Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለቀቅ አድርጓት ሱመያን Gtm

 
”ለቀቅ አድርጓት ሱመያን”
አትመስሉም ማንነቷን
አልተከተላችም መንገዷን
ስም ፈልጉ ለጅህልናችሁ
የሚገጥም ከተግባራችሁ
ስሟን ብቻ ወዳችሁ
ተግባሯን የናቃችሁ
እስኪ እርጉ በቤታችሁ
እውነት ሱመያን ከወደዳችሁ
ሸሂድ ተባባሉ እርስ በራሳችሁ
ያለ እውቀት እያጨበጨባችሁ
በጅህልና ሞት ማለቅ ሆነ ውጤታችሁ
ሱመያ ነች አሏት
ከወንድ ጋር ስትጋፍ ያየዋት
ሱመያ ነች አሏት
ሱሬ ተወጥራ ያየዋት
ሱመያ ነች አሏት
ፀጎራ የታየ ተቀንድባ ያየዋት
ሱመያ ነች አሏት
ድምፇ ሲጮው የሰማዋት
ለቀቅ ሱመያን አታውቃቹም
አትመስላቹም
ውስጥ ያነዳል ድርጊታችሁ
እየሰማ እንዳልሰማ መሆናችሁ
ሱመያ ነሽ እያሉ ያታልሉሻል
በላይክ ይደግፉሻል
ከቤትሽ አውጥተው ይጠሮሻል
ሂጃብ ሲወድቅብሽ ፎቶ አንስተው
ሱመያ ይሉሻል
በቤተሽ ስትቀመጪ ሙናፊቅ ይሉሻል
ሱመያን ስትከተይ ሌላ ስም ይሰጦሻል
ይበሉሽ አትስሚያቸው
ከቅጥፈት አያልፍም አንደበታቸው
እውነተኛ ውሸተኛ
ውሸተኛ እውነተኛ
ይሆናል ብለውናል የአላህ መልክተኛ
{صل الله عليه وسلم}
ስለዚህ አይድነቅሽ
ሸሂድነተን አይወክልምና ተግባራቸው አይሸልግልሽ

Post a Comment

0 Comments