Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከአርሽ በላይ በሆነው ጌታዬ እምላለው! ቀብር አለብንና ፤ አላህ ፊት መቆም አለብንና ፤ ሲራጥ አለብንና ፤ ጀነት ወይንም ጀሐነም አለብንና ... ከሐቅ በህዋላ ማንንም በጭፍን አንከተልም !!

Abubeker Siraj's photo.
ከአርሽ በላይ በሆነው ጌታዬ እምላለው!
ቀብር አለብንና ፤ አላህ ፊት መቆም አለብንና ፤ ሲራጥ አለብንና ፤ ጀነት ወይንም ጀሐነም አለብንና ...
✘ ከሐቅ በህዋላ ማንንም በጭፍን አንከተልም !! ✘
ማሊክም ቢሆኑ፣ ወላ ኢማሙ አሕመድ፣ ወላ ኢብኑ ተይሚያሕ፣ ወላ መሐመድ ዐብዱል ወሐብ፣ ወላ ኢብኑ ባዝ፣ ወላ አልባኒ፣ ወላ አማን አል ጃሚ (ረሕመቱላሂ ዐለይሒም ጀሚዐን)
አሁንም ..
ወላ ፈውዛን ፣ ወላ ዑበይድ አል ጃቢሪ ፣ ወላ ረስላን ፣ ወላ ረቢዐል መድኸሊ ... ( አላህ የህፈዘሁም ጀሚዐን)
እኛ የምንከተለው ሐቅን ብቻና ብቻ ነው!
ሐቁም የአላህ ኪታብና መልዕክተኛው (صلى الله عليه وسلم) ናቸው!
ታዲያስ ድሮስ ከጌታችን በቀር ለኛ መመለሻ ማን አለንና?
ታሪክ ግን ብዙ ያስተምረናል!
ሐቅን የሙጢኝ የያዙ ሁሉ በሐቅ ተፃራሪዎች ሁሌም ይፈተናሉ!
ከድሮም ጀምሮ ሐቅን የሙጢኝ ያሉት የአላህና የመልዕክተኛው ወዳጆች ስም ይለጠፍላቸዋል!
ለምሳሌ ያክል ..
በኢማሙ ሻፊዒይ (ረሒመሁላህ) ዘመን ሰዎች የኢማሙ ሻፊዒይን ዳዕዋ መና ለማስቀረት ደባ መክረው ኢማሙ ሻፊዒይን «ሯፊዲ» ናቸው ብለው ስም በመለጠፍ ማስወራትና ሕዝቡን ከሳቸው ዒልም ተጠቃሚ እንዳይሆን ማራቅ ጀመሩ! ይሄኔ ነው ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ብለው ይሄን እርባና ቢስ ሐሜት በሁለት ስንኝ ግጥም ድባቅ የመቱት ...
ﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﺭﻓﻀﺎً ﺣﺐ ﺁﻝ ﻣﺤﻤـــــــــدٍ
ﻓﻠﻴﺸﻬﺪ ﺍﻟﺜﻘﻼﻥ ﺇﻧﻲ ﺭﺍﻓﻀـــﻲ !
(ቤተ–ሙሐመድን መውደድ ሯፊዲነት ከሆነ)
(ሰውም ጂንም ይመስክር እኔም ሯፊዲ ነኝ)
ታዲያ ይቺ ግጥማቸው አገር አዳርሳ ጆሮ ጠቢን አሳፍራ ፣ የሸፍጠኞችን ሸፍጥ አሳጥታ ይሀው ታሪክ መዝገብ ላይ ለውሸታም አግድም አደጎች መመከሪያነት ትሆን ዘንድ ቁጭ ብላለች!
ታዲያ ታሪክ ራሱን ደግሞ የዘመኑ ፈርጥ የነበሩትን ተውሒድን በተሐድሶ ጥሪ ዓለም ያዳረሱት ሸይኹል ኢስላም ሙጀዲዱል ዳዕወቱ ተውሒድ ሙሐመድ ዐብዱል ወሐብ (ረሒመሁላህ) ጋር ሱናው ደረሰ!
አሁንም ጠላቶች እኚህን የኢስላም ሊቅ አንድም አዲስ ይዘው የመጡነት ነገር እንደሌላቸው ከማወቃቸውም ጋር የሚያደርጉትን የተውሒድ ዳዕዋ የ«ወሐቢ» ዳዕዋ በማለት ስም ለጠፉላቸው !
ዓላማቸውም የተውሒድን ዳዕዋ የአንድ ግለሰብ አስተሳሰብ አድርጎ በመሳል ከዚህ የተውሒድ ዳዕዋ ሰው በርግጎ እንዲርቅ የታቀደ ሴራ ነበር ። አላህ ግን ዓላማቸውን አላሳካላቸውም (( እነሱም ያሴራሉ አላህም ያሴራል ። አላህ ከሴረኞች ሁሉ በላጭ ነው))
ታላቁ ዓሊም ሠማሃቱ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ለነዚህ ስም ለጣፊዎች የኢማሙ ሻፊዒይን የግጥም ዘዬ ተውሰው እንዲህ በማለት መለሱላቸው ..
ﻓﺈﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﻣﻦﺩﻋﺎ ﺇﻟﻰ ﺗﻮﺣﻴﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻫﺎﺑﻲ
ﻓﺄﻧﺎ ﻭﻫﺎﺑــــــــــــﻲ،
((ወደተውሒድ መጣራት ወሐቢ ካስባለ
አዎ! እኔ ወሐቢ ነኝ))
ዛሬ እንደምንመለከተው የተውሒድን ዳዕዋ ቅድሚያ በመስጠት ሕዝቡን ከሽርክ ፅልመት ለማውጣት የሚጥሩ ዱዐቶች «ወሐቢ» የሚል መጠሪያ ይለጠፍባቸዋል ።
ይሀው «ወሐቢ» ከሚለው ሰውን ማስበርገጊያ እና ከተውሒድና ሱና ማራቂያ ቅፅላ ትይዪ አሁን ደግሞ ባለንበት ዘመን ተጨማሪ አዲስ ቅፅላ ከሱና ጠላቶች መንደር መሰማት ጀምሯል ። ይህም ልክ ከሸኹል ኢስላም ሙሐመድ ዐብዱል ‪#‎ወሐብ‬ (ረሒመሁላህ) ስም ወስደው « ‪#‎ወሐቢ‬ » የሚል ስያሜ እንዳመጡት አሁን ደግሞ ከታላቁ የዘመናችን ዓሊም ከሆኑት አል ዓላማ ዶ/ር ረቢዕ ኢብኑ ሐዲ አል ‪#‎መድኸሊ‬ (ሀፊዘሁላህ) ስም ወስደው ወደተውሒድና ሱና የሚጣሩ ከሽርክና ቢድዓ የሚያስጠነቅቁ ወንድሞችና እህቶችን «መድኸሊ» ብለው ስም መለጠፍ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል።
እኛ ሁለት ጥያቄ ብቻ እንጠይቃለን
1) ሸኽ ረቢዕ ዐቂዳቸው ብልሹ ነውን?
2) ሸኽ ረቢዕ አዲስ ይዘውት የመጡት ነገር አለን?
መልሱን ከታላቁ የዘመናችን ዓሊም ከነበሩት ሸኽ ሙሐመድ ሷሊህ ቢን ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንስማ ።
ሸኹ ስለሸኽ ረቢዕ ተጠይቀው እንዲህ አሉ: –
“ሸይኽረቢዕ አልመድኸሊ ከሱና ዑለማዎች አንዱ ነው፡፡ ዐቂዳውም
ጤነኛ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ዘንድ ቁንጮ የሆኑ
ሰዎችን ጥፋት ሲያጋልጥ ጊዜ የተለያዩ ስሞችን ለጠፉበት፡፡”
(ከሽፉሊሳም፣ ካሴት)
አዎን! ሸኽ ረቢዕን የሱና ጠላት የሆኑት ሰዎች ለምን ሊጠሏቸው ቻሉ የሚለውን ብናይ ምክንያቱ አንድና አንድ ነው! እሱም ተውሒድና ሱና ቅድሚያ ሰጥተው ስለሚያስተምሩና ሽርክና ቢድዓን ከነቤተሰቦቻቸው ስለሚያስጠነቅቁ ነው ። ሌላ አዲስ ነገር የለም!
ታዲያ ነገሩ እንዲህ ከሆነና እኛም ተውሒድና ሱናን አስቀድመን ሽርክና ቢድዓን ከነቤተሰቦቻቸው ስንቃወም «መድኸሊ» የሚል ስያሜ የሚለጠፍልን ከሆነ የኢማሙ ሻፊዒይን ግጥም ዘይቤ ተውሰን ለለጣፊዎቹ እንዲህ እንላቸዋለን .
ﺍﻥ ﻛﺎﻥ ﺣﺐ ﺍﻟﺤﻖ ﻣﺪﺧليا
ان كان كره الباطل مدخليا
ﻓﻠﻴﺸﻬﺪ ﺍﻟﺜﻘﻼﻥ ﺃﻧﻲ الرﺋﻴس ﻣﺪﺧﻠـــــﻲ
ሐቅን መውደዴ «መድኸሊ» ካስባለኝ
ባጢልን መጥላቴ «መድኸሊ» ካስባለኝ
ሰውም ጂንም ይመስክር ዋናው «መድኸሊ» ነኝ
ሸኽ ረቢዕ ማናቸው፤ ታላላቅ ዑለማዎች ስለዚህ የሱና ተፃራሪዎች «መድኸሊ» የባጢል ዘመቻ ምን አሉ፤ ስለሸኹስ ምን ይላሉ የሚለውን ውዱ ወንድሜ ዑመ ር ሐሰን በጥሩ እና ለንባብ በሚመች ሁኔታ አዘጋጅቶልናልና ከታች ያሉት አስፈንጣሪዎች ተጭነን እናንብባቸው ክፍል አንድ
http://tewhidfirst.blogspot.com/2015/01/blog-post_29.html
ክፍል ሁለት
http://tewhidfirst.blogspot.com/2015/05/blog-post_28.html
በመጨረሻም የምመክረው
ሸኹን እስከነመፈጠራቸው ሳታውቁ ተውሒድና ሱናን በመተግበራቹና ወደሱም በመጣራታቹ ብሎም ሽርክና ቢድዓን ከነቤተሰቦቻቸው በመቃወማቹና ከነርሱም በማስቀቃቹ ምክንያት «መድኸሊ» ፣ «ጃሚይ» ተብላቹ ስም የተለጠፈላቹ ወንድሞቼና እሕቶቼ በወቃሽ ወቀሳ በለፋፊ ወሬ አትደናበሩ ፣ አትዘኑ ፣ ተስፋም አትቁረጡ ይሄ የነቢያቶች ሁሉ ሱናህ ነውና ሶብር አድርጉ ።
በጭፍን ተመርታቹ፤ በቡድንተኝነት ታውራቹ፤ በውሸት ላይ ተንተርሳቹ .... ሰው ተውሒድና ሱናን አስተምሮ ሽርክና ቢድዓን ስለተቃወመ ብቻ «መድኸሊ» ሲባል ሰምታቹ የምታስተጋቡ ወንድም እና እህቶች “አላህን ፍሩ!” ልባዊ ምክሬ ነው ።
ባረከላሁ ፊኩም

Post a Comment

0 Comments