)ዓመታት ስታስተምር ቆይታለች፡፡
✍የተሳካላት መምህርት መሆን ችላለች፡፡
✍ነቢዩ(ﷺ) “ግማሽ እምነታችሁን ከዚች ቀይ ሴት አዒሻ/ ተማሩ” ሲሎ መክረዋል፡፡
✍ትንተና፣ ማብራሪያና፣ ለፈታኝ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት አስችሏታል፡፡
☞ይህንንም አቡ ሙሳ ከተናገሩት አስተያየት እንረዳለን፡- “እኛ የአላህ መልዕክተኛ ባልደረቦች ማንኛዉም አይነት አስቸጋሪ ጥያቄ ሲያጋጥመን በአዒሻ አማካኝነት መፍትሄ እናገኝ ነበር፡፡ (ቲርሚዚ የዘገቡት)
እሷን ለቀቅ አድርጉ! ከቻላችሁ ስራዋን አጥብቃችሁ በመያዝ ተግብሩ ትድኑ ዘንድ! ካልቻላችሁ ዝም በሉ በእናንተ አፍ ስሟ መጥራቱ በራሱ ትልቅ ወንጀል ነው የሚሆንባችሁ!!!

Post a Comment

0 Comments