Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢራን በሃገራችንም የሺዐ እምነቷን ለማስፋፋት ደፋ ቀና እያለች ነው

ኢራን በሃገራችንም የሺዐ እምነቷን ለማስፋፋት ደፋ ቀና እያለች ነው። ባለፈው ረመዷን የቁርአን ሒፍዝ ውድድር ብለው በኢራን ኤምባሲ ባዘጋጁት ዝግጅት ወጣቶችን እየመለመሉ ለራሳቸው ግብዐት እየተጠቀሙ ይገኛል። በተጨማሪም አሹራ በደረሰ ጊዜ በጋዜጣዎች የአሹራ እና ከርበላን ገድል እናውሳ በማለት ጦማሪዎችን አሰማርተው አንድ አምድ መግዛት ህዝቡ ዘንድ የሺዐን አስተሳሰብ እየረጩ ይገኛል። ኢራን ሺዐን ለማሰራጨት ጠብ እርግፍ የጀመረችው ዛሬ ሳይሆን ከድሮም ጀምሮ በአዲስ አበባ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ ወደ ዘነበወርቅ በሚወስደው መንገድየሚገኘው በቀድሞ ስሙ «አሕሉል በይት» ከዚያም «ነስር» የሚባል ትምሕርት ቤት በመስራት በምግባረ ሰናይ ድርጅት ስም በልጆች ላይ የሺዐን እምነት ሲያሰራጩ ቆይተዋል ።
በሐረር ከተማ መስጂድ እንደሰሩ ሆኖም ለጊዜው ሰጋጅ እንደሌለበትም ሰምተናል። በድሬዳዋ ከተማም የአሹራ ቀንን በማስመልከት በሐበሻ ሺዐዎች አማካኝነት ድግስ አዘጋጅተው ሰውን እየጠሩ በመማረክ ላይ እንደሚገኙ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉኝ።
ከሁሉም በላይ ግን በኢራን ኤምባሲ በኩል እየተሰራጨ የሚገኘው በቁርአን ውድድር እና በበጎ እርዳታ መሰል ጣፋጭ መርዝ ለሕዝባችን አሳሳቢና ስለዚህ ጉዳይ ብዙ መባል ብዙ መፃፍ ብዙ መተንተን ይገባዋል ባይ ነኝ።
አንዳንድ ሰው ሐሰን ታጁ የተባለው ሰውየ የፃፈውን «ሺዐ» የተሰኘ መፅሃፍ ልክ እንደ ጀብድ ሲያገነውና ሲያሞግሰው ስመለከት እሸማቀቃለሁ። ሐሰንን በደንብ አውቀዋለሁ። ካሻው መጥቶ “አይደለም” ይበለኝ እንጂ የሱ ሪሞት ያለው ዩሱፍ አል ቀረዷዊ ጋር ነው። ዩሱፍ አልቀረዷዊ ሲተነፍስ አብሮ ይተነፍሳል፤ ሲያነጥስ አብሮ ያነጥሳል። ሲያለቅስ ያለቅሳል ሲስቅም ይስቃል።
ምን መሰላቹ ዩሱፍ አልቀረዷዊ አላህ ይምራውና ከጥንት ጀምሮ ህዝበ ሙስሊሙን ግራ ሲያጋባ የኖረ ሰው ነው። ይሄን የምላቹ እንዲው ከተራ ነገር ተነስቼ አይደለም። ሰውየው ዲናዊ ብይን (ፈታዋ) ከመስጠት በበለጠ ፓለቲካዊ ብይን በመስጠት የፓለቲከኛ አካሄድን እንደሚመርጥ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
እስከከ የሊቢያውን ቃዛፊን እንይ
ቃዛፊ እና ቀረዷዊ ጉድ ያስባለ ወዳጅነት ነበራቸው ሆኖም የዐረብ ፀደይ (የዐረብ ሃገራት አመፅ) በመጣ በማግስቱ ቀረዷዊ በቲቪ ቀርቦ “ቃዛፊን ግደሉት! የገደለው ሰው አያስብ! ደሙ በኔ ትከሻ ላይ ነው!” ብሎ ፈታዋ ሰጠ። ለምን?
ቃዛፊ ጨቋኝ ስለነበር? ለሱ ቢሆንማ ቀድሞም ባልተወዳጀው! ቃዛፊ ስልጣን ላይ የቆየው የአንድ አዛውንትን እድሜ ያክል ነው። በዘመነ ስልጣኑ ጨቋኝና የማያፈናፍን እንደነበር ዓለም እያወራ ቀረዷዊ ግን ከጎኑ ነበር።
የሶሪያው በሻር አልአሳድ ጋርም ብንሄድ ተመሳሳይ ኬዝ ያጋጥመናል። በሻር የዓለዊያት አንጃ የሆነ የሺዐ ቅርንጫፍ እምነት ተከታይ ነው። ቀረዷዊ ግን ይህን ሰውየ እንደ ተራራ አግዝፎ አሞግሶታል። ሃገሩን ለመጎብኘት ሲሄድ በሻር እና የሃገሪቱ ሙፍቲ ተቀብለውት በቲቪ ቃላት እስከሚያጥረው ሲቆልላቸው ታይቷል።
ከዐረብ ፀደይ በህዋላስ? ከዳው!
አሁንም በቲቪ ቀርቦ “ግደሉት!” አለ። ልክ እንደ ሜክሲኮ ሃሺሽ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ ማፊያዎች ይጠቀምባቸውና ግደሏቸው ይላል።
ሌሎቹንም መዘርዘር እንችል ነበር ከርእሳችን ስለወጣን መሪውን አዙረን እንመለስ።
ቀረዷዊ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የሊባኖሱን ሒዝቡላህ ይደግፍ ነበር። ሙጃሒዶች እያለ ለዐለም ሕዝብ ያስተዋወቃቸው እራሱ ነበር። ሒዝቡላህ የሺዐ ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ከፍልስጢኑ ሐማስ ጋር በመሆን ወደ አይሁዶች መሬት አንድ ቀጫጫ በትር የመሰለች ሚሳዒል ይተኩሱና እነሱ ወደ አውሮፓ ያመልጣሉ። ይህን አጋጣሚ የሚጠብቁት አውሬዎቹ አይሁዶች ደግሞ በአፀፋው 1000 ሙስሊሞችን ከገደሉ በህዋላ የሒዝቡ ሸይጧን መሪዎችና የሐማስ መሪዎች በአልጀዚራ ቀርበው “ሞት ለአሜሪካ! ሞት ለኢስራዒል!” ይላሉ። ብቻ ቀረዷዊ ከሒዝቡሸይጣን ጋር ቁርኝት አይሉት ጋብቻ ነበረው። እነሱንም የፈረደበት የዐረብ ፀደይ ሲመጣ “እንተዋወቃለን እንዴ?” አላቸው። ለምን? በሻር አልአሳድን ሒዝቡሸይጣኖች ስለሚረዱ። ከዚያም ቀረዷዊ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ስሺዐ መናገር ጀመረ። ፃፈ ተሳደበ ኮነነ !!!
እንደውም ምን አለ መሰላቹ?
“ትናንት የሱዑዲያ ዑለማዎች ስለሒዝቡላህ የተናገሩት ልክ ነበር። ዛሬ መሳሳቴ ገባኝ።” አለ።
ሐሰንም የኢትዮጵያው ቀረዷዊ እንጂ ሌላ አይደለም። ከአስተማሪው ዶ/ር እድሪስ የወረሰውን የኢኽዋን ፊክራ በቀረዷዊ ንድፈ ሃሳብ እንጂ አያራምድም። ትናንት “ሺዐ ሱኒ እያላቹ አትከፋፍሉን!” እያለ የለፈፈው ሐሰን ልክ ቀረዷዊ በባሻር አልአሳድ ምክንያት ሒዝቡላህ እና ሺዐ ላይ ሲዘምት የኛውም ሐሰን ታጁ “ሺዐ” የሚል መፅሃፍ አሳተመ። ቀረዷዊ “ዘፈን ሐላል ነው” የሚል መፅሃፍ ያሳተመ ጊዜ ሐሰንም ሳይጨምር ሳይቀንስ “ዘፈን ሐላል ነው” ብሎ እንደተረጎመው ማለት ነው።
አላሁልሙስተዐን
ለማንኛውም ከኢራን ላይ አይናችንን አንንቀል!
ሃገራችን ላይ በሐበሻዎች አማኻኝነት የተለያዩ መፃህፍቶችንም እያሳተሙ እንደሆነ እቅዳቸውም እንዴት እንደሆነ የሚያትቱበትን ቪዲዮ ከዚህ ቀደም ተርጉሜ ለጥፌ ነበር።
አላህ ካለ በአዲስ መልክ ይቀርባል ኢንሻአላህ
ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ሽርክ ሽርክ ነውና ኩፍር ኩፍር ነውና ከኢራን ይምጣ ከቱርክ አንቀበልም አይደል እንዴ?
ልከረ እንደኢራኖቹ ቱርኮችም ሃገራችን ላይ ሱጁድ የሚደረግለትን ከአላህ ውጪ የሚመለከውን የነጃሺ ዶሪህ ‘መስጂድ’ በብዙ ሚሊየን ብሮች በአዲስ መልክ ለማሳደስ ከነጃሳው መጅሊስ ጋር መፈራረማቸውን እንደውም ስራ መጀመራቸውን ሰማን!
ኢናሊላሂወኢናኢለይራጂዑን
ሰዎች ሆይ እንንቃ!