ታላቁ አሊም ሙሀመድ ቢን ሷሊህ ን ኡሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) ስለ ሸይኽ ረቢእ ተጠይቀው እንዲህ አሉ ፡
‹‹ሰውየው (ሸይኽ ረቢእ) የሱና ሰውነው የሀዲስም ሰው ነው፡፡›› በመቀጠልም እንዲህ አሉ ‹‹ሸይኽ ረቢእ በሰለፎች
መንሀጅ የሚጓዝ ሰው ነው በተለይ ደግሞ አቂዳን ተህቂቅ በማድረግ (በማረጋገጥ) በኩልና የሚቃረኑትን መልስ
በመስጠት እንዲሁም vየሸይኽ ረቢእን ኪታብ መግዛትና መሸጥ እንዴት
ይታያል? ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መለሱ ‹‹ጥያቄው አስፈላጊ ጥያቄ አለመሆኑ ግልፅ ነው አንድ ነገር
ልንገራችሁ ኢማሙ አህመድ ስለ ኢስሃቅ ኢብን ራሀዊህ በተጠየቁ ግዜ እንዲህ አሉ ስለ ኢስሃቅ ቢን ራሃዌይህ
እጠየቃለሁ? እንዲያውም ኢስሃቅ ነው ስለእኔ መጠየቅ ያለበት ብለው ነበር ›› አሉ ፡፡ ከዚህ የምንረዳው (ስለኔ
ረቢእ ይጠየቅ እንጂ ስለ ረቢእ እንዴት እኔ እየጠቃለሁ) ማለታቸው ነው ፡፡ ምንጭ- ሸሪጥ (አስኢለቱ ሲወይዲያ)
4. ታላቁ ና እውቁ አሊም አሸይኽ አል አላማ ሷሊህ ኢብን አብደላህ አልፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹መንሀጁል
አነቢያእ ፈደእዋ ኢለሏህ ›› የሚለው የሸይክ ረቢእ ኪታብ የነብያቶችን አካሄድ እና የተቃራኒ ጀማአዎችን አካሄድ
እያመሳከረ የሚዘግብ ምሳሌዎቹ የሚማርኩ ግልፅና ሀቅን ለሚፈልግ አስፈላጊ የሆነ ኪታብ ነው፡፡ ይህ ኪታብ ሁሉን
ነገር ያሟላ በቂ ኪታብ ነው ፡፡ ለኩራተኞችና ለትዕቢተኞች መረጃ ይሆንባቸዋል፡፡›› ምንጭ- (ሙቀዳመቱ ነስረዳ
አዚዝ ሊሸይኽ ረቢእ) ‹‹ታላላቅ የመዲና ኡላማ የሆኑት ለምሳሌ ሼይኽ አብዱል ሙህሲን ኢባድ፣ ሸይኽ ረቢእ ኢብን
ሃዲ፣ሸይኽ ሷሊህ ሱሀይሚ፣ሸይኽ ሙሀመድ አማነልጃሚ እነዚህ ኡላማዎች ከሰለፊያ መስመረ አስቦም ይሁን ሳያስብ የወጣን
እና ኡማውን ለማሳሳት የተነሳ ሁሉ አጥጋቢ መልስ ሰጥተዋል፡፡ አስጠንቅቀዋልም፡፡ ጤነኛውንና በሽተኛውን የመለየት
ብቃት ሙያውም ተሞክሮውም አላቸው ፡፡ እናም ከአስተምህሮቶቻቸው ብዙ ጥቅም አለበትና ፡፡›› ምንጭ-ሸሪጥ
(አሰደስተል ሱወይዲን) ረቡአሳኒ 5፣14-17 ጥቂት ስለመድኸሊ 1. v መድኸሊ የሚለው ቃል ከይት መጣ ? v
መድኸሊ የሚለው ቃል ከሸይኽ ረቢእ ኢብን ሃዲ አልመድኸሊ የተያዘ ነው 2. v መድኸሊያ የሚለው ስም የተለጠፈው
በማን ላይ ነው ? v ቁርአንና ሀዲስን በሚከተሉ፣ ሱና የሚንፀባረቅባቸው የአቂዳ አፍቃሪዎችና ተውሂድን አሳምረው
የተረዱና የያዙ ሙብተዲኦዎችን ና ኢኽዋኖችን እንዲሁም ሌሎችን ቡድኖች የሚጋፈጡትን የሰለፊ አቋም ያላቸውን ሁሉ
መድኸሊያ ይሏቸዋል፡፡ ልክ ተውሂድ ያለውን ሰው ሁሉ ወሃብያ ብለው እንደሚጠሩት ወይም እንደሚለጥፉበት ሁሉ ቢድአን
የሚቃወምን ሰው ሁሉ መድኸሊያ ይሉታል፡፡ 3. ለመሆኑ ይህን ስያሜ ያመጡት እንማን ናቸው ? v ይህን ስያሜ ያመጡት
የፓለቲካ ሰዎች፣የሱና መካኖች ፣የአቂዳ እንቅፋቶች፣ የቢድአ አራማጆች፣ የባጢል አራጋቢዎች አስመሳይና አሳሳቾች
የሆኑት ኢኽዋኖች ናቸው ፡፡ እኚህ ቡድኖች ከኡላማኦች ስራ ሰዎችን ለማባረርና ለማደራሰት የተለያዩ መጠሪያ ስያሜዎች
መለጠፍ የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡ ድሮ ድሮ ‹‹ባዝያ፣ኡስይሚኒያ፣ጃሚ ያ፣›› እያሉ ሰዎችን ከሱና ሲያግዱ
ነበር፡፡ ባዝያ ፡- ወደ ሸይኽ ኢብን ባዝ ለማስጠጋት ፈልገው ሲሆን ኡሰይሚኑያ ፡- ደግሞ ወደ ሸይኽ ኡሰይሚ
የሚያስጠጉበት ነው ፡፡ ልከ እንደዚሁ ጃሚያ ፡- ወደ ሙሀመድ አማነልጃሚ አስጠግተውበታል፡፡ ዛሬ ዛሬ ደግሞ
መድኸሊያ ሱፐረ ስለፊያ፣ የመሳሰሉትን ስያሜዎች ሲያራግቡ ይታያሉ ፡፡ ነገ ደግሞ ምን እንደሚሉ ማን ያውቃል
?ምናልባት ‹‹ፈውዘውያ›› በማለት ወደ ሼይኽ ፈውዛን ሊያስጠጉ ይችላሉ፡፡ ኢክዋኖች ልዩ ባህሪያቸው ይኸው ቅጥፈትና
ማስመሰል ሲሆን ለሸይጣን የሚዘገንን (ለሸይጣን ሼም የሚያሲይዝ) ውሸትን ሲዋሹ ይሰማሉ ፡፡ 4. መድኸሊያን ለምን
መረጡ ? v ኢኽዋኖች የውሸት ፋብሪካዎች ፣ የቢድአ መጋዘኖች ፣ የአቂዳ እንቅፋቶች፣ የሱና ፀሮች ፣ሀቅን
የሚያድለበሰብሱ አስመሳዮችና የፖለቲካ አራጋቢዎች የኡለማ ጠላቶች መሆናቸውን ሸይኽ ረቢእ ባደባባይ አጋልጧቸዋል
ፅፎባቸዋል፡፡ መፈናፈኛ አሳጥቷቸዋል፡፡ አከርካሪአቸውንም ሰብሮታል፡፡ ስለሆነም ማንኛውንም የኢኽዋንን አመለካከት
በግልፅ የሚቃወም ሰው ሲያዩ መድኸሊይ ይሉታል፡፡ በጣም የሚገርመው እነዚህ ኢክዋኖች የሱፊ ወንድሞች፣የሺአ
ወዳጆ፣እንዲሁም የአህባሸ ድልድዮች መሆናቸው ፡፡ ታዲያ እነዚህ ቡድኖች (ፈርቃዎች ) ጋር አንድ መሆን ይቻል
ይሆን? ይህን ተግባራቸውን (ቢድአቸውን) ካልተውማ በፍፁም !! እኚህን ታላቅ አሊም ከዚህ በላይ የተጠቀሱት
ኡለማዎችና ሌሎችም ያወደሷቸው አንዳንድ አላዋቂ ልካቸውን የማያውቁ ተራ ስዎች መድኸሊያ ምን እያሉ ሕዝብያዎች
የሚሏቸውን እንደገደልማሚቱ ያስተጋባሉ ፡፡ እነዚህ ሰዎች መጨሀቸው ለምን ኢኽዋን ተነካ ብለው ከሆነ አላህ እንዳለው
በቁጭት ይሙቱ ገና ይቃጠላሉም ምክንያቱም ብዙ ረቢአዎች እየተፈጠሩ ነውና፡፡ አላህ ሰምተው ከሚጠቀሙት ያድርገን
0 Comments