Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ በተራዊህ ሰላት ውስጥ ኢማሙን ለመከታተል በማለት ማእሙሞች ቁርአን መያዛቸው እንዴት ይታያል? (ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ)

Taju Nasir's photo.
ጥያቄ፦ በተራዊህ ሰላት ውስጥ ኢማሙን ለመከታተል በማለት ማእሙሞች ቁርአን መያዛቸው እንዴት ይታያል?
መልስ፦ ለዚህ አላማ ብሎ ቁርአንን መያዝ ሱናን መፃረር ነው። ይህም በተለያየ መልኩ ነው፦
አንደኛ፦ በቂያም ላይ ሰውየው ቀኝ እጁን ግራ እጁ ላይ ማድረጉ ይቀርበታል።
ሁለተኛ፦ አስፈላጊ ላልሆኑ እንቅስቃሴዎች ይዳርጋል። እነሱም፦ ለምሳሌ ቁረአንን መክፈት፣ መዝጋት፣ በብብት ሥር ወይም በኪስ ማድረግና የመሳሰሉት ናቸው።
ሦስተኛ፦ እነዚህ እንቅስቃሴዎች የሰጋጁን ትኩረት ያዛባሉ።
አራተኛ፦ ሰጋጁ የሱጁድን ቦታ መመልከቱ ያመልጠዋል። አብዛኛዎቹ ዑለሞች እንደሚሉት ደግሞ በሰላት ጊዜ የሱጁድን ቦታ መመልከት ሱናና በላጭ ነው።
አምስተኛ፦ ይህን የሚያደርግ (ቁርአንን የሚይዝ) ሰው ልቡ ወደ ሌላ ቦታ ካሰበ ሰላት ውስጥ መሆኑን ሊረሳም ይችላል። በአንፃሩ ቀኝ እጁን ግራ እጅ ላይ አድርጎና አንገቱን ሰብሮ ወደ ሱጁድ ቦታ እየተመለከተ በኹሹዕ ከቆመ ግን ልቡን ለመሰብሰብና ከኢማም ሗላ ሆኖ በመስገድ ላይ መሆኑን ለማስታወስ በጣም ቅርብ ነው።
(ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ)