Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል ሀያ ሁለት

አቡ ኢልሀም's photo.
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ
ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል ሀያ ሁለት
መዲና ውስጥ በቆዩበት ወቅት በተቀሩት የእስልምና ድንጋጌዎች ታዘዙ ምሣሌ ዘካ ፣ ፆም ፣ ሀጅ ፣ ጂሀድ ፣ አዛን በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ከዚህም ውጪ ባሉ የእስልምና ድንጋጌዎች
እነዚህን ድንጋጌዎች ለአስር አመት ሙሉ ሲያስተምሩ ከቆዩ ቡሀላ የአላህ ሠላትና ሠላም በሣቸው ላይ ይሁንና ሞቱ ሆኖም እምነታቸው ግን ዘላቂ ነው ። ይህ ነው እምነታቸው! አንድም መልካም ነገር የለም እሣቸው ለህዝባቸው ያመላከቱት ቢሆን እንጂ ፣ መጥፎም የለም ያስጠነቀቁት ቢሆን እንጂ ።
ያመላከቱት መልካሙ ነገር ተውሒድ እና አላህ የሚወዳቸውን ነገራቶች በአጠቃላይ ነው ። ያስጠነቀቁት ነገር ደግሞ ሽርክ እና አላህ የሚጠላቸውን ነገራቶች በአጠቃላይ ነው ።
ወደ ሠው ልጆች በአጠቃላይ ነው የላካቸው ።አላህ በሁለቱም ግሩፖች ላይ (ሠው እና ጂን) እሳቸውን መታዘዝ ግዴታ አድርጓል
መረጃ አላህ እንዲህ ይላል [እናንተ ሠዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ በላቸው]
አጭር ማብራርያ
የረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አሞሞት በአጭሩ
የአላህ መልእክተኛ (ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም) ከመሞታቸው ቀደም ብሎ በሀጀተል ወዳእ ላይ ትልቅ ምክር አዘል ከባድ የሆነ ሁጥባ አድርገው ነበር በመቀጥልም "ዛሬ እምነታችሁን ሞላሁላቹ… "የሚለው የቁርአን አንቀፅ ሢወርድ አቡበክር ሢዲቅ በሠማ ወቅት አለቀሠ… ሡሀቦች "ይህች አንቀፅ ልክ እንደሌሎች አንቀፅ የተወረደች አንቀፅ ናት ለምን ታለቅሣለህ? በማለት ሢጠይቁት ይህ አንቀፅ የነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም መሞቻ መቅረቡን የሚያመላክት አንቀፅ ነው አላቸው"ወደ አላህ የምትመለሡበትን ቀን ፍሩ… ) የሚለው አንቀፅ ከወረደ ከዘጠነኛው ቀን ቡሀላ በአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ላይ በሽታው ይበረታባቸው ጀመርየኡሁድ ሠማሀታት ወደ ተቀበሩበት ጉድጓድም መሄድ እንደሚፈልጉ ተናገሩ ሔደው እገደሉ አፋፍ ላይ ቆመው "አሠላሙ አለይኩም የእሁድ ሠመሀታት ሆይ! እኛ በአላህ ፍቃድ ከናንተ ጋር ተገናኞች ነን እኔም በአላህ ፍቃድ ከናንተ ጋር የምገናኝ ነኝ "አሉከዚያራ መልስ የአላህ መልዕክተኛ ያለቅሡ ጀመር ። ምንድነው የሚያስለቅሦት? ብለው ሢጠይቋቸው "ወንድሞቼ ናፈቁኝ " በማለት ሢመልሡ እኛ ወንድሞችህ አደለንም እን? ሢሉ መልሠው ጠየቁ የአላህ መልዕክተኛም "እናንተ ጓደኞቼ ናቹ ወንድሞቼ እነዛ ከኔ ብሀላ የሚመጡ እኔን ሣያዩ በኔ የሚያምኑ ናቸው "በማለት መለሡላቸው ያ! አላህ ከመልዕክተኛው ወንድሞች አድርገንከመሞታቸው ከ3 ቀን በፊት እመይሙና ቤት ሆነው በሽታው እጅጉኑ ሢበረታባቸው ሚስቶቻቸው ሁሉም እንዲሠበሠቡ አዘዙ ተሠበሠቡ "አኢሻ ቤት ሁኜ በሽታዬን ላስታም ትፈቅዱልኛላችሁን?"በማለት ጠየቁ ፈቁዱላቸው። በራሣቸው ሊቆሙ ሞከሩ አልቻሉም አልይ ኡብኑ አቢ ጣሊብ እና ፈድል ኣብኑ አባስ ደግፈው ከመይሙና ቤት ወደ አኢሻ ቤት ወሠዷቸው ።ሡሀቦች የአላህ መልዕክተኛን ለመጀመርያ ግዜ በንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ሆነው ስላዩዋቸው በአላህ መልዕክተኛ ላይ ምን ደረሠ በማለት ደጋግመው መጠየቅ ጀመሩ ሠዎች እመስጂድ ውስጥ ተሠባሠቡ እስኪገፋፉ ድረስ መስጂዱ ሞላ ።አኢሻ ከሠው ልጅ ይህን ያክል ላብ ሢወጣ አይቼ አላውቅም እስክትል ድረስ ያልባቸው ጀመር ።በእጄ ፊታቸውን እያበስኩ እሣቸው (ላ ኢላሀ ኢለላህ ኢነ ሊል መውቲ ለሠከራ" ሲሉ ነበር ትላለች እናታችን አኢሻ ።እመስጂድ ውስ ጫጫታው ሢበዛ የአላህ መልዕክተኛ ምንድነው? ሢሉ ጠየቁ ያንተ መታመም አስጨንቋቸው ነው ሢባሉ ያዙና እዛ ውሠዱኝ አሉ ሌቆሙ ሞከሩ አልቻሉም እራሣቸውን እስኪስቱ … ሠዎች ደግፈው ሚንበር ላይ አወጧቸው የመጨረሻቸው ሁጥባ እንዲህ ሢሉ አቀረቡ "እናንተ ሠዎች ሆይ! ለእኔ ፈርታቹ ነውን? "አዎን የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ""እናንተ ሠዎች ሆይ! ቀጠሯቹ ከኔ ጋር ነው ዱንያ አደለችም ቀጠሯቹ ከኔ ጋር ሀውድ ላይ ነው። በአላህ ይሁንብኝ እኔ ከዚሁ ከመቆምያዬ እንደማየው ነኝ። በአላህ ይሁንብኝ እኔ በናንተ ላይ ድህነትን አልፈራም እኔ በናንተላይ የምፈራው ዱንያን ነው ። ከናንተ በስተፊት የነበሩት እንደ ተሽቀዳደሙባት ትሽቀዳደሙና እንደጠፋቻቸው እንዳትጠፋቹ ነው።… በመቀጠልም "በአላህ አስምላቹሀለው ሠላትን አደራ… " በማለት ደጋገሙ በመቀጠል "በሤቶቻችሁ ላይ አላህን ፍሩ (እንዳትበድሏቸው) በሤቶቻችሁ መልካምን እንድትውሉ እመክራቹሀለው "። በመቀጠልም "ጌታው ባርያውን በዱንያና እሡ ዘንድ ባለው አስመረጠው ባርያውም ጌታው ዘንድ ያለውን መረጠ "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ይህን ሢሉ ምንለማለት እንደፈለጉ ከአቡበከር ሢዲቅ በቀር ማንም አልተረዳቸውም ነበር ለዚህም አቡበከር ሢዲቅ ማልቀስ ጀመሩ የረሡልን ንግግር በማቋረጥም"አባታችን ፣ እናቶቻችን ፣ ልጆቻችን ፣ ሚስቶቻችን ፣ ገንዘቦቻችን ፊዳ ይሁንሎት እያለ ሢደጋግም ሠዎች እንዴት የአላህ መልዕክተኛን ንግግር ይቆርጣል የአላህ መልእክተኛ ከአቡበከር ወቀሣውን መከላከል ጀመሩ እንዲህም አሉ "እናንተ ሠዎች ሆይ አቡበክርን ተውት ከናንተ መካከል አንዳችሁም እኛ ዘንድ ውለታ የለውም የመለስንለት ቢሆን እንጂ, የአቡበክርን ሢቀር የሡን ውለታ መመለስ ስላቃተኝ የሡን ውለታ መመለስ ለአላህ ትቼዋለው የሁሉም የመስጂድ በሮች ይዘጋሉ የአቡበክር ሢቀር "በስተመጨረሻም ከሚንበር ከመውረዳቸው በፊት ለሙስሊሞች ዱአ ማድረግ ጀመሩ "አላህ ይጠብቃቹ ፣ አላህ ይርዳቹ፣ አላህ ያፅናቹ ፣ አላህ ያግዛቹ …"በህዝቦች መሀል ለመጨረሻ ግዜ ይህንን ተናገሩ "እናንተ ሠዎች ሆይ! እስከ ቂያማ ቀን ድረስ እኔን ለተከተሉኝ ሠዎች ሠላምታ አድርሱልኝ "ከዛም ከሚንበር አውርደው ወደቤት መለሧቸውእቤት ሆነው አብድረህማን ኢብኑ አቡበክር መፋቅያ ይዞ ገባ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ወደ መፋቅያው መመልከት ጀመሩ በሽታቸው በጣም ከመበርታቱ የተነሣ ስጠኝ ማለት አቅቷቸው ዝም ብለው ይመለከቱታል አኢሻ ረዲየላሁ አንሀ መፋቂያውን ሢመለከቱ አይታ ፈልገው እንደሆነ በመረዳት ከአብድረህማን በመቀበል በተከበረው ነብይ አፍ ስር አኖረችው ሆኖም መፋቅያው ደረቅ ስላለ መፋቅ አልቻሉም ። አኢሻ አፏ ስር ከታ ለስለስ አድርጋ በድጋሚ ወደ ነብዩ አፍ ከተተችው "ለመጨረሻ ግዜ ወደ ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አፍ የገባው የኔ ምራቅ ነው አላህ በኔ ላይ ከዋላቸው ችሮታዎች መካከል የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በህይወት እያሉ የኔ እና የሣቸው ምራቅ መገናኘቱ ነው "ትል ነበርቀጥላም ልጃቸው ፋጢማ ገባች የአላህ መልዕክተኛ መቆም አለመቻላቸውን ስታይ አለቀሠች አይኖቹዋ መሀል ይስሟት ነበርየአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም "ፋጢማ ሆይ ወደኔ ቅረቢ" አሉ ጠጋ ስትል አናገሯት ይበልጡኑ አለቀሠች ስታለቅስ "ፋጢማ ሆይ ወደኔ ቅረቢ አሏት " አሁንም በድጋሚ በድብቅአናገሯት ሣቀች ከሞቱ ቡሀላ ምንድነው በሚስጥር ያሉሽ ተብላ ስትጠየቅ መጀመርያ "እኔ ለሊት ሟች ነኝ "ይሄ አስለቀሠኝ በሁለተኛው ደግሞ "በኔ ላይ ሀቅ ካላቸው ቤተሠቦቼ የመጀመርያዋ አንቺ ነሽ "ሢሉኝ ሣኩኝ አለችአኢሻ እንዲህ ትላለች "እቤት ውስጥ ያለውን ሠው ባጠቃላይ አስወጡ "ካሉ ቡሀላ "አኢሻ ሆይ ወደኔ ጠጋ በይ አሏት እና እደረቷ ላይ ተኝተው እጃቸውን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ"እላይኛው ቀበሌ … "በማለት ሢደጋግሙ እየተስመረጡ መሆኑን ተረዳሁኝጅብሪል ገባና አንተ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! መለኩል መውት በር ላይ ቆሙዋል እንዲገባ እያስፈቀደህ ነው ከዚህ በፊት ለማንም አላስፈቀደም የአላህ መልዕክተኛም "ጅብሪል ሆይ ፍቀድለት" አሉት መለከል መውት ገባ ሠላምታ አቀረበ እንዲህም አለ አላህ በዱንያ መኖርን እና ከአላህ ጋር መገናኘትን እንዳስመርጥህ ነው የላከኝ "አላቸው እሳቸውም "እላይኛው ቀበሌ "በማለት ደጋገሙመለከል መው አናታቸው ጋር በመቆም "አንቺ ጥሩ ነፍስ ሆይ የሙሀመድ ኢብኑ አብደላህ ኑህ ወደ አላህ ወደ ሆነው ውዴታ ውጪ ጌታ የወደደ ሢሆን ሣይቆጣብሽአኢሻ "እጃቸው ወደቀች ጭንቅላታቸውም ከበደኝ መሞታቸውን ተረዳው የማደርገውን አጣው በሩን ከፍቼ ወጣሁና የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ ዐለይሒ ወሠለም አረፉ አልኩኝ መስጂዱ በለቅሦ ተናወጠኡስማን ኢብኑ አፋን እንደ ህፃን ልጅ እየተያዘ ያለቅሣል ፣ኡመር ሠይፉን አውጥቶ አንድ ሠው ሙሀመድ ሞቷል ይበልና አንገቱን ነው የምቆርጠው ሙሀመድ አልሞተም ሙሣ ጌታውን ሊገናኝ እንደሔደው እሡም ጌታውን ሊገናኝ ሔዶ ነው ይመለሣል በማለት ተናገረ ፣ ፅኑው የሆነው አቡበክር ሢዲቅ ያሉበት ገባና አአአ… የልብ ወዳጅ አአአ… ውዳችን አአአ… ነብያችን አለናሣማቸው ህይወትህም ሞትህም አማረ አለና ወጣ ከዛም "ሙሀመድን የሚገዛ ካለ ሙሀመድ በርግጥ ሞቷል አላህን የሚገዛ ካለ አላህ ህያው ነው የማይሞት "ኡመር ሠይፉን ጣለ ሞተው እንደነበረ አውቂያለው ብቻውን ሆኖ የሚያለቅስበት ቦታ ይፈልግ ጀመርየአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ተቀበሩ በአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አፈርን መበተን አስቻላችሁን አለች ፋጢማፋጢማ "አባቴ ሆይ! የጌታውን ጥሪ ሠማ አባቴ ሆይ! መኖርያህ ጀነተል ፊርደውስ ነው… አለች