Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ረ መ ዳ ን ና ሴ ቶ ች

Abufewzan Ahmed's photo.
` ረ መ ዳ ን ና 💐 ሴ ቶ ች
ረመዳን የተሰኘው ወር በሂጅራ አቆጣጠር የአመቱ 9ኛው ወር ነው።
ሙስሊም የሆነ ሰው ሁሉ ይህንን ወር በየአመቱ ሙሉውን በመፆም እንድናሳልፈው ከጌታችን ሱብሃነሁ ወተዓላ 2ኛው አመት ሂጅሪያ ላይ ተደንግጎልናል።
ረመዳን ወርን መፆም የኢስላም 4ኛው መሰረት (አርካን) ነው። ስለሆነም የአንድ ሙስሊም ሙስሊምነት መለኪያ በመሆኑ በሸሪዓ ኣለመፆም ከተፈቀደላቸው ግለሰቦች በስተቀር ማንኛውም ሙስሊም የመፆም ግዴታ አለበት።
የረመዳን ወር ፆም በውስጡ በርካታ ትሩፋቶችና ልዩ የሆኑ ፀጋዎች ኣሉት።
መልዕክተኛውም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለ9 አመታት ያህል ፆመውታል።
በመሆኑም እንደማንኛውም ዒባዳ የፆሙ ስርኣት፣ ደንብና መስፈርት አለውና በርካታ ረመዳናዊ ድንጋጌች ተላልፈውልናል።
ከነዚያም መካከል አንድ ግለሰብ እንዲፆም የሚገደደው መቸ እንደሆነ የሚገልፀው የትምህርት ክፍል ዋነኛው ነው።
እነሆም እህቶቻችንን የተመለከተው የፆም ጅማሬ ርእስ እንደሚከተለው ነው።
` ረ መ ዳ ን 💐 መ ጣ ል ሽ
ታዲያ ልጃ ገረዶች በመፆም የሚገደዱት ከመቸ ጀምሮ ነው
ታዳጊ በሆነች ልጃገረድ ሴት ላይ ፆም ግዴታ የሚሆንበትን ግዜ በተመለከተ ሸይኽ ዐብደላህ ኢብን ጅብሪን (ረሂመሁላህ) ተጠይቀው ተከታዩን ምላሽ ሠጥተዋል ☞
ጥያቄ፦ አንዲት ታዳጊ ልጃገረድ ፆም መጀመር ያለባት መቼ ነው
« ታዳጊ የሆነች ልጃገረድ ፆም መጀመር ያለባት ሌሎች ግዴታ የሆኑ የአምልኮት (ኢባዳ) አይነቶችን መጀመር በሚኖርባት ግዜ ነው።
አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን ደረሰች የሚባለው☞
🍁 አስራ አምስት አመት ሲሞላት
🍁 ብልቷ አካባቢ ፀጉር መውጣት ሲጀምር
🍁 የወር አበባዋ መፍሰስ ሲጀምር ወይም ስታረግዝ ነው።
ስለዚህም ከነዚህ ከተጠቀሱት ነገሮች አንዱ በተከሰተባት ጊዜ ልጅቱ የአስር አመት ልጅ ብትሆንም እንኳ ለአቅመ ሔዋን ደርሳለችና መፆም በእርሱዋ ላይ ግዴታ ይሆንባታል።
አሁን አሁን እንደሚታየው በርካታ ልጃገረዶች የመጀመሪያ የወር አበባቸውን የሚያዩት በአስር ወይም በአስራ አንድ አመታቸው ነው።
ሆኖም ወላጆቻቸው ይህንን ሁኔታ ችላ እያሉና ልጆቻቸው አሁንም ገና የሆኑና ለአካለ መጠን እንዳልደረሱ በማሰባቸው እንዲፆሙ አያደርጓቸውም።
ይህ ፈፅሞ ስህተት ሲሆን ታዳጊ የሆነችው ልጃገረድ የመጀመሪያ የወር አበባዋን ካየችበት ግዜ ጀምሮ ለአቅመ ሔዋን መድረሷና ሙሉ ሴት መሆኗ የተረጋገጠ በመሆኑ ግዴታ የሆኑ የአምልኮት ተግባራት ሁሉ በእርሱዋ ላይ ይፀኑበታል። » ብለዋል።
ይህ ደግሞ በተለያዩ ሃዲሶች የተደገፈ አቋም ነው። በፉቀሃእ (በሊቃውንት) ዘንድም የታወቀ ጉዳይ ነውና አስራ አምስት አመት የሚለው የእድሜ ገደብ ከላይ የተገለፁትን ምልክቶች ላላየች ልጃገረድ ብቻ ነው።
አላህ መጪውን ረመዳን ሰላም ያድርሰን። ከሚጠቀሙበትም ያድርገን።
••••••••••••••••••••••••
🍃ተንቢሃት ዋትሳፕ ግሩፕ🍃
www.fb.com/tenbihat
__________
ሻዕባን 09/1436
27 /05/2015

Post a Comment

0 Comments