Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሰዎች ሁሉ ምርጥ የጥበበኞች ሁሉ ጠበብት የመካሪዎች ሁሉ አለቃ የቅኖች ሁሉ መሪ የለስላሳዎች ሁሉ ቁንጮ የጣፋጮች ሁሉ በላጭ የአስተማሪዎች ሁሉ ሹም ታውቃቸዋለህን?

 
14/07/2015
የሰዎች ሁሉ ምርጥ
የጥበበኞች ሁሉ ጠበብት
የመካሪዎች ሁሉ አለቃ
የቅኖች ሁሉ መሪ
የለስላሳዎች ሁሉ ቁንጮ
የጣፋጮች ሁሉ በላጭ
የአስተማሪዎች ሁሉ ሹም

ታውቃቸዋለህን?
አዎን! ረሱሉል ሁዳ صلى الله عليه وسلم እኛ ፍቅር ሰው ! ሽርክን ገርስሰው ተውሒድን ሲያነግሱ ተለምዶን አስቀርተው ሱናቸውን ሲያሰርፁ አላዋቂውና ስሜቱን የሚከተል ማሕበረሰብ “በርቱልን!” አላቸው እንዴ?
በል እንደውም “ታማኙና ተመስጋኙ” እያለ እንዳላሞገሳቸው “እብድና ውሸታም” አላቸው!
አንባቢ ሆይ! ድፍረት ቢሆንብኝም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?
እኛ ምርጥ ነቢይ صلى الله عليه وسلم መልካምነታቸውን ጠንቅቆ ልክ እንደ ልጆቹ የሚያቃቸው ማህበረሰብ እንደዛ ለጆሮ የሚዘገንን ውንጀላ የወነጀላቸው ፣ ቅጥፈት የቀጠፈባቸው፣ እንደውም ሊገድላቸው የሞከረው .... ረሱል صلى الله عليه وسلم ሒክማ ስላልነበራቸው ነውን?
ሲጣሩ ደረቅና ሻካራ ስለነበሩ ነውን?
መልስህ ‘አዎ’ እንደማይሆን ከማወቄም ጋር ለአንተ የተውሒድ ዳዒያህ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ..
የሱናውን መንገድ እስካለቀቅክ ድረስ አይደለም የሃገርህ ዓለም ላይ ያለ ሕዝብ ተሰብስቦ ሊጎዳህ ቢመጣ የተውሒድና የሱናን ዳዕዋ “አይ! ይቅርብኝ” ልትል ነውን? እንኳን አንተን ከጥበበኞች ሁሉ በላጩ ጥበበኛን የአስተማሪዎች ሁሉ አስተማሪ የሆኑት ረሱል صلى الله عليه وسلم እንኳን ከስድብ ፣ ከዛቻ፣ ከመግደል ሙከራ አልተረፉም!
ታዲያ አንተ ማን ሆንክና አስር ሰዎች መልካቸውን እየቀያየሩ ሰደቡኝ፣ አስፈራሩኝ፣ መቱኝ፣ ደበደቡኝ ብለህ ከተውሒድና ሱና ዳዕዋ ወደህዋላ የምትሸሽ?
ፅናት ይኑርህ!
አላህ በተውሒድና በሱና ላይ ያፅናን

Post a Comment

0 Comments