Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የውሸት አንድነት

የውሸት አንድነት
አንድ ሰው ተነስቶ እኔ አህባሽ አይደለሁም፡፡ አህባሾች አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን አያምኑም ቢል ብዙዎች ‹‹ማሻ አላህ፣ ጀዛከላሁ ኸይረን፣ ለአላህ ስል እወድሃለሁ›› እና የመሳሰለውን ይሉታል፡፡
ልክ ይሀው ሰው እኔ ሱፊ አይደለሁም፡፡ ምክንያቱም ሱፍዬችም ልክ እንደ አህባሾች አላህ ከአርሹ በላይ መሆኑን አይቀበሉም እንዲያውም ‹‹አላህ ሁሉ ቦታ ነው›› ይላሉ ሲል፣ ‹‹አንድነት በታታኝ፣ አላህ ሙስሊም ብሎ ነው የጠራን፣ ቅጥረኛ፣ ሙናፊቅ፣ የኡማው አንድነት አያሳስብህም…….. እና ….›› ይሉታል፡፡
እስቲ አንተ የአላህ ባርያ አላህ የሰጠህን ንፁህ ጭንቅላት ተጠቀምበት፡፡ አህባሽን የጠላሀው የእውነት ጥመቶችን ይዞ ስለመጣ ከሆነ ታድያ አንድ ብቻ የሆነችውን ሃቅ ተቃርኖ የመጣ ማንኛውንም ጀመዓ ይሁን ግለሰብ ለምን አትቃወምም፣ ለምንስ አትጠላም?
እውነት ለአላህ ብለህ/ሽ ከነበረ አህባሽን የጠላሀው/ሽው?
ብቻ የውሸቱ አንድነት ምንነቱን ለማወቅ እነዚህን እና መሰሎች ከበቂ በላይ ናቸው፡፡ አላህ ለሱ ብለው ከሚወዱ ለሱ ብለው ከሚጠሉት ያድርገን፡፡