Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የውስጥ አይን አይታጠብም

"የውስጥ አይን አይታጠብም"
***********************
የነብዩ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ትዕዛዝ እሳቸው እንዳሳዩን ብቻ ነው የምንተገብረው።
1) አንድ ሰው ውዱ ሲያደርግ የውስጥ አይኑን አያጥብም። ምንም እንኳን አይን አላህ ያልፈቀደላትን ተመልክታ ሊሆን ቢችልም። ፊት ሲታጠብ አብሮ የውጨኛው የአይን ክፍል ይታጠባል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያሳዩን ይህን ብቻ ስለነበር።
2) ካዕባ ላይ ጠዋፍ ሲደረግ ሀጅረል አስወድ እሳቸው ስለሳሙት አቅሙ ለቻለ ሰው ይሳማል። ሩክነል የማኒ ለቻለ ሰው በእጅ ይዳበሳል። እኛም እሳቸው የቆሙበት መቆም አለብን።
ከነዚህ ምሳሌዎች የምንረዳው እኛ የአላህ ውድ የሆኑትን ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መከተል እና እሳቸው ያሳዩንን ብቻ መከተል ግድ ይለናል መመራትን ከፈለግን።
ዲን በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ የወረደውን መከተል ነው። አለበለዚያ ዲን በአቅል ያለ ማስረጃ ቢሆን ኖሮ "ኹፍ" ካልሲ ላይ ሲታበስ ከስር ይሆን ነበር ነገር ግን ነብዩ ያሳዩን ከላይ አብሰው ነው።
እኛም አላህ እውቀትን እና የሳቸውን ሱና ከሚተገብሩት እንዲያደርገን እንለምነዋለን።