Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዒድ ሰላት አሰጋገድን ስንቶቻችን እናውቃለን ?

1. ለዒድ ሰላት ምንም አይነት ነዋፊል (ሱና) ሰላት የለውም
ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደትናገሩት ‘‘የአላህ መልዕክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን)
በዒደል ፊጥር ቀን (ወደ መስገጃው) ቦታ እንደወጡ ሁለት ረካዕ (የዒድ ሰላትን) አሰገዱ’’ (ቡኻሪና
ሙስሊም) በአቡ ሰዓድ ረዲየላሁ ዐንሁ ደግሞ:- ‘‘በዒድ አል አድሃም (አረፋም) ጭምር..’’ ተብሎ ተዘግቧል ። (ቡኻሪ)
ኢብኑ ሃጀር ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ ከዒድ ሰላት በፊት ትርፍ ሰላት ቢኖር ኖሮ በተዘገበልን ነበር ። (ፈት ሁል ባሪ)
2. ለዒድ ሰላት አዛንም ሆነ ኢቃም የለውም ጃቢር ቢን ሳሙራህ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተናገረው:-
‘‘ከአላህ መልዕክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ጋር ከአንዴም ሁለቴ የዒድ ሰላቶችን
ሰግጃለው ነገር ግን አዛንም ሆነ ኢቃም አልተደረገም’’ (ሙስሊም አቡዳውድ)
3. ኹጥባ
ኢማም አሕመድ እንደዘገቡት ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከረሱል (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) የዒድ ሰላትን ሲሰግድ ሁሌም ከሰላቱ በኋላ ነበር ኹጥባ የሚያደርጉት
4. ኒያ
ለዒድ ሰላትም ሆነ ለሌሎች ሰላቶች በከንፈርና በምላስ የሚባል ኒያ የለም ነገር ግን በልብ ማሰብ
ነው ያለው ።
                                       የሰሰላቱ አሰጋገድ
5. ተክቢራዎች
የመጀመሪያው ረከዐ ላይ ተክቢረተል ኢሕራምን ጨምሮ (የሰላት መጀመሪያን) ለሩኩዕ ሲወረድና
ሲመለሱን ሳያጠቃልል ሰባት ተክቢራዎች (አላሁ አክበር) አሉት ። የሁለተኛውና የመጨረሻው ተክቢራ ደሞ አሁንም ተክቢረተል ኢሕራምን ጨምሮ ለሩኩዕ ሲወረድና ሲመለሱን አምስት ተክቢራዎች አሉት ። 

እመት አዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንደተናገረችው ‘‘የዒድ አልፊጥርና አድሃ (የሰላት) ተክቢራዎች የሩኩዕ ተክቢራዎችን ሳያጠቃልል የመጀመሪያው ሰባት ሲሆን ሁለተኛው ላይ ደሞ አምስት ነው ‘’ አቡ ዳውድ ኢብኑ ማጃህ
6. ፋቲሃና ሌላው የሚቀራው ከተክቢራው በኋላ ነው
አብደላህ ቢን አምር ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተናገረው ‘‘በሁለቱም ረከዐ ቁርዓን መቅራት የሚከተለው
ከተክቢራዎቹ ቀጥሎ ነው ’’ አቡ ዳውድ በይሃቂ
7. አንድ ሰው ሰላቱ ከተጀመረ በኋላ ተክቢራ አምልጦት ቢደርስ ስ ?
በደረሰበት ተክቢራውን ከኢማሙ ተከትሎ ይበል ፤ ላመለጠው ተክቢራ ማስተካከያ ማለት አይጠበቅበትም ምክንያቱም ሱና እንጂ ዋጂብ አይደለምና ።
8. ለያንዳንዱ ተክቢራ እጅን ማንሳት
በብዙ ዑለማዎች (ኢማም ማሊክ፣ኢማም ሻፊዒይ፣ኢማም ኢብኑ ሙባረክ፣ኢማም አሕመድ ሌሎችም) ስምምነት ለየተክቢራዎቹ እጅን ማንሳት አለበት ብለው ያስቀመጡ ሲሆን ኢማም ናስሩዲን አል አልባኒ ረሂመሁላህ ግን ዑለማዎቹ የተንጠለጠሉበት ሃዲስ ማለትን (ከኢብኑ ዑመር የተዘገበው) ደካማ መሆኑን ተናግረው ቢነሳም ችግር እንደሌለው አትተዋል።
9. ለተክቢራዎቹ ድምፅን ከፍ ማድረግ
ተክቢራ ስናደርግ ድምፅን ከፍ ማድረግ ምንም አይነት ማስረጃ ያልመጣለት ሲሆን ፤ አንድ ሰው
የትኛውንም ዚክር ሲል ድምፁን ዝቅ ማድረግና አጠገቡ የሚሰግዱትን ሰጋጆች መረበሽ የለበትም ።
10. በተክቢራዎች መካከል ምን መባል አለበት ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተናገረው:-
አንድ ሰው መጥቶ ለዒድ ሰላት ላይ ምን ልበል ብሎ ሲጠይቀው ኢብኑ መስዑድም የሚከተለውን ምላሽ ሰጠው
‘‘ተክቢራ (አላሁ አክበር) በል ከዚያም አላህን አምስግን አወድስ ፣ ከዚያም ሰላዋት አውርድ
(አላሁመሰሊ አላ ሙሃመዲ ) ከዚያም ዱዐ አድርግ ከዚያም (በድጋሚ) ተክቢራ በል ከዚያም አላህን
አምስግን አወድስ ፣ ከዚያም ሰላዋት አውርድ (አላሁመሰሊ አላ ሙሃመዲ ) ከዚያም ዱዐ አድርግ
ከዚያም….’’ጠበራኒ ዘግበውታል በአል ኢርዋ እና በሌሎቹም ሰሂህ ተብሏል
11. ከተክቢራ በኋላ
ከተክቢራ በኋላ ኢማሙ ፈቲሐን ማንበብና ሌሎች ሱራዎችን ( ሱረቱል አዕላ ፣ ሱረቱል ጋሺያህን ቢቀሩ ይወደዳል) ይቀራል ። ሱመራህ ረዲየላሁዐንሁ እንደዘገቡት ‘‘የአላህ መልዕክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) በሁለቱ ዒዶች ሰቢህ ኢስሚ ረቢከል አዕላ (ሱረቱል አዕላ) እና ሃል አታከ ሃዲሱል ጋሺያህ (ጋሺያዕህ)ን ይቀሩ ነበር ’’ አሕመድ ሰሂህ በ አል ኢርዋ ከኢማሙ የሚከተለው ሱረቱል ፋቲሐን ድምፁን ሳያሰማ ይቀራል ሌላውን ሱራ ኢማሙ ሲቀራ ብቻ ያዳምታል እንጂ አብሮ አይቀራም ።
12. ሰላት አጠናቀን ወደ ቤት እንደተመለስን 

ከዒድ ሰላት በኋላ ያለ የሱና ሰላት ሰዒደልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተናገሩት:- ‘‘
የአላህ መልዕክተኛ ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁን ከዒድ ሰላት በፊት ምንም ትርፍ ሰላትን
አይሰግዱም ነበር ነገር ግን ሰላት አጠናቀው ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት ረካን ይሰግዱ ነበር’’ አሕመድ
ኢብኑ ማጃህ
13. ኢማሙ ሱናን የማይከተል ቢሆንስ ?

አንዳንድ ቦታ ላይ አንዳንድ የመስጂድ ኢማሞች ከሱናው ወጣ ያለ አስተምሕሮን የሚከተሉ አሉ ፤
ሆኖም እኛ ሌላ ሱናን የሚከተል ወይም ለሱና የሚቀርብ ኢማም ሌሎች ቦታዎች ላይ የሚያሰግድ
ካገኘን ወደዛው መሄድ ይገባናል ካልገኘንም ኢማሙን መከተል ይገባናል ። ምክንያቱም ረሱል
ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁን:- ‘‘ኢማም መከተልን ይገባዋል ብለዋል በሌላም ሃዲስ ኢማም
ስሕተት ይሰራል የተሳሳተው ለራሱ ነው እናንተ ግንለሰገዳቹበት ምንዳን ታገኛላቹ ’

Post a Comment

0 Comments