Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሳይሰገድብህ ስገድ! እንዲሰገድብህም ስገድ!!

Abujunaid Salah Ahmed
📎 ሳይሰገድብህ ስገድ! እንዲሰገድብህም ስገድ!!
ሳይሰገድብህ ስገድ! አንድ ወንድማችን ይህንን አባባል «እንዲሰገድብህ ስገድ» ብሎት ነበር። አዎን! ምእመናን ይሰግዱብህ፤ የአላህንም እዝነት ይለምኑልህ ዘንድ ባንተ ላይ ከመሰገዱ በፊት ለጌታህ ስገድ።
ለሁሉም ሰላትን ጠበቅ!
የዱንያ ህይወት ምንም ብትረዝም አጭር ናት፤ ለአከኼራ ያለንን ዝግጅት ሁልጊዜ እንገምግም። አላህ መጨረሻችንን እንዲያሳምረው ሞትን በማስታወስ እንገሰፅ!!
ሞትን ለማስታወስ!
የቀብር ዚያራ ለወንዶች የተወደደ ነው። ቡረይዳህ ኢብኑል ሁሰይብ ባስተላለፉት ሀዲስ «እኔ ቀብር መዘየርን ከልክያችሁ ነበር፤ (ካሁን በኃላ) ቀብርን ጎብኙ።» ማለታቸውን ሙስሊም ዘግበዉታል።
በኢማሙ አህመድ ዘገባም «አኺራን ያስታውሳችኋል» ብለዋል። ኢብኑ ማጀህ ተመሳሳይ ዘገባ አላቸው አለባኒም ሰሂህ ብለውታል።
زيارة القبور مستحبة للرجال لقول النبي صلى الله عليه وسلم في حديث بريدة بن الحصيب : ( إني كنت نهيتكم عن زيارة القبور فزوروها ) رواه مسلم 977 ، وفي رواية (فإنها تذكركم الآخرة ) رواه أحمد 1240 وابن ماجة 1569 وصححه الألباني في صحيح ابن ماجة .
🔚 ዓላማችን ኢስላማዊ እውቀትን ማዳረስ ነው::