Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እህቴሆይ: ትግስት ስንቅሽ ፣ ቁርዓን ጋደኛሽ አድርገሽ ያዥ



#እህቴሆይ:

አዒሻ (አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ልጅ እንዳሌላት(እንዳልወለደች) ታውቂያለሽን?ይህም ሆኖ ሳለ ግን አንድም የሱና ኪታቦች ውስጥ "አንቱ የአሏህ መልክተኛ ሆይ: አሏህ ዘር እንዲሰጠኝ ዱዓ አድርጉልኝ" ብላ መጠየቁዋን የሚጠቁም ዘገባ አይገኝም።

ታውቂያለሽን? ነብዩ ሙሃመድ (ዓለይሂ_ሰላቱ_ወስሰላም) አዒሻ እድሜዋ 18 እያለ ነበር የሞቱት።
በጣም ይወዷት ነበር ፣ እርሷም በጣም ቅናት ነበራት(የፍቅር)።
እርሳቸው ከሞቱም ቡሃላ 47 አመታት ኖራለች።ግን እንደዛም ሆኖ ስለ ትዳር ተቆጭታ አታውቅም።



ግን እርሷ በዒልም እዳ በዒባዳ ተጠመደች ፤ ለታላላቅ ሰሃቦች አስተማሪም ሙፍቲም ነበረች ።
ህይወት ፥ መውለድ፣ማግባት፣ቤት፣ጣውንትነት፣ገነዘብ፣የወላጆች ሞት፣ልጆችን ማጣት ላይ የምትቆም አደለችም!!!

አሏህ አንድን ነገር አይወስድም፣በረሱ ቦታ የተሻለን ቢተካ እንጂ

ዱንያ ደግሞ የፈተና አገር ነች፣ለማንም ሙሉ ሆና አታውቅም

ልብሽን፥ በኢማን፣በመውደድ፣በአሏህ ላይ ግምት ሙይው።
ግዜሽን ደግሞ፥ እውቀትን በመፈለግ፣ራስሽነን እና ህብረተሰብሽን በሚጠቅም ነገር ሁሉ ሙይው።

ትእግስትን ስንቅሽ … ቁርዓንን ደግሞ ጓደኛቸው አድርጊ።

{{ቁርዓንን አንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም}}

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ እንዲህ ይላል፥ "ለሶስት ነገሮች ብዬ እንጂ ዱንያ ላይ መቆየትን አልወድም ነበር ፥ ለፆም፣ለሊት ስግደት፣እና ልክ ከቴምር ጥሩዎቹ ፍሬዎች እንደሚመረጡ ሁሉ ጥሩ ንግግሮችን የሚመርጡ ሰዎችን ለመቀማመጥ"

ምናለ ህይወትን እነዛ የመጀመርያዎቹ ትውልዶች እንደተረዷት ብንረዳት፣ከቅርቢቱ እና የሩቂቱ ህይወት ጥሩ የተባለውን ሁሉ ባሸነፍን(ባገኘነው) ነበር!!!

ወላሁአእለም

#أُخَـيَّــتي

هل تعلمين أن عائشة رضي الله عنها لم تنجب ولم يكن لها ذرية ومع ذلك لم يوجد أثر في كتب السنة النبوية أن عائشة قالت : يا رسول الله ادعُ الله لي بالذرية !!

•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

وهل تعلمين أن النبي صلى الله عليه وسلم مات عنها وعمرها ١٨ سنة وكان شديد الحب لها وكانت شديدة الغيرة
أي عاشت بعده ٤٧ سنة !!
ومع ذلك لم تتحسر على الزواج!!

•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

لكنها اشتغلت بالعلم والعبادة وكانت معلمة ومثقفة و مفتيه لكبار الصحابة
لن تتوقف الحياة على الإنجاب ولا على الزواج ولا على البيت ولا على الضرة ولا على المال ولا على موت الوالدين
أو فقد الأبناء !!

•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

ما أخذ الله شئ إلا وعوض خيراً منه

والدنيا دار ابتلاء لم تكمل لأحد أبداً،،

إملأِ قلبك بالإيمان والرضا وحسن الظن بالله ووقتك بطلب العلم والعمل في كل ما ينفع نفسك ومجتمعك .

اجعلِ الصبر زادك .. والقرآن صاحبك
( ما أنزلنا عليك القرآن لتشقى)

يقول عمر بن الخطاب "لولا ثلاث ما أحببت البقاء في الدنيا: ظمأ الهواجر( الصيام) والسجود في الليل ومجالسة أقوام ينتقون أطايب الكلام كما يُنتقى أطايب الثمر "

•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

ليتنا نفهم الحياة كما فهمها الرعيل الأول
فنفوز كما فازوا بخيري الدنيا والآخرة

Post a Comment

0 Comments