አሰላሙ ዐለይኩም ወንድም እህቶች ከዘመናዊ ጥንቆላ እንጠንቀቅ እናስጠንቅቅ!
የተለያዩ የወደፊት እጣፈንታችንን “እናውቅላችኋለን” የሚሉ የኢንተርኔት ጥንቆላዎች በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ እየመጡብን ነው፡፡ ለምሳሌም ከሰሞኑ “እጣ ፈንታህ ምንድን ነው?” (what is your destiny) የሚል ሊንክ ብዙ ሰው እየተጠቀመው ይገኛል፡፡ በስሩም ምን ያክል ልጅ እንደሚኖረን፣ ስራችን ምን እንደሚሆን፣ የጤና ሁኔታችን፣ የምናገባበትን ጊዜ፣ የምንይዘውን የመኪና አይነት እና በምን ያክል እድሜ እንደምንሞት በድፍረትና በቅጥፈት ይናገራል፡፡ ይሄ አይን ያወጣ ጥንቆላ ነው፡፡ ጥንቆላ በኢስላም ከክህደት ጋር የተቆራኘ አደገኛ ወንጀል ነው፡፡ የኛን እጣ ፈንታ ከአንድየው በስተቀር ማንም ሊያውቀው አይችልም፡፡ እናም
1. ጥንቆላና ሺርክ መልካቸውን ስለቀያየሩ፣ በእንግሊዝኛ ስለቀረቡ፣ በቴክኖሎጂ ስላሸበረቁ እውነታቸው አይቀየርም፡፡ ጥፋትነታቸው አይለወጥም፡፡ ስንዝር ታክል ወደ እውነትም አይቀርቡም፡፡ እናም ነገ ወይም ከነገ ወዲያም በሌላ መልክ ቢመጡ አድሮ አዲስ ልንሆን አይገባም፡፡ “ጭራቅ ሹካ እና ቢላዋ ስለተጠቀመ ሰለጠነ አይባልም!”
2. ይሄ የተውሒድ ግንዛቤያችን ምን ያክል የወረደ እንደሆነና በዚህ ረገድ ይበልጥ ልንማርና ልናስተምር እንደሚገባን የሚያስረዳ ነው ፡፡ ይሄ “ከነ አቡ ጀህል መሀል ያላችሁ ይመስል ተውሒድ ተውሒድ አትበሉ፡፡ ተውሒደድ የሌለው ሙስሊም የለም” እያሉ ተኝተው የሚያስተኙ የተውሒድ ደዕዋ እንቅፋቶችን ሴራ የሚያጋልጥ ነው፡፡
አላህ ለመልካሙ ሁሉ ያድለን፡፡