Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በተውሂድ የምትተዳደረውን አገር ለመንካት የሚሞክሩትን እስቲ ታዘቧቸው በኩፍር ስለተጨማለቁት ሺዐዎች ምን ሲሉ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?

በተውሂድ የምትተዳደረውን አገር ለመንካት የሚሞክሩትን እስቲ ታዘቧቸው በኩፍር ስለተጨማለቁት ሺዐዎች ምን ሲሉ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ሳውዲን ለመወረፍ ብዙ ሲወጡ ሲወርዱ ይታያል፣ እርማትም ሊሰጣት ይገባል ብለው አሳቢ ለመምሰል ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን አንድም ቀን በአላህ ላይ ስለሚያጋሩት ከዚህ በታች በአላህ ፍቃድ የምዘረዝራቸውን ኩፍር እና ጥመት ተግባራትና አባባሎች የሚናገሩትን ሺዐዎች (ኢራኖች)፣ ከሺዐዎች ጋር አንድ ነን የሚሉትን ኢኽዋኖች ምንም ሲሉ ተሰምተው አይታወቁም እነዚሁ ሳውዲን የሚተቹ ልባቸውን የታመሙ ዋልጊዎች፡፡ - ያ ሁሴን፣ ያፋጢማ፣ ያ አልይ፣ ያ ዘይነብ እያሉ ከአላህ ውጭ የሚጠሩትን ሺወዎች፣ - ‹‹ቁርዐን ተቀንሷል፤ ሱረቱል ዊላያ የሚባል ሱራ አለ ያላሉ›› የሚሉትን ሺዐዎች፣ - ሀዲስንም ቡኻሪ፤ ሙስሊም፤ አህመድ የመሳሰሉትን የማይቀበሉትን ሺዐዎች፣ - ‹‹አንተ ሁሴን ከአላህ በላይ ትልቅ ነህ›› ብለው ኩፍር ነሺዳ የሚያነሽዱትን ሺዐዎች፣ - የሺዐ መሪ ከነበሩት አንዱ ሃያቶላ ኹመይኒ እንዲህ ይላል ‹‹አነዚህ ሙሽሪኮች መዲናን መውረርና እነዛን ሁለት ጣዖቶች (አቡበክር እና ኡመርን) ማስወገድ ፈለጉ›› - ከሺዐዎች መሪ አንዱም ስለ ምዕመናን እናት አኢሻ እንዲህ አለ ‹‹አኢሻ በእርግጥ ካሃዲ(ካፊር) ናት›› የአላህ እና የረጋሚዎች እርግማን ሁሉ በርሱ ላይ ይሁን፡፡ - ከሺዐዎች አንዱም ተጠየቀ ‹‹ሱንዩ አለም ሙስሊም ይባላል ወይ?›› እሱም ‹‹አይባሉም፤ ምክንያቱም ሙስሊም የሆነ ሰው አቡበክርን እና ኡመርን አይወድም›› በማለት መለሰ፡፡ - የኡመር ኢብነል ኸጣብን ገዳይ አቡ አላ አልመጁሲን የዲን ጀግና ነው ብለው አላህን ከዚህ የተረገመ ሰው ጋር እንዲቀሰቅሳቸው ዱዐ ያደርጋሉ እነዚሁ ሺዐዎች፣ - ኡመር የተገደለበትን ቀን የኢድ ቀን አድርገው ይዘዋል እነዚሁ ሺዐዎች፤ - አቡበክርና ኡመር ከሸይጧን በታች ጀሀነም ውስጥ እየተቀጡ ነው ይላሉ እነዚሁ ሺዐዎች፤ - ሌላው ሀሰን ነስረላህ በመባል የሚታወቀው የሂዝቦላህ መሪ ታላቁን ሰሃባ አቡሱፍያንን ሲያከፍር በቴሌቭዥን ታይቷል፤ - በአደባባይ ቀብር የሚመለክባት አገር ኢራንን ዝም ብለው፣ - ኢብነል ቀይም እንደገለፃቸው ‹‹አንድም የውጭ ጠላት እስላምን ለማጥቃት አይመጣም ሺዐዎች እየመሩ ቢያመጡት እንጂ››፤ የሺዐዎች ጉድ ተነግሮ አያልቅም፡፡ - ሺዐዎች ሁጃጆች ላይ የፈፀሙትን በደል በታሪክ ማወቅ የፈለገ ሰው የሚከተለውን ሊንክ ይመልከት https://www.youtube.com/watch?v=gDICmOtPBMA ይሄ በትንሹ ስለ ሺዐዎች ነው፡፡ - ‹‹እዚህ ጋር አረጋግጣለሁ ከዩሁዳዎች ጋር ያለን ጦርነት የሀይማኖት አይደለም›› (አል-ሙጅተመዓ መፅሄት ዙል ቃኢዳህ 30 1415)፡፡ የሚለውን የኢኸዋኑን መስራች ሀሰን አል በና ዝም ሲሉ ይታያሉ፡፡ አስገራሚው የሁዳዎች ጋር የእምነት የአቂዳ ጦርነት እና ጠላትነት ከሌለን ምን ይሆን ያለን ሱብሃነላህ፡፡ እነዚሁ የሁዳዎች ናቸው ነብየላህ ያእቁብንና የህያን የገደሉት፣ ነብየላህ ኢሳን ለመግደል ሙከራ ያደረጉት፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመርዝ ሊገድሉ የሞከሩት እና የመሳሰለውን፡፡ - መውሊድ ላይ ሆነን እንዲህ እንል ነበር‹‹ይህ ሀቢብ (ነብያችንን) ከተወዳጆቹ ጋር መጣ፤ የሁላችንንም ከዚህ በፊት የሰራነውን ወንጀል ምሯል››፡፡ የሚለውን የኢህዋን መስራች ሀሰን አል-በና ዝም ብለው ሳውዲ በተውሂድ በምትዳደረዋ አገር እና አስተዳደር ላይ ምላሳቸውን ያስረዝማሉ፡፡ አላህ ግን ‹‹ከአላህ ውጭ ማን ነው ወንጀልን የሚምር?›› ይላል፡፡ ኡማውን እንደሚከተለው እያለ በጅምላ የሚያከፍረውን ተክፊሪ ሰይድ ቁጡብ ዝም ብለው ሳውዲና በተውሂድ ያሉ አስተዳደሮቿን ይወርፋሉ - ‹‹በእርግጥ በምድር ላይ ሸሪዐና ፊቅህ መመሪያው የሆነ አገርም ሆነ ማህበረሰብ የለም›› (ዚላል አል-ቁርዐን 4/2122) - ‹‹በእርግጥ ይህ እየኖርንበት ያለው የጃሂልያ ማህበረሰብ የሙስሊም ማህበረሰብ አይደለም›› (ዚላል አል-ቁርዐን 4/2009) - ‹‹ዛሬ ጃሂልያ ላይ ነን፡፡ የአላህ መልክተኛ ከመላካቸው በፊት ወደ ነበረው ፤ እንዲያውም ከዚህ በባሰ ዙሪያችን በጠቅላላ ጃሂልያ ነው›› (መዓሊም ፊጠሪቅ ገፅ 21. 17 እትም፣ 1991) ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከላይ ላሉት የሰይድ ቁጡብ ተክፊር የዘቀጡ አባባሎች መልስ የሚሆኑ ትምህርታቸው ላይ እንዲህ ብለው ነበር ‹‹በኔ መላክ ትልቁ ጃሂልያ ተወግዶላችኋል››፣ ‹‹ከኔ ኡመት ሀቅ ላይ እና የበላይ የሆነች ቡድን አትጠፋም፤ እነሱን የሚቃወማቸውም አይጎዳቸውም……›› የሚሉት ሀዲሶች ኡመተል ኢስላም ሙሉ በሙሉ ጨርሶ ከሳቸው መላክ በኋላ ሊጠም እና ጃሂልያ ውስጥ ሊገባ እንደማይችል ይጠቁማል፤ ከጀማዓተ አተክፊር የመጣ አመለካከት እንጂ እስልምና ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ፍልስፍና ነው፡፡ እዚህ ጋር ሳውዲን በተመለከተ እነዚህ ልባቸውን የታመሙ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ እና ትችት አለ እሱም ‹‹ሳውዲ ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት አላት›› መልሱ ዛሬ ማን ነው እስቲ ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት የሌለው? - የቱርክም መሪ ኦርዶጋን አላህ ይጠብቀው ከኦባማ አስተዳደር ጋር ግንኙነት አለው፡፡ - ኢህዋኒው ሙሐመድ ሙርሲም ስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን እንዲያውም ከአሜሪካ መንግስት 1.5 ቢሊዬን ዶላር ሁሉ እርዳታ አግኝቷል፡፡ - አሁንም የሙሐመድ ሙርሲ አስተዳደር ስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ ከዩሁዳዎች ጋር እራሱ ሉካን ቡድኑን ልኮ ስምምነቶችን ፈፅሟል፡፡ ስልጣን ከመያዙ በፊት ግን ከዩሁዳዎች ጋር ግንኙነት አያስፈልግም እና የመሳሰለውን ሲል ነበር፡፡ ማረጋገጥ የፈለገ የሚከተለውን ሊንክ ማየት ይችላል https://www.youtube.com/watch?v=pZbs3nk57rk - አሜሪካ እና ኢራን ላይ ላዩን ጠላት ይመስላሉ ግን አይን ላለው አሜሪካ ኢራቅን ወራ ከዛ ስልጣኑን ከሺዐ አስረክባ ነው የወጣችው፡፡ መቼም ይሄ ያላቸውን ግንኙነት ምን እንደሚመስል ማወቅ ለፈለገ ታላቅ ጠቋሚ ነው፡፡ አሜሪካ የሱንይ አገሮችን ስትደበድብ ስትዘርፍ አንድም ቀን ኢራን ላይ አድርጋው አታውቅም፡፡ - ኢራንም ከኢስራኢል ጋር ላይ ላዩን ጠላት ቢመስሉም ዋና ጠላት አድርጋ ይዛ ቀን ከለሊት የምትሰራው ለሱናው አለም መጥፋት ነው፡፡ ይህን ብቻ ካልኩ እስቲ እነዚህ ኢትዬጵያ ላይ ተቀምጠውም ይሁን አለም ላይ ሳውዲን ለመወረፍ የሚሞክሩ ብሎም ሳውዲና አስተዳደሯ ስህታቸው ሊነገር ይገባዋል የሚሉት አካላት ከላይ የተዘረዘረው ጥመት ሁሉ ያለባቸው ሺዐዎችና ደጋፊዎቻቸው ኢኽዋኖችን ምን ሲሉ ብሎም ምናቸውን ሲያርሙ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ሁሉን አሸናፊ አላህ ሆይ! ሳውዲንም ሆነ ሌሎች ሙስሊም አገራትን ከነመሪዎቻቸው አንተን የሚያስወድድ ስራ እንዲሰሩ ምራቸው፡፡ ሺዐዎችንና፣ ጠበቃዎቻቸውን አንተው ያዝልን፡፡