Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

` الاختلاط بين الرجال والنساء 👥 የወንዶችና ሴቶች ቅልቅሎሽ

Abufewzan Ahmed's photo.
` الاختلاط بين الرجال والنساء
👥 የወንዶችና ሴቶች ቅልቅሎሽ 👥
የተንቢሃት ልዩ መልዕክት ቁ• 23
ኡኽቲ... ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ ያናግሩሻል፤
ከታላቁ ሊቅ ሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ቢን ባዝ ድንቅ ምክርን ያዘለ ፈትዋ የተቀነጨቡ ጭብጦች [አላህ ይዘንላቸው]
ሒጃብ ምንድነው መረጃውና አስፈላጊነቱን ሁሉ ዳስሰው ተከታዮቹን ቁምነገሮች አስተላልፈዋል፤
☞ ሒጃብሽ አስፈላጊና ግዴታሽ ነው!
☞ ከቅርብ ቤተሰቦችሽና አማቾችሽ [ካአጎትና ካአክስት ልጅ፣ ከባል ወንድም… ] ጭምር ተሸፋፈኚ። በቀላሉ ስሚያገኙሽ ይበልጥ አስጊው የነሱ መንገድ መሆኑንም ልብ በይ።
⇄ልቡ ንፁህ ነው እንዲህ ያለ ነገር አያስብም የሚል ቀጭን ምክንያት ከፊትና አንፃር ቦታ የለውም
↪ባህልና ተለምዶ ከሸሪዓ በላይ ሊሆን አይገባም።
⇘ከወንዶች ጋር ያለ በቂ ሒጃብ ከመቀላቀል ተቆጠቢ።
⇘ተሸፋፍነሽም ቢሆን ማህረምሽ (አባትሽ፣ አጎትሽ፣ ወንድምሽን የመሳሰሉ የቅርብ ቤተሰብሽ) በሌለበት ከባዕድ ወንድ ጋር በገለልተኛ ቦታ እንዳትገኚ።
ከወንዶች ጋር ከሚያጋፋሽና ከሚያነካካሽ ቦታዎች ያቅምሽን ያህል ራቅ በይ።
✔ሸይጣን ባገኘው ቀዳዳ ሊያጠቃሽ አሰፍስፏልና መንገዶቹን አትቅረቢ።
⚂ላሳለፍሽው ህይወትሽ ተውበት አድርገሽ ጌታሽን ምህረቱን ጠይቂው።
⇘የማንንም ትችት፣ ወቀሳና ውዥንብርም አትፍሪ። እንዳሻው ሊዘልብሽ እንጂ አዝኖልሽ አይደለምና።
↳ ለሁሉም ቁርኣናዊና ሀዲሳዊ ግልፅ መረጃዎችን ከነማብራርያው ገልፀውልሻል☞
♂ የክብርሽ በር ክፍት ሆኖ እንዲቀር የሚሟገቱሽ ሰዎች ምን ይሆን ፍላጎታቸው
ያቀረቡልንን መረጃዎች☞
قال الشيخ الامام العلامة ابن باز -رحمه الله - السلام عليكم ورحمة الله وبركاته أما بعد :
🔅قال الله سبحانه وتعالى :
﴿ وَقُلْ لِلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلا مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِ ّ﴾
النور: 31
« ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ »
🔅وقال تعالى :﴿ وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ ذَلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ ﴾
الاحزاب:53
አላህ አዝዘ ወጀልለ የውስጥ አዋቂ ነውና☞
« ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡ » ይላል
قالت أم سلمة رضي الله عنها : " لما نزلت هذه الآية خرج نساء الأنصار كأن على رءوسهن الغربان من السكينة وعليهن أكسية سود يلبسنها " ،
ኡሙ ሰለማህ ረዲየላሁ ዐንሃ ስለ ሶሃቢያት አቋም እንዲህ ትላለች☞
🔅وقال تعالى :﴿ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُلْ لِأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِنْ جَلابِيبِهِنَّ ذَلِكَ أَدْنَى أَنْ يُعْرَفْنَ فَلا يُؤْذَيْنَ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَحِيمًا ﴾
الاحزاب:59
« አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
“ይህች አንቀፅ ስትወርድ የአንሷር ሴቶች ከቤታቸው ወጡ። ከእርጋታቸውና ጥቁር ከመልበሳቸው የተነሳም አናታቸው ላይ ቁራ ያለ ይመስል ነበር።”
በማለት እነዚያ ቀዳም ምእመናን ሴቶች የቁርኣን አንቀፁን እንዴት ሙሉ በሙሉ በመሸፋፈን እንደተረዱትና እንደተገበሩት አስገንዝበዋል።
ከሱና መረጃዎች መካከልም☞
🔅 ومن أدلة السنة أن النبي ﷺ لما أمر بإخراج النساء إلى مصلى العيد قلن يا رسول الله إحدانا لا يكون لها جلباب فقال النبي ﷺ : " لتلبسها أختها من جلبابها " رواه البخاري ومسلم ،
መልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሴቶችን ለዒድ ሰለሰት ሲያዝዙ አንዷ ሴት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ በመካከላችን ጅልባብ የማይኖራት ኣለች" ስትላቸው “እህቷ ከጅልባቧ ታልብሳት” ሲሉ መልሰውላታል።
በማለት ጅልባብ ላለመልበስ ምንም አይነት ከልካይ ምክንያት እንደሌለ ገልፀዋል
🔅وقد ثبت في الصحيحين عن عائشة رضي الله عنها قالت : كان رسول الله ﷺ يصلي الفجر فيشهد معه نساء متلفعات بمروطهن ثم يرجعن إلى بيوتهن ما يعرفهن أحد من الغلس وقالت : " لو رأى رسول الله ﷺ من النساء ما رأينا لمنعهن من المساجد كما منعت بنوا إسرائيل نساءها " ،
ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች☞
« መልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፈጅር ሰላትን ሲያሰግዱ ሴቶችም በመሸፋፈኛቸው ተጠቅልለው አብረው ይሰግዱና ማንም ሳያያቸው ወደየቤታቸው በጭለማው ይመለሱ ነበር። “ ነገር ግን እኛ ዛሬ ያየነውን የሴቶች ሁኔታ መልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቢያዩ ኖሮ በኑ ኢስራዒል ሴቶቻቸውን እንዳገዱት ሁሉ እሳቸውም ያግዷቸው ነበር።” »
ብላለች በማለት ቀስ በቀስ የሂጃብ ስርኣትና የቅልቅሎሽ ደንብ እየተጣሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
🔅وعن عائشة رضي الله عنها قالت :
" كان الركبان يمرون بنا ونحن محرمات مع رسول الله ﷺ فإذا حاذونا سدلت إحدانا جلبابها على وجهها من رأسها فإذا جاوزونا كشفناه " رواه أحمد وأبو داود وابن ماجة
ለሐጅ አምልኮት ፊትን መከፈት የተደነገገ ቢሆንም ባዕድ ወንድ ሲገጥም ግን ዓኢሻ ረዲየለሰሁ ዐንሃ እንዳለችው☞
«ከመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ኢህራም አድርገን እየሄድን ሳለ ተሳፋሪዎች እየመጡ ያልፉን ነበረና፤ እኛጋ ሲደርሱ አንዳችን ከአናታችን ላይ ጅልባባችንን ወደ ፊታችን ጣል እናደርግና ሲያልፉን ደግሞ ፊታችንን እንከፍታለን።» በማለት ጥንቃቄያቸውንና ፊት የመሸፈንን ግዴታነት አቅርበዋል።
🔅وقد خرج النبي ﷺ ذات يوم من المسجد وقد اختلط النساء مع الرجال في الطريق فقال النبي ﷺ : " استأخرن فإنه ليس لكن أن تحققن الطريق عليكن بحافات الطريق " فكانت المرأة تلصق بالجدار حتى أن ثوبها ليتعلق به من لصوقها ،
ከመስጂድ እንኳ ሲወጡ ግርግር እንዳይፈጥሩ፣ ከወንዱ እንዳይቀላቀሉ☞
« ወደኋላ ሁኑ። የመንገዱን መሃል መያዝ አይገባችሁም። ጥጉን ይዛችሁ ሂዱ።» በማለት ከግፊያና ከአጉል መነካካትና መተሻሸት አግደዋል።
🔅ذكره ابن كثير عند تفسير قوله تعالى :
﴿ وَقُلْ لِلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِن ﴾
ኢብኑ ከሲር «ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡… » የሚለውን አንቀፅ ሲተረጉሙ ☞
“ ለቅርብ ቤተሰቦቿ ካልሆነ በቀር ሴት ልጅ ፊቷን መገለጥን ተከልክላለች። ከባዕዳን ጋር መገለልን፣ መቀላቀልን እንደተከለከለች ሁሉ ፊቷን መሸፈን ግድ ተደርጎባታል።” ብለው አስፍረዋል።
🔅فعن عقبة ابن عامر رضي الله عنه أن رسول الله ﷺ قال : " إياكم والدخول على النساء " فقال رجل من الأنصار يا رسول الله أفرأيت الحمو؟ قال : " الحمو الموت " متفق عليه ، والمراد بالحمو أخ الزوج وعمه ونحوهما ؛
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም « ሴቶች ላይ መግባትን ተጠንቀቁ።» ሲሉ ከአንሳሮች መካከል አንዱ ሰው "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የባሏ ወንድም፣ አጎቱ ቢሆኑስ? " ሲላቸው «የባሏ ወንድምና የባሏ አጎትን የመሳሰሉትማ ሞት ነው» ብለው የቅርብ ሰዎች ይበልጥ ጥንቃቄ እንዲደረግባቸው አስጠንቅቀዋል።
🔅 وقال ﷺ في الحديث المتفق عليه :
" لا يخلون رجل بامرأة إلا مع ذي محرم "
« ወንድ ልጅ መህረሟ በሌለበት ከሴቷ ጋር እንዳይገለል።» በሚልም ራሳችንን ለፈተና እንዳንዳርግ ተቁመዋል።
🔅 وقد ثبت عنه ﷺ أنه قال : " لا يخلون رجل بامرأة فإن الشيطان ثالثهما " رواه الإمام أحمد بإسناد صحيح عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه ،
« ወንድ ከሴት ልጅ ጋር አይገለል። ሶስተኛቸው ሸይጣን ነውና። » በማለት አጉል በራስ መተማመን እንደሌለብን መክረዋል።
والله اعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
ሙሉውን መልዕክት በቀጣዩ ማስፈንጠርያ ያገኙታል⇘
____________
http://www.binbaz.org.sa/node/8288
----------------------
www.facebook.com/tenbihat
✒ ረጀብ19/07/1436
ግንቦት May 08/05/2015