ረመዳን አስመልክቶ ምክር
ሼኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ: “የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”
ሼኽ ፈውዛን: "አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው። ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: 'ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።' በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል: 'ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።' ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው።
ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው። ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።
ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት። ረመዳን የፍንጥዝያ፣ የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"
0 Comments