Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሲህር ((ድግምት))

ቅድሚያ ለተውሒድ's photo.
ሲህር ((ድግምት))
ድግምት፦ “ሲህር” (ድግምት) በዓረብኛ ቋንቋ ስውር የሆነና ምክንያቱ ያልታወቀ ነገር ማለት ነው፡፡
ሸሪዓዊ ትርጉሙ፦ ልብን ወይም አካልን በማሳመም ወይም በመግደል ተፅዕኖ የሚያሳድር እንዲሁም በባልና ሚስት መካከል የሚለያይ ልፍለፋና ትብተባ ሲሆን ነገር ግን ሁሉም ተፅዕኖ ሊያደርግ የሚችለው በአላህ ፍቃድ ብቻ ነው::
ድግምት ኩፍር ሲሆን ድግምተኛም በአላህ የካደ ካፊር በመሆኑ አኺራ ላይ ምንም ዕጣ ፈንታ የለውም፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
َ
‹‹ሰይጣናትም በሱለይማን (ሰሎሞን) ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ (ድግምተኛ አልነበረም)፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር
(ያስተምሩዋቸዋል)፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር
ይማራሉ፡፡ እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም
ይማራሉ፡፡ የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም እድል የሌለው መኾኑን በእርግጥ ዐወቁ፡፡
ነፍሶቻቸውንም በርሱ የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በኾኑ ኖሮ (ባልሠሩት ነበር)፡፡›› (አል በቀራህ 1ዐ2)
☞ ይህን ርዕስ ላነሣ የወደድኩ በአሁን ወቅት ላይ ለደጋሚዎች ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እየሆነ ለማህበረሠቡ ደግሞ ከሚባለው በላይ በሠላም የመኖር ጠንቅ እየሆነ እየመጣ ያለ ነገር መሆኑ ነው
☞ በድግምት ምክንያት ተማሪ ከትምህርቱ ይታገዳል አዎን ወንድሞቼ በተለየያዩ ዩኒቨር ሲቲዎች የምንሠማው ነገር እጅጉኑ ለጆሮ የሚሠቀጥጥ ልብን የሚያሣምም ነገር ነው በሀራም መንገድ ጓደኜነት አልፈልግም ብላ እራሧን ከወንጀል ለመጠበቅ የምትጥረዋን ፈሪሀ አላህዋን የሚያስቋጥረውን አስተብትቦ አስተብትቦ ከትምህርቷ እና ከቂርአቷ ያግዳታል ሲብስ ደግሞ ለከፋ በሽታ እና ለህልፈት ይዳርጋታል ።
☞ በድግምት ምክንያት ሠራተኛው ከስራ ቦታው ይፈናቀላል ለአንድ ወንድሙ አላህ ዱንያን ሰጥቶት ገንዘቡን አላህ ባዘዘው ነገር እያዋለው በዛው መጠን አላህ ደግሞ በሠጠው ነገር ላይ እየጨመረለት ሢሔድ ይመለከትና በቅናት መንፈስ እርር ድብን ቅጥል ብሎ ወደ ነዚሁ ደጋሚዎች ጎራ ይላል የሚያስተበትበውን አስተብትቦ ሠውየውን በተለያየ ነገር ያውከዋል ከስራው ያፈናቅለዋል… ።
☞ ድግምት ቤተሠብ ይበትናል ባልን ከሚስቱ ሚስትን ከባሏ ይለያያል በሚዋደዱ ጓደኛሞች መሀል ጥላቻን ይጥላል ይለያያቸዋል
✔ ሌሎችም በማህበረሰቡ ውስጥ በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ ኡማውን የሚያውክ አጥፊ ተግባር ነው
✔ኢስላም እነዚህን የከፋ ጥፋቶች እንዲሁም በውስጡ ያሉ ሽርክያት የሆኑ ተገባሮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ይህን ተግባር(ሲህርን) ከክህደት እና ከአጥፊ ነገራቶች ተርታ ያሰልፈዋል
የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ
(ሠባት አጥፊ ወንጀሎችን እራቁ) እነማን ናቸው ተብለው ሢጠየቁ "በአላህ ላይ ማጋራት ፣ ድግምት ፣ አላህ ህርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል ፣ አራጣ መብላት፣ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት ፣ የፍጥጫ ቀን ወደውሀላ ማፈግፈግ ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ንፁህ ምዕመናትን በዝሙተኛነት መስደብ "በማለት መለሡ
✔ አልፎም ደጋሚው ላይ በርካታ የኢስላም ሊቃውንታት የክህደትን ብይን ይሠጣሉ ይህን ብይናቸውንም እላይ በጠቀስነው የቁርአን አንቀፅ ላይ ይደገፋሉ
✔ ወደ ዚህ ደጋሚ ጋር መሔድ በራሱ (ሔዶ ማሠራቱ አይደለም) መሔዱ ብቻ በነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ላይ በተወረደው መካድ ነው የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ
"የሩቅ ሚስጥር አውቃለው ብሎ የሚሞግት ሠው ጋር ወይንም ጠንቋይ ጋር የመጣ እና የተናገረውን እውነት ብሎ የተቀበለው ሠው በርግጥም በሙሀመድ ላይ በተወረደው ክዷል "
✔ በዚህ መሠረት ደጋሚም አስደጋሚም የኢስላምን ብርሀን ከላያቸው ላይ አውልቀው የጣሉ የጨለማው ማህበረሠብ ቂላቂሎች ናቸው ማለት ነው
ምክር ቢጤ
ለደጋሚዎቹ
☞ እናንተ ደጋሜዎች ሆይ አላህን አትጠነቀቁትምን? ለማትሞላ ዱንያ ሙስሊሞችን አዛ ስታደርጉ ቆይታችሁ!! ሁሉም አላህ ፊት ቆሞ የሚተሣሠብባት ቀን ሲመጣ የዛኔ ለአላህ ምን ትሉታላችሁ?? አላህ እንዲህ ይላል
"እነዚያ ምእመናንን እና ምእመናትን ባልሠሩት ነገር የሚያሠቃዩ እብለትን እና ግልፅ ሀጥያትን በርግጥ ተሸከሙ "
ለአስደጋሚዎቹ
☞ አንተ በወንምህ ደስታ የቀናህ ምትሀተኛ ሆይ አላህን ፍራ አንተም ነገ አላህ ፊት ቆመህ ትጠየቃለህ በወንድምህ ቀንተህ የሡን ለማጥፋት ከምትዋት አላህ ከማይጎለው ካዝናው እንዲሠጥህ ተማፀነው ይህ ለዱንያህም ለአሔራህም የተሻለና በላጭ ነው ። አንቺም በእህትሽ እውቀት እርር ድብን ብለሽ ለክፋት ከምትሮጪ አላህ አንቺንም አዋቂ የማድረግ አቅም አለውና ተናንሠሽ ተማፀኝው ።
ለማህበረሠቡ
☞ በመጀመርያ ደረጃ የሚከሠቱ ነገራቶች በአጠቃላይ የሚከሠቱት በአላህ ፍቃድ እና ውሣኔ መሆኑን ጠንቅቀን ልናውቅና አምነን ልንቀበል ግድ ይላል የሚደርስብን ማንኛውም ችግር ወይንም የምናገኘው ማንኛውም ጥቅም አላህ ከፃለን ውጪ ሊሆን አይችልም
"እወቅ! ህዝቦች አንተን አንዳች ነገር ለመጥቀም ቢሠባሠቡ አላህ የፃፈልህ ካልሆነ በቀር አይጠቅሙህም,በአንዳች ነገር ሊጎዱህም ቢሠባሠቡ አላህ የፃፈብህ እስካልሆነ ድረስ አይጎዱህም "ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
☞ ይህ ከመሆኑም ጋር እነዚህ ሤረኞች መጀመርያ ወደ እኛ እንዳይደርሱ መከላከያዎች አሉ እነሡን መጠቀም ከደረሡ ቡሀላም ቀላል ማስወገጃ መንገድ አለው በዛ መንገድ ማስወገድ
ከመከሠቱ በፊት
☞ በተለያየ አጋጣሚ እንድንላቸው የታዘዝናቸውን የአዝካር አይነቶች በቦታቸው ማለት ምሣሌ ከቤት ሲወጣ ፣ ወደ ቤት ሲገባ ፣ የጠዋትና የማታ ዚክር … እና ሌሎችንም አዝካሮች በተገቢው መልኩ መጠቀም
ከተከሠተ ቡሀላ
☞ ለታመመው ሠዎ የተለያዩ በሀዲስ ተነጥለው የመጡትን የቁርአን አንቀፆች እና ዱአዎች እያነበቡ መድሀኒቱን ተጠቅሞ በአላህ ፍቃድ ፈውስ ማግኘት
አላህ ከድግምተኛ ሴራ ይጠብቀን!!!!

Post a Comment

0 Comments