Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አል-ዒባዳህ መስፈርቶቹና መሰረቶቹ

Selsebil Zumekan's photo.
አል-ዒባዳህ መስፈርቶቹና መሰረቶቹ
አምልኮ አላህን በብቸኝነት መገዛት ማለት ሲሆን አላህ ሰውንም ሆነ ጂንን የፈጠረው እሱን ሊያመልኩት ብቻ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ [٥١:٥٦]
“ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም::” {አዝ ዛሪያት 56}
አምልኮ ወይም “ኢባዳ” የተሰኘውን ቃል ዑለማዎች በተለያዩ ሀረጎች የገለፁ ሲሆን የሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ አገላለፅ ግን አጠቃላይና ብዙሃን ዑለማዎች ዘንድ ተመራጭ ሆኗል፡፡
ኢብን ተይሚያ እንዲህ ብለዋል፦
“አምልኮ ማንኛውም አላህ የመወዳቸውና የሚቀበላቸው ንግግሮችና ስራዎች ውስጣዊና ውጫዊ ተግባራት ማለት ነው::”
“አል ዒባደቱ ተውቂፊያህ”
ይህ ሸሪዓዊ መርሆ ሲሆን ትርጉሙ የአምልኮ ተግባራት ሸሪዓዊ መረጃዎችን መሰረት ያደረገ እንጂ በስሜትና በግል ፍላጐት የሚፈፀም አይደለም ማለት ነው፡፡
አላህ እንዴት መመለክ እንዳለበት ሰዎች በምርምርና ጥናት የሚደርሱበት ባለመሆኑ መልክተኞችን በመላክና መፅሀፎችን በማውረድ የአምልኮ አይነቶችን ስርዓቶቻቸውንና ዝርዝር የአፈፃፀም ሁኔታዎችን በሚገባ አስረድቷል፡፡
በመሆኑም አላህ በሚወደውና በሚቀበለው መልኩ ለማምለክ ስራዎቻችንን በቁርአንንና ሀዲስ መረጃዎች መሰረት ማድረግ ግድ ይሆናል::
አላህ እንዲህ ይላል፡-
فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ [١١:١١٢]
“እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::”
ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ [٤٥:١٨] “ከዚያም ከነገሩ (ከሃይማኖት) በትክክለኛይቱ ሕግ ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል” {አል ጃሲያህ 18}
የዒባዳ መስፈርቶች
ማንኛውም አምልኮ ሁለት መስፈርቶችን ካላሟላ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
አንደኛው፡- ኢኽላስ ሲሆን ትርጉሙም አምልኳዊ ስራዎችን ለአላህ ብቻ መፈፀምና ለርሱ በሚገቡ ስራዎች አንድንም ፍጡር አለማጋራት እንዲሁም አምልኮን ከይዩልኝ ይስሙልኝና ከመሳሰሉት ርካሽ ዓላማዎች ማጥራት ማለት ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا [١٨:١١٠]
«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው::” {አል ከህፍ 110}
فَاعْبُدِ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ [٣٩:٢]أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ
“አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው፡፡ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው::” {አዝ ዙመር 2-3}
قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ [٣٩:١١]وَأُمِرْتُ لِأَنْ أَكُونَ أَوَّلَ الْمُسْلِمِينَ [٣٩:١٢]قُلْ إِنِّي أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّي عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ [٣٩:١٣]قُلِ اللَّهَ أَعْبُدُ مُخْلِصًا لَّهُ دِينِي [٣٩:١٤]
“በል «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፡፡«የሙስሊሞችም መጀመሪያ እንድኾን ታዘዝኩ፡፡»«እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በል፡፡አላህን «ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እግገዛዋለሁ» በል::” {አዝ ዙመር 11-}
ለአላህ ብቻ መፈፀም የሚገባውን አምልኳዊ ተግባር ለፍጥረታት ማድረግ አምልኮን ከመሰረቱ የሚንድ የአላህን ምህረት የሚያርቅና የጀሀነም እሳት ውስጥ የሚያዘወትር አደገኛ ኃጢአት ነው::
አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا [٤:٤٨]
“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::” {አን ኒሳእ 48}
وَلَوْ أَشْرَكُوا لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ [٦:٨٨]
“ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር::” {አን አንዓም 88}
وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ [٣٩:٦٥]بَلِ اللَّهَ فَاعْبُدْ وَكُن مِّنَ الشَّاكِرِينَ [٣٩:٦٦]
“ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል:: ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም:: ከአመስጋኞቹም ኹን::” {65-66}
ለአላህ ብቻ መሰራት ያለባቸውን አምልኮዎች ስንፈፅም የሰዎችን እይታና አድናቆት የምንፈልግ ከሆነ ደግሞ ስራችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “አላህ እንዲህ አለ ፡- እኔ ከተጋሪዎቼ ሁሉ ሀብታሙ ነኝ ማንኛውም ሰው የትኛውንም ስራ ሰርቶ ከኔ ጋር ሌላን ካጋራበት እርሱንም ስራዉንም እተወዋለሁ::”ሙስሊም (2985)
መህሙድ ኢብን ለቢድ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “ለናንተ ከምሰጋቸው ነገሮች ሁሉ አስከፊው ትንሹን ሽርክ ነው” ሰሃቦችም፦ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሽርክ ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁ እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይዩልኝ ነው፤ አላህ የቂያማ እለት ሰዎችን ከመነዳ በኋላ እናንተ በዱንያ እንዲያዩላችሁ ትሰሩላቸው ወደ ነበራችኋቸው ሰዎች ሂዱና እነሱ ዘንድ ምንዳ ታገኙ እንደሆነ ተመልከቱ ይላቸዋል::”ሙስነድ አህመድ (23630)
ሁለተኛው መስፈርት፡- ʿአል ሙታበዓህ’
የአምልኮ ሁለተኛው መስፈርት ʿአል ሙታበዓህ’ ሲሆን የነቢያችንን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መመሪያ መከተል ማለት ነው፡፡
ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደኛ የተላኩት አላህ የሚወደውን ስራ ሊያስተምሩንና የአምልኮ ተግባሮችን ዝርዝር ሁኔታ ሊያስረዱን በመሆኑ እሳቸውን አርአያ ማድረግ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا [٣٣:٢١]
“ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ::” {አል አህዛብ 21}
وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا[٥٩:٧]
“መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ::” {አል ሀሽር 7}
እሳቸው በንግግራቸው ወይም በተግባራቸው ካሳዩት ስራ ውጭ የትኛውም አምልኳዊ ተግባር አላህ ዘንድ ተቀባይነት ካለማግኘቱም አልፎ ለጀሀነም ቅጣት የሚዳርግም ነው፡፡
ዓኢሻ ባስተላለፉት ሀዲስ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “በዲናችን ውስጥ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ይመለስበታል፡፡”ሙስሊም (1718)
በሌላ ዘገባም እንዲህ ብለዋል “ማንኛውንም ስራ የኛ ትዕዛዝ ሳይኖረው የሰራ ይመለስበታል፡፡”ሙስሊም (1718)
ዒርባድ ኢብን ሳሪያህ ባስተላለፉትም ሀዲስ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “መመሪያዬን አደራችሁ:: የመልካም ምትኮቼንም መመሪያ በቀንጣጢያችሁ ንከሱት:: አዳዲስ ነገሮችን ተጠንቀቁ:: መጤ ነገር ሁሉ የጥመት ነው፡፡” ኢብን ማጀህ (42)
የአምልኮ መሰረቶች
ኢስላማዊ አምልኮዎች በሶስት መሰረቶች የተገነቡ መሆን አለባቸው፡፡
1ኛ. ተመላኪውን (አላህን) በሙሉ ልብ የላቀ ውዴታ መውደድ፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ[٢:١٦٥]
“እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ ይበልጥ የበረቱ ናቸው::” {አል በቀራህ 165}
2ኛ. አላህን በሙሉ ልብ መከጀል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَيَرْجُونَ رَحْمَتَهُ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُ[١٧:٥٧]
“እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡ ቅጣቱንም ይፈራሉ::”{አል ኢስራእ 57}
3ኛ. አላህን ከልብ መፍራት
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَيَرْجُونَ رَحْمَتَهُ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُ[١٧:٥٧]
“እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡ ቅጣቱንም ይፈራሉ::”{አል ኢስራእ 57}
ዑለማዎች እንዲህ ይላሉ “አላህን በውዴታ ብቻ የሚያመልክ ዚንዲቅ (ከዲን ትዕዛዝ አፈንጋጭ) ነው:: አላህን በክጀላ ብቻ የሚያመልክ ሙርጂዓ ነው:: አላህን በፍራቻ ብቻ የሚያመልክ ኸዋሪጅ ነው፡፡”

Post a Comment

0 Comments