Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የፍጥረት አለም የመኖር ሚስጥሩ Gtm

አቡ ኢልሀም's photo.
የፍጥረት አለም የመኖር ሚስጥሩ
አለም ተዘርግቶ ፍጥረት እንዲኖሩ
የነብያት መላክ ስቃይ ማስተናገድ
የሙዕጂዛ መብዛት የኪታብ መወረድ
የሰሃቦች ልፋት ከሀገር መሠደድ
ሆኖ ከተገኘ ተውሂድን ለማምጣት
ቅድሚያ ለተውሂድ ቅድሚያ በመስጠት
በቅድሚያ ለተውሂድ የለውም ጥፋት
በቅድሚያ ለተውሂድ ምንም ሳትከፋ
እኔኑ ምከረኝ ተውሂድን አታጥፋ
መንገድን አትዝጋ ይነገር በኢፋ
ስራ እንዲወደድ በአረህማኑ ጌታ
ወንጀላችን በዝቶ ለማግኘት ይቅርታ
ጀነትን ለማግኘት ከአዛብ ቆይታ
ቅድሚያ ለተውሂድ ነው የሚሠጠው ቦታ
ቅድሚያ ለተውሂድ
ቅድሚያ ለተውሂድ
ሰላም ይስፈንና ምድር ትረጋጋ
አላህ ሆይ ጠብቀን ከሽርክ አደጋ