Abufewzan Ahmed
` °•° ማንን ነው የወደድነው°•°
ክፍል -4
` ሙሐመድﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ከመነሻ እስከ መድረሻ
ክስተት 5
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°
ክፍል -4
` ሙሐመድﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ከመነሻ እስከ መድረሻ
ክስተት 5
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ነቢዩ ኢብራሂምን አለይሂ ሰላም ያሉበትን የፍልስጢንን ምድር ለቅቀ እንዲሰደዱ አዘዘ።
አዲሷንና የተናፋቂው ልጁን እናት
ሃጀርን ከነ ልጇ አስከትለዋል። የሄዱበት አቅጣጫ እንዳይታወቅም ዱካቸውን እያጠፉ ጉዞ ጀመሩ።
ሃጀርም የተራመደችበት የኮቴዋ ፋና እንዳይታይ በጥንቃቄ ተራመደች።
ይህ ሁሉ ጥረት በቤታቸው የተከሰተውን አዲስ በረከት ማንም እንዳያውቅባቸው ነበር።
እንደሚታወቀው በተራው ህዝብ ኣፍ የገባ ነገር ባብዛኛው መልካምነት የለውም። በአሉባልታና በውዥንብር ሀገሩን ከመናጥ ውጭ ለቤተሰቡ ሰላም የሚፈይደው የለም። እሳቸውም ጉዳያቸውን አላህ እንዳዘዛቸው ተገበሩት።
~ ኢብራሂም ነቢይ ናቸውና ከራሳቸው ፍላጎት የሚፈፅሙት ምንም ነገር የለም።
~ የኢስማዒል እናት ሃጀርም ባሏን በመታዘዝና ባለውለታዋን ሳራን ላለማስከፋት ስትል ቤቷን ለቅቃላት አቅጣጫው ወደ ማይታወቅበት ስፍራ ጉዞ ቀጥላለች።
~ አራስ ነኝና ልረፍ አላለችም። ልጄም ጨቅላ ነውና ትንሽ ከፍ ይበልልኝ አላለችም። የመልካም ውለታ ምላሹም መልካም ነውና የባለውለታዋን ደስታ ላለመንፈግ የመጣውን ለመሸከም ወሰነች፤ ተጓዘች።
የወደፊቷ የአሽረፈል ኸልቅ የሙሐመድ ﷺ የትውልድና የኑቡዋ ሀገር የሆነቿ የመፅናኛዋ ምድር፣ ቅድስቲቷን ሀገር ኣስቧት፤ ለማንና ለምን እየተዘጋጀች እንደሆነም አስተውሉ።
የነ ኢብራሂም ግስጋሴ ቀጠለ ፤ የሻም ምድርን ፍልስጢንን ለቅቀው ወጥተው ፤ የሂጃዝ ምድርንም አቋርጠው ቅድስቲቷ ስፍራ መካ ደረሱ። ይህ ጉዞ ባሁኑ ዘመን ልኬት ከ2300 ኪሎሜትር በላይ እንደሆነ ይገመታል።
በዚያች የፋራን ተራሮች በከበቧት፣ ሰላማዊና የተረጋጉት ሸለቆዎች ባጀቧት፣ ከምድሮች ሁሉ ያማረቿና በተባረከቿ ስፍራ ፤
በዚያ ወደፊት ጎልቶ በሚታየው ታላቁ ክቡር ጅምር ግንባታ ዘንድ፣ በዚያ የካዕባ ጥንስስ መሰረት ስር… ኢብራሂም አለይሂ ሰላም ሃጀርንና ጨቅላውን ኢስማዒልን አስቀመጡ።
እነሆ ኢብራሂም በዚህ ቦታ ሲያሰፍራቸው ጥቂት ምግብና በአነስተኛ እቃ ውሃ ሰጥተዋቸው ማንም በሌለበት፣ የሰው ዘር ባልተሰማበት ፣ አረንጓዴ ቡቃያ በማይገኝበት፣ የወፍ ድምፅ እንኳ በማይሰማበት፣ የሰው ዘር ኖሮበት በማያውቀው ባዶ በረሃ ትተዋቸው ወደ ሳራ ሊመለሱ ፊታቸውን አዞሩ።
ኡሙ ኢስማዒል ልትከተለው ሞከረች፤ ነገር ግን ነቢዩ ኢብራሂም ጉዞአቸውን አጠንክረው ተራመዱ።
የሃጀር ሁኔታን እናስተውል
~ ከደመቀ ቤተ መንግስት ፣ ከሞቀ ከተማ ወጥታ ከማታውቃቸው ሰዎች ጋር ኑሮን ጀመረች። ብዙም ሳትቆይ የልጅ እናት ሆነች።
የጀመረችው አዲስ ኑሮ በቅፅበት ተቀይሮ ለስደት ተዳረገች።
ያንን ሁሉ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ፣ ያንን በረሃ አቋርጣ መካ ደረሰች። ዛሬ ደግሞ የሰው ዘር በማይታይበት፤ ምንም አፅናኝ በሌለበት በመካ ሸለቆዎች ከነ ጨቅላ ህፃኗ ለብቻዋ ትተዋት ሊሄዱባት ነቢዩ ኢብራሂም ቆርጠዋል። ፊታቸውንም ዘወር ሳያደርጉ ጉዟቸውን ቀጠሉ።
🎆
ሃጀርን ድንጋጤ ያዛት፤ ስጋትና መዋለል ወረራት። በዚህ ኮረብታ መሃል ለማን ትቷት እንደሚሄድ ግራ ገባት።
ከተተወላት አንዲት አቁማዳ ውሃና ለምግብነት የምትውል አነስተኛ ተምር እንጂ ምንም ስንቅ የላትም።
በዚህ በረሃ የሚገጥማትን አስከፊ ነገር የሚከላከልላት ከአምላኳ ከአላህ በስተቀር ለሰበቡ እንኳ የምታየው ትጥቅም ወገንም የላትም።
በዚህን ግዜ ነበር ወደ ልጇ አባት ነቢዩ ኢብራሂም ተማፅኖዋን የጀመረችው።
ወደ ኢብራሂም እያየችም
”إلا من تكلنا يا إبراهيم“
" ኢብራሂም ሆይ
ለማን ነው የተውከን ? "
ስትል አስተጋባች።
በዚህ ሸለቆ ውስጥም ለብቻዋ ጥሏት እንዳይሄድባት ደጋግማ በሚያሳዝን አንደበት ጥያቄዋን ቀጠለች።
ከኢብራሂም ጉዞ እንጂ መልስ አላገኘችም።
ኡሙ ኢስማዒል ተስፋ አልቆረጠችም ዐይኗንም በሱ ላይ ተክላ ተከተለችው።
« ኢብራሂም ሆይ
ማንም ምንም በሌለበት በዚህ ሸለቆ ትተኸን ወዴት ነው ምትሄደው »
አሁንም መልስ የለም።
የሷ ጭንቀትና ስጋት ጨምሯል።
ኢብራሂምም ርህራሄና ሀዘኔታ ይዟቸው የጌታቸውን ትእዛዝ አላስረሳቸውም። ተዘናግተውም ዘወር ብለው ሳያይዋት እንዳልሰማት ሆነው ጉዟቸውን ቀጠሉ።
በዚህን ግዜ ሃጀር አንድ ነገር አስተዋለች። የኢብራሂም ቆራጥነትና ዝምታ ጥያቄ ወደ ሌላ ርእስ እንድትገባ አስገደዳት።
ክስተት 6
```````````
ኡሙ ኢስማዒል ሃጀር ሌላ ጥያቄ መጣላት… …
________
ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ከመነሻ እስከ መድረሻ
በ ክፍል -5 ቀጣዩን ቀደርና
የኡሙ ኢስማዒል ጥያቄን ምላሽ በአላህ ፈቃድ እናያለን።
احمد سيرة abufewzan 28Jan14
7 Rabi'e al-sani 1436
~`~…………………………~`~