Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በሸይኽ ረቢእ ላይ ኡላማዎች ፅፈውባቸዋል ይባላል ፡፡ ለመሆኑ ታላላቅ ኡላማዎች ስለነሱ ምን ብለዋል ?

በሸይኽ ረቢእ ላይ ኡላማዎች ፅፈውባቸዋል ይባላል ፡፡
ለመሆኑ ታላላቅ ኡላማዎች ስለነሱ ምን ብለዋል ?
የኡለማዎች ውዳሴ ለሼይኽ ረቢአል መድኸሊ
1. ሰማሀቱ አልሙፍቲ አልሸይኽ አብደል አዚዝ ኢብን ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) ስለ ሸይኽ ረቢእ እና ስለ ሙሀመድ አማን አልጃሚ ተጠይቀው እንዲህ አሉ፡
‹‹ . . . . በተለይ በኚህ የተከበሩ ሁለት አሊሞች ሁለቱም አህሉ ሱና ናቸው ፡፡ በእውቀታቸው፣ በታላቅነታቸውና በተስተካከለ አቂዳቸው አውቃቸዋልሁ፡፡ ስለዚህ አደራችሁን በመፀሀፎቻቸው ተጠቀሙ፡፡›› (ሸሪጥ አል አስኢለቱ ሱወይዲያ)
አሁንም እንዲህ አሉ
‹‹ሸይኽ ረቢእ አህሉ ሱና ወልጃማአ ውስጥ ካሉት ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ ፅሁፍም ንግግሩም ይታወቃል፡፡›› ‹‹በመዲና ኡለማዎች ምንም ጥርጣሬ የለብንም፡፡ እነ ሸይኽ ረቢእ፣ሙሀመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ሷሊህ ኢብን ሰእድ አሱሀይሚ፣ሙሀመድ ቢንሃዲ አልመድኸሊ ሁሉም ፅኑ አቋም ያላቸው የእውቀት ሰዎች መልካም አቂዳ ያላቸው ናቸው፡፡›› ነገር ግን ብልሹ ሰዎች መጥፎ ዳኢዎች ና እነሱን የመሳሰሉት ናቸው በነዚህ ኡለማዎች ላይ የተለያዩ ማምታቻዎችን የሚለቁት፡፡›› በመቀጠል እንዲህ አሉ ‹‹ሸይኽ ረቢእ ጧኢፍ ላይ (አተመሱኩ ብል መንሀጅ አሰለፊ) በሚል ርእስ ያደረገውን ሙሃደራ ሰምቻዋልሁ፡፡ ይህችን የተባረከች ዳዕዋ ንግግር አዳምጫለሁ፣ መልካም ሰርቷል ለሰውም አስጠቅሟል ፡፡አላህ እጥፍ ድርብ የሆነ አጅር ይስጠው ››
2. ታላቁ አሊም አልሙሀዲስ አስለፊ አል አሰሪይ ሙሀመድ ናስረዱነል አልባኒ አላህ ይዘንላቸው ስለ ሸይኽ ረቢእ እና ሸይኽ ሙቅቢል ተጠየቁ እንዲህ አሉ ‹‹እነዚህ ሁለቱ መሻኢኾች ወደ ቁርአንና ወደ ሀዲስ ተጣሪዎች ናቸው እንዲሁም ሰለፉን ሷሊህ ወደ ነበሩበት መንሃጅ ይጣራሉ ትክክለኛውን መንገድ የተውንና የተፃረረን መልስ በመስጠት የተካኑ ናቸው፡፡›› በመቀጠልም ‹‹ የሸይኽ ረቢእ የተለያዩ ኪታቦችን አንብቢያለሁ ሁሉም ኪታቦቹ ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ምንም ስህተት አላገኘሁም፡፡ ከአህሉሱናዎች መንሐጅም አልወጣም፡፡›› በጥሩ ልንገራችሁ ‹‹የዘመኑን የጃርህና የተእዲል ባንድራ የያዘው ወንድማችን ዶ/ር ሸይኽ ረቢእ አልመድኸሊ ነው፡፡ በሱላይ ረድ የሚሰጡ ሰዎች እውቀትን መሰረት በማድረግ አይደለም የሚመልሱት በጭራሽ ምክንያቱም እውቀት ከሱ ጋር ነውና ያለው፡፡ ረቢእ ላይ ረድ አደርጋለሁ የሚል ሰው ከሁለት አንዱ ነው ፡፡ ወይ ጃሂል ነው መማር አለበት ወይም ሰው ለማስጠላትና በሰው ላይ ቅስቀሳ ለማድረገ ያሰበ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (ምንጭ-ሸሪጥ አልሙዋዘናት ቢድአቱል አስር)
3. ታላቁ አሊም ሙሀመድ ቢን ሷሊህ ን ኡሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) ስለ ሸይኽ ረቢእ ተጠይቀው እንዲህ አሉ ፡
‹‹ሰውየው (ሸይኽ ረቢእ) የሱና ሰውነው የሀዲስም ሰው ነው፡፡›› በመቀጠልም እንዲህ አሉ ‹‹ሸይኽ ረቢእ በሰለፎች መንሀጅ የሚጓዝ ሰው ነው በተለይ ደግሞ አቂዳን ተህቂቅ በማድረግ (በማረጋገጥ) በኩልና የሚቃረኑትን መልስ በመስጠት እንዲሁም የሸይኽ ረቢእን ኪታብ መግዛትና መሸጥ እንዴት ይታያል? ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መለሱ ‹‹ጥያቄው አስፈላጊ ጥያቄ አለመሆኑ ግልፅ ነው አንድ ነገር ልንገራችሁ ኢማሙ አህመድ ስለ ኢስሃቅ ኢብን ራሀዊህ በተጠየቁ ግዜ እንዲህ አሉ ስለ ኢስሃቅ ቢን ራሃዌይህ እጠየቃለሁ? እንዲያውም ኢስሃቅ ነው ስለእኔ መጠየቅ ያለበት ብለው ነበር ›› አሉ ፡፡ ከዚህ የምንረዳው (ስለኔ ረቢእ ይጠየቅ እንጂ ስለ ረቢእ እንዴት እኔ እየጠቃለሁ) ማለታቸው ነው ፡፡
ምንጭ- ሸሪጥ (አስኢለቱ ሲወይዲያ)
4. ታላቁ ና እውቁ አሊም አሸይኽ አል አላማ ሷሊህ ኢብን አብደላህ አልፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡፡
‹‹መንሀጁል አነቢያእ ፈደእዋ ኢለሏህ ›› የሚለው የሸይክ ረቢእ ኪታብ የነብያቶችን አካሄድ እና የተቃራኒ ጀማአዎችን አካሄድ እያመሳከረ የሚዘግብ ምሳሌዎቹ የሚማርኩ ግልፅና ሀቅን ለሚፈልግ አስፈላጊ የሆነ ኪታብ ነው፡፡ ይህ ኪታብ ሁሉን ነገር ያሟላ በቂ ኪታብ ነው ፡፡ ለኩራተኞችና ለትዕቢተኞች መረጃ ይሆንባቸዋል፡፡››
ምንጭ-(ሙቀዳመቱ ነስረዳ አዚዝ ሊሸይኽ ረቢእ)
‹‹ታላላቅ የመዲና ኡላማ የሆኑት ለምሳሌ ሼይኽ አብዱል ሙህሲን ኢባድ፣ ሸይኽ ረቢእ ኢብን ሃዲ፣ሸይኽ ሷሊህ ሱሀይሚ፣ሸይኽ ሙሀመድ አማነልጃሚ እነዚህ ኡላማዎች ከሰለፊያ መስመረ አስቦም ይሁን ሳያስብ የወጣን እና ኡማውን ለማሳሳት የተነሳ ሁሉ አጥጋቢ መልስ ሰጥተዋል፡፡አስጠንቅቀዋልም፡፡ ጤነኛውንና በሽተኛውን የመለየት ብቃት ሙያውም ተሞክሮውም አላቸው ፡፡ እናም ከአስተምህሮቶቻቸው ብዙ ጥቅም አለበትና ፡፡››
ምንጭ-ሸሪጥ (አሰደስተል ሱወይዲን) ረቡአሳኒ 5፣14-17