Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ምንም አዲስ ነገር የለም ሸይኽ ሙሐመድ አብድል ወሃብን (ረሂመሁላህ)

ምንም አዲስ ነገር የለም
ሸይኽ ሙሐመድ አብድል ወሃብን (ረሂመሁላህ) ሽርክ እና ቢድዓ ላይ የወደቁ ሱፍዬች፣ አህባሾች፣ ሺዐዎች፣ ቀብር አምላኪዎች፣ አሽአሪዬች፣ ኢኽዋኖች እና ተብሊጎች ይጠሉታል፡፡
ሸይኽ ረቢዕ ኢብን ሀዲ አል መድኸሊን (ሀፊዘሁላህ) ኢኽዋኖች፣ ሺዐዎች፣ ቁጥቢዬች፣ ሱሩርዬች፣ ተክፊሮች፣ ተብሊጎች፣ ሱፍዬች፣ ሌሎችም ፖለቲከኞች ይጠሏቸዋል፡፡
ለምን ?
ምክንያቱም የያዙትን ውድቅ አስተሳሰብ እና እምነት በቁርዓን እና በሀዲስ ማስረጃ ውድቅ ስለሚያደርጉባቸው ነው፡፡
እንደሚታወቀው ለሃቅም አጋዥ አላት ለጥመትም ተከታይ አላት፡፡
ታድያ ምን አዲስ ነገር አለው? የቢድዓ ሰው የሱና ሰዎችን፣ ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩትን፣ ከሽርክ እና ቢድዓ የሚያስጠነቅቁትን እንዲወድ አይጠበቅም፣ ይህን የሚያስብ ምስኪን ነው፡፡
ምንም አዲስ ነገር የለም ትላንት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በእነ አቡ ጀህል የተጠሉት እና ጠላት ተደርገው የተያዙት ተውሂድን ይፋ ስላደረጉ እና ሽርክን ስላወገዙ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ እነ ኢማሙ አሕመድ በቢድዓ ሰዎች የተጠሉት፣ የተገረፉት ሱናን አጥብቀው ስለያዙ ነው፡፡ በየዘመኑ ወደ ሃቅ የሚጣሩትን የሱና ወዳጆች ማንም አይጠላቸውም ወይ ጃሂል (አላዋቂ) ወይንም የስሜት እና ቢድዓ ተከታይ ቢሆን እንጂ፡፡
አላህ ለሱና ኡለማዎች ክብር ከሚሰጡት ያድርገን፡፡