Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆምን የሚያበላሹ (የሚያፈርሱ)ነገሮች ስምንት ናቸው፡፡

ፆምን የሚያበላሹ (የሚያፈርሱ)ነገሮች ስምንት ናቸው፡፡ እነርሱም፦
1. የግብረስጋ ግንኙነት የረመዳንን ፆም መፆም ግዴታነት የፀናበት ፆመኛ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የግብረስጋ ግንኙነት ከፈፀመ በዚህ ድርጊት ምክንያት ፆም ይፈታል፡፡ በመሆኑም ይህንን ዕለት በሌላ ጊዜ መፆሙ ግዴታ ከመሆኑም ጋር ማካካሻ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ማካካሻውም ባርያን ነፃ ማውጣት ካላገኘም ሁለት ወራትን በተከታታይ መፆም ይህንም ካልቻለ ስልሣ ምስኪኖችን ማብላት ነው፡፡
2. ብልትን በመነካካት ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጋር በመተሻሸት ወይም በመሳሳም አሊያም በመተቃቀፍ እና በተመሳሳይ ሁኔታዎች ፍትወትን ማፍሰስ፡፡
3. እንደ ሲጋራ ያሉ ነገሮችን መጠቀምም ይሁን ሌሎች የሚጠቅሙም ሆነ የሚጐዱ ነገሮችን መብላት ወይም መጠጣት፡፡
4. ምግብን ሊተኩ የሚችሉ ሀይል ሰጪ መርፌዎችን መወጋት ፆምን ያበላሻል፡፡ ምክንያቱም እንደነዚህ አይነት መድሃኒቶች ሙሉ በሙሉ የምግብ አይነት ጥቅም ሊሰጡ የሚችሉ ከመሆናቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የምግብነት ባህሪ የሌላቸውን መድሃኒቶች በመርፌ በጡንቻ ወይም በደም ስሮች ላይ በመወጋት መጠቀም ፆምን አያበላሽም፡፡ በጐሮሮው ውሰጥ የጠብታው ጣዕም ቢታወቀውም እንኳ ፆሙ አይበላሽም፡፡
5. ደምን መውሰድ ይህም ማለት ለምሳሌ አንድ ፆመኛ ደም ቢፈሰው እና ምትክ ደም መውሰድ ቢያስፈልገው ፆሙ ይበላሻል፡፡
6. የወር አበባ እና የወሊድ ደም መፍሰስ፡፡
7. በዋግምት እና በመሳሰሉት መንገዶች ደምን ማስወጣት፡፡
8. ሆንብሎ (እጅን እና መሰል ነገሮችን በመጠቀም) ማስታወክ (ማስመለስ) ሲሆን ነገር ግን ግለሰቡ ከቁጥጥሩ ውጪ ሆኖ ቢያስመልሰው ፆሙ አይበላሽም፡፡

Post a Comment

0 Comments