Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፡ አንድ ሙስሊም በአኼራ ህይወቱ ስኬታማ እንደሚሆን በምን ልቡን ሊያረጋጋ ይችላል? ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ)

ጥያቄ፡ አንድ ሙስሊም በአኼራ ህይወቱ ስኬታማ እንደሚሆን በምን ልቡን ሊያረጋጋ ይችላል?
ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ)
ምላሽ፡ የሚሰራውን ስራ እስካሳመረ ድረስ ይረጋጋል
መልካም ስራ ከሰራ ከጌታው መልካም ነገርን ይጠብቅ
አላህ እንዲህ ብሏል፤
(ባሪያዬ ከኔ እንደሚጠብቀው ያገኘኛል፤ ሲያስታወስኝ ከሱ ጋር ነኝ!)
ስራዉን ካሳመረ፤ መልካም ስራ በመስራት ላይ ከበረታና ስራዉን ካስተካከለ፤ ከአላህ መልካም መጠበቁ አይቀርም!
ስራው መጥፎ በሆነ ቁጥር ከአላህ የሚጠብቀው መጥፎ ምንዳን ይሆናል
ሙእሚን አላህን የመፍራት ግዴታ አለበት፤ አላህ እንደሚያየው በማሰብ ስራውን መቆጣጠር አለበት
አላህ የደነገጋቸውን ወሰኖች ሊጠነቀቅ ይገባል
አላህ ግዴታ ያደረገበትን መወጣት ያስፈልገዋል

የዚህም ምልክቱ፤
ለሰላት ትኩረት መስጠት እና መጠባበቅ ነው
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
(ሰላት፤ የአይኔ ማረፍያ ተደርጋለች)
በሌላም ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
«ሰላትን የተጠባበቀና ባግባቡ የሰገደ ሰው በትንሳኤ እለት፤ ብርሀን ማስረጃ እና ነጻ መወጫ ትሆነዋለች፤
ሰላትን በአግባቡ የማይሰግድ ሰው ግን ብርሀን፣ ማስረጃና ነጻ መውጭያ የለውም!»
በቂያማ እለት ከፊርዓውን ከሃማን ከእነ ኡበይ ኢብኑ ኸለፍ ጋር ይቀሰቀሳል፤
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
«አንድ ባርያ ከሰራቸው ስራዎች መጀመሪያ የሚመረመረው ሰላቱን ነው»
ሰላቱ ጥሩ ከሆነ፤ በርግጥም ድኗል ስኬታማም ነው!
ሰላቱ ጥሩ ካልሆነ ግን ከስሯል ተስፋውም ጨልሟል!
በሌላም ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
«ከዲናችሁ መጀመሪያ የምታጡት ታማኝነት (አማናን) ነው፤ መጨረሻ የምታጡት ደግሞ ሰላትን ነው»
ነብስህን ከተሳሰብክ፣ ለአላህም ብለህ ከታገልካት፤ ሰላቶችን ተጠባብቀህ ባግባቡ በጀመአ ከሰገድክ፤
ስራህን ካሳመርክ፤
በዚህ ጊዜ በአላህ ላይ ጥሩ ተስፋ ይኖርሀል!!
አላህ ለወዳጆቹ የገባዉን ቃል፤ ስኬታማነትን እና ደስታን ትጠባበቃለህ
አላህ እንዳለው፤
(ألَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّـهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ ٰ الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ ٰ لَهُمُ الْبُشْرَى فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ) يونس 62-64

<<ንቁ! የአላህ ወዳጆች፤ በነርሱ ላይ ፍርሀት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፤ እነርሱም እነዚያ ያመኑት እና ይፈሩት የነበሩት ናቸው፤ ለነሱ በቅርቢቱ ህይወትም በአኼራም ብስራት አላቸው>> ዩኑስ 62-64

እነዚህ በአላህ ያመኑ፣ አላህን የፈሩና በዲኑ ላይ የጸኑ ሰዎች ወዳጆቹ ናቸው
አዎን!! ስራዉን ያሳመረና በመልካም ስራ ላይ ነብሱን የታገለ ከአላህ መልካምን ይጠብቃል!!
©nesiha.com