Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ ጀሚሉረህማን አል አፍጋኒ አሰለፊ ረሒመኹሏህ 1358- 1412 ሒጂሪያ

July 18 at 8:01pm · 2015

እ .ኤ.አ በ1987 የሶቪየት ህብረት የአሁኗ ራሺያ እና የአፍጛኒስታን ሙጃሂዶች መካከል ለ9 አመታት የቆየ ጦርነት ተካሂዶ ነበር ። ጦርነቱ የተነሳው ድንበር አልፈው የገቡ የሶቭየት ሃይሎች ድንገት ወረራ በማካሄዳቸው ሲሆን በጦርነቱ ከ1·5 ሚሊዬን በላይ ንፁህ የአፍጛን ዜጎች ሞተዋል። 3 ሚሊዬን ያክሎቹ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ። በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችም እንዲሁ ስፍር ቁጥር የላቸውም ።
በጦርነቱ ሶቭየት ሃይሎች ላይ ጠንካራ ጥቃት ካደረሱ ሙጃሂዲን መካከል የኩናር ሙጃሂዶች ኢማም የነበሩት ታላቁ የተውሒድ ጠበቃ የሱና አስተማሪ ሸይኽ አልኢማም ጀሚሉረሕማን አልአፍጛኒ ነበሩ። አላህ ይዘንላቸው

ጀሚሉረሕማን አልአፍጛኒ ጠቅለል ባለ ቃል ዓሊም እና ተሰጥዖ ያላቸው ድንቅ መሪ ነበሩ። የሶቪየቶችን ወረራ ተከትሎ ጂሃድን የቀሰቀሱ ቀደምት ሙጃሂድ የነበሩ ሲሆን የሚኖሩባት አካባቢ የሆነችው የኩኑር ከተማን ከሽርክና ቢድዐ በማፅዳት አነስተኛ ኢስላማዊ ደውላ (ግዛት) አቋቁመውም ነበር ።
ጀሚሉረሕማን ያቋቋሙት ኢስላማዊ ግዛት በተውሒድና በሱና የጠነከረ፣ ወንጀል ያልተንሰራፋበት፣ በቀደምት ሰለፎች አካሄድ (መንሐጅ) የሚመራ የነበረ ሲሆን ወራሪ አክፍሮት ሃይላት ለሆኑት ሶቭየት ሃይሎች ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባቸው ነበር።
ሸኹ ረሒመሁላህ ፎቶውም ላይ እንደምትመለከቷቸው ለሱና ትልቅ ቦታ የሚሰጡና ሱናን የሚተገብሩ ሰው ነበሩ። በርሳቸው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሁሉ በሱና የተዋቡ ፣ ከቁማር፣ ወለድ የፀዱ ሱሪ የማይጎትቱ፣ ፂም የማይላጩ ሌሎችንም ክልክላቶች የማይዳፈሩ በተውሒዱል ሩቡቢያ፣ ዑሉሂያ፣ አስማወሲፋት የታነፁ በኪታቦች በመላዕክቶች በምፅዓት ቀን እና በቀደር እምነት ያመኑ፣ የሰለፎችን አካሄድ የሚያራምዱ ጠንካራ ሰለፊዮች ነበሩ ።
ሸኽ ጀሚል የኩኑርን ግዛት ከሶቭየት ሃይሎች ወረራ የታደጉ ሲሆን በዚች ትንሽ ግዛት የትክክለኛ ሸሪዐ ሕግን አቋቁመው በሱም ይመሩ፣ ያስተዳድሩ ነበር። ወታደሮቹም ሆኑ የግዛቱ ዜጎች ሁሉም ንቁና ቀልጣፋ አዛን ሲሰማ ሁሉም ከተኛበት ነቅቶ ወይንም ስራውን አቋርጦ ወደ መሳጂዶች የሚያመራ፣ ተውሒድን የሚማር፣ ሱናን የሚተገብር፣ ሐላል የሚመገብ ክልክላቶችን የማይዳፈር ምርጥ ህዝብ ነበር። በግዛቷ ት/ቤቶች፣ ክሊኒኮች ፣ ሆስፒታል የመሳሰሉትን ያቀፈና ዛሬ ላይ ኢኽዋን ተክፊሮች የሚጮኹለትን “ደውላ” ለማቋቋም በቅተው ነበር ።
በዛን ወቅት ሶቭየት ሃይሎች የእምነት አልባ ርዕዮት ዐለምን በአፍጛን ምድር ዘርተው ያላቸውን ነዳጅና ኦፒየም የተባለ ንጥረ ነገር ዘርፈው ለመውጣት ሲታገሉ ሸኽ ጀሚሉረሕማን ሕዝቡን ዐቂዳና ሱና እያስተማሩ ጅሃዱንም አንድ ላይ ያስኬዱ ነበር ። እንጂ የዛሬ “ታጋዮች’’ እንደሚሉት “ተውሒድ ተከድኖ ይብሰል” ፤ “ይደረስበታል” “አሁን ጠላት ፊት ለፊት ቆሟልና አንድነት ይቅደም” አላሉም። ብሎም ጊዜው ያሰጋልና ከሽርክና ከቢድዐ ባልተቤቶች ጋር “መውሊድ አይለያየንም” እንበል ብለው አልደሰኮሩም። በል እንዳውም ብረት የያዘ ወታደር በሰማይ እንደ አሞራ የሚበርና ፈንጅ የሚጥል ሰራዊተ አክፍሮት ሃይልን ጥቃት እየተጋፈጡ በዛ ጭንቅ ሰዐት ተውሒድን ይሰብኩ ዐቂደቱ ሰለፊያን ያስተምሩ ነበር።
ታዲያ በዚህ መሃል ነበር ተውሒዱ ተስፋፍቶ ከአላህ ውጪ የሚመለክ እየጠፋ በአፍጛን ምድር ከኩናር የሸሪዐ ግዛት ፈንጥቆ በወጣው የሱና ወጋገን ሲበራ፣ የቢድዐ ቡድንተኝነት ተገርስሶ የሰለፎች ፍንትው ያለ መንሐጅ ሲተካ ራስ ምታት የሆነባቸው ኢኽዋኖች ከዘመን መዝገብ ላይ የማይፋቅ ትልቅ ሴራና ደባን አቅደው የክፋትን መርዝ የረጩት ።
ጊዜው እ.ኤ.አ በ991 በሚያዚያ ወር ላይ ከጙሉቡዲን ሂክመቲያር ቡድን አባል የሆኑ የተወሰኑ ኢኽዋኖች ወደሸኹ ማረፊያ ቁርአን ሊማሩ መስለው ይመጣሉ ። የሸኹን ካምፕ የሚጠብቁ ሙጃሂዶች ምንም እንኳን ሊፈትሿቸው ቢሞክሩም ሸኽ ጀሚል እንዳይፈትሻቸው ያዛቸዋል ። ሸኹ ለዐረቦች ካለቸው ክብር በመነሳት ወደርሱ የሚመጡትን ዐረቦች እንዳይፈተሹ ይከለክሉ ነበር። [“ከጅምሩም ኢስላምን የረዱት ዐረቦች ናቸውና”] የሚል አቋም ስለነበራቸው ። እናም እነዚህ ኢኽዋኖች ሸኹ ጋር ሲገቡ ሸኹ በጥሩ መስተንግዶ አስተናገዷቸው ። ምግብና መጠጥም አቀረቡላቸው፣ ከአላህ ቃል (ቁርአን) አነበቡላቸው ፣ አስተማሯቸውም። ሰዎቹ ጨርሰው ለመሄድ ሲነሱ ነው ታዲያ አሰቃቂው ነገር የተከሰተው !። አንዱ ግብፃዊው ኢኽዋኒ ከኪሱ ውስጥ ሪቮልቨር የተባለውን ሽጉጥ መዞ በማውጣት ወደሸኹ ጭንቅላት አነጣጥሮ በማከታተል ሶስቴ ይተኩሳል ። የሸኹ ሩህም ወደሰማይ አረገች ። ረሒመሁላህ ረህመተን ዋሲዐ
ገዳዩም ወዲያው ራሱን ገድሎ ይሞታል ። አላህ የሚገባውን ይስጠው
የገዳዩ አጥፍቶ ጠፊ አንጃ የሆኑት ሂክመታይን የተባሉት ኢኽዋኖች የሸኹን ሞት አስከትለው ሱፊይ ቀብር አምላኪዎችን፣ ባታኒ የተባለውን የሶሻሊዝም ፓርቲ ጋር ተቀላቅለው ጥምር ሃይል በመፍጠር በግዛቷ የሚገኘውን የተውሒድ አርበኛ ሰለፊ እየመረጡ መጨፍጨፍ ተያያዙት ። ጀሚሉረሕማን ያቋቋመውን የሸሪዐ ግዛትም አጠፉት ።
እኚህ ናቸው ኢኽዋኖች! ለኢስላም እንታገላለን ብለው ኢስላምን ይታገላሉ ። በተውሒድ፣ በሱና እና በሰለፎች መንሐጅ የተሞላን ንፁህ ጭንቅላት በሶስት ጥይት ያለርሕራሄ ይገድላሉ ።
ሸኹ በዘመኑ ከካፊር ጋር እንጂ አልተዋጋም ፤ ካፊርን እንጂ አልገደለም፤ አንድም ጊዜ አፈሙዙን ወደካፊር እንጂ ወደሙስሊም አላዞረም ። በል እንዳውም ዐረብ የተባለን እንዳየፈተሽ ይከለክል ነበር ። ነገር ግን ተውሒድ ሲነግር የሚመለክ ቀብር ሲጠፋ አላህ በብቸኝነት ሲጠራ የሚያማቸው ኢኽዋኖች ሸይኹን ገደሉት! ።
ነገሩማ ..
((ﻭَﺍﻟْﻌَﺎﻗِﺒَﺔُ ﻟِﻠْﻤُﺘَّﻘِﻴﻦ))
[[ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡]] (ቀሶስ 83) ነው ።
ሸኹ በአላህ መንገድ ላይ ሳሉ ነው የተሰውት። በህይወት እያሉም የስራቸውን ውጤት አላህ አሳይቷቸዋል ። የአፍጛኒስታንን ከፊል ግዛት በተውሒድ በሱና በሰለፎች መንሐጅ አቁመዋል ።
ሸኹ በዘመኑ ባደረጓቸው የጂሃድ ጥሪዎች ብዙ ሰዎች ከብዙ ሃገር መልስ ሰጥተዋቸዋል ። ከተለያየ ዐረብ ሃገራት በአላህ መንገድ ላይ ለመታገል የሚሄደው የሰለፊ ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር ። ይህን ጂሃድ ከተሳተፉት ትላልቅ ስብዕናዎች መካከል ዛሬ ላይ በኢኽዋን ተክፊሮች አንደበት “የአይሁድ ቅጥረኛ” ፣ “የቤተ መንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚ” እና የመሳሰሉትን አፀያፊ ውንጀላዎች የሚያስተናግዱት የዘመናችን ታላቅ ዓሊም ዶክተር ሸኽ ረቢዕ ኢብኑ ሐዲ አልመድኸሊ ይገኙበታል ። ሸኽ መድኸሊ አፍጛኒስታን በሸኽ ጀሚል በሚመራው የሙጃሂዶች ክንፍ ውስጥ ለመዋጋት ከሶስት ጊዜ በላይ ሄደዋል ። ሸኹ ከዛም ጊዜ ጀምሮም ሆነ እስከአሁን ድረስ “አፍጛኒስታን ጂሃድ ሄጄ ተዋጋው’’ እያሉ ለፍፈው አያውቁም ። ሆኖም የቅርብ ሰዎች ይህን ታላቅ ስራቸውን ሸኹን ለመዘከር ሲያነሱ አያይዘው ሲያነሱት ይሰማል።
ሸኽ ጀሚል ቅን፣ ቸር፣ ጠንካራ የጦር መሪና የአላህ ሃቅ ሲጣስ የሚያስቆጣቸው ታላቅ ሰው ነበሩ ። እንኳን ጥይት በአናታቸው ውስጥ ሊገባ ቀርቶ እሾህ እንኳን የማይገባቸው ምርጥ የሱና ታጋይ ነበሩ ። ሸኹ ለተውሒድና ሱና ትልቅ ቦታ የሚሰጡ ሰው የነበሩ ሲሆን የአላህን ብቸኛ ተመላኪነት በማስፈናቸው አላህ ለሙዕሚኖች ቃል በገባው መሠረት እሱን በብቸኝነት በተውሒድ የማምለክን መሠረት በመመሥረታቸው በምድር ላይ ሸሪዐን ለማንገስ ሾሟቸዋል ።
አላህ እንዲህ ይላል :–
(( አላህ እነዚያን ከናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን፣ እነዚያን ከነሱ በፊት የነበሩትን (በስልጣን) እንደተካ፣ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፤ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ‪#‎ቃል‬ ሰጥቷቸዋል ‪#‎በኔ_ምንንም_የማያጋሩ_ሆነው_ይገዙኛል‬፤ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነሱ አመጠኞች ናቸው።)) [ኑር 54]
አላህ ለጀሚሉረሕማን ሙጃሂዲኖች ስልጣንን ሰጥቷቸውና አደላድሏቸው ሲያበቃ ‘አሁን ስልጣንን ይዘናልና ..” ብለው ለዲን ጀርባን አልሰጡም። በተውሒድ አርበኝነታቸው ገፉበት ፣ ሰላትን አቋቋሙ፣ ዘካን ደነገጉ፣ በጥሩ ነገር ማዘዝ በመጥፎ መከልከልን ተያያዙት ። ልክ አላህ እንደገለፃቸው ...
(( (አነርሱም) እነዚያ በምድር ላይ (በስልጣን) ብናስመቻችው፣ ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፣ ዘካንም የሚስጡ፣ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፣ ከመጥፎ ነገርም የሚከለክሉ ናቸው፤ የነገሮቹም ሁሉ መጨረሻ፣ ወደ አላህ ነው።)) [ሐጅ 41]
ታዲያ እነዚህን የአላህ ወታደሮች ነበር ሶቪየት ሳትሆን፣ እስራኤልም ሳትሆን፣ (በቀጥታ) አሜሪም ሳትሆን የኛው “ወንድሞቻችን” የምንላቸው ኢኽዋኖች አረመኔያዊ በሆነ መልኩ ጨፍጭፈው የገደሏቸው ።
የኢኽዋን እጅ ምንኛ ከሰረች !
(( ይህ ፅሁፍ ሸኹን ለማስታወስ በአጭሩ የተከተበ ነው እንጂ ከሸኹና ከጂሃዳቸው ጋር ተያይዞ ብዙ ማለት ይቻላል። አላህ ከፈቀደ ወደፊት እመለስበታለው። ባረከላሁ ፊኩም))
ስለሸኹ በደንብ ለማወቅ በታላቁ ዐሊም ሸኽ ሙቅቢል ረሒመሁላህ የተከተበውን
« ﻣﻘﺘﻞ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺟﻤﻴﻞ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻷﻓﻐﺎﻧﻲ ﺭﺣﻤﻪ الله»
የተሰኘውን ኪታብ ማንበብ ይችላሉ
አላህ ለጀሚሉረሕማን እና ለአፍጛን ሰለፊ ሙጃሂዶች ይዘንላቸው
ጀነቱል ፊርደውስን ይሸልማቸው

Post a Comment

0 Comments