Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢትዬጵያ ሙስሊምን የጥይት እራት ለማድረግ እነማን ከነማን ጋር እየሰሩ ነው?

'ይህ ለናሙና ያህል እንጂ በጣም ብዙ በማስረጃ የተደገፉ ማቅረብ የምንችላቸው አለን በአላህ ፈቃድ።
የኢትዬጵያ ሙስሊምን የጥይት እራት ለማድረግ እነማን ከነማን ጋር እየሰሩ ነው?
ኡመር ኢብነል ኸጣብ ብልጦች አይደለንም ብልጣብልጦች ግን አይሸውዱንም ይላል፡፡

በአላህ በመታገዝ ከዚህ በታች የፃፍኩትን ፅሁፍ የፈርስት ሂጅራ ቪድዬን ማስረጃነት አድርጌ ነው፡፡ ፅሁፉ በማስረጃ ለሚያምኑ የቀረበ ነው፡፡

የፈርስት ሂጅራ መድረክ መሪ ክርስትያኑ ዮሃንስን ምን ብሎ ወደ መድረክ ጠራው?
‹‹ወንድሜ ዮሃንስ›› 
እንግዲህ እነዚህ ናቸው ለዲንህ ቆመናል የሚሉን፡፡ ዲናቸውን የማያውቁ ፖለቲከኞች፡፡ ሸሪዓችን አንድ ሙስሊም ያልሆነን ሰው ‹‹ወንድሜ›› ብለን እንዳንጠራ ከልክሎናል፡፡ ዳሩ እነዚህ በኢስላም ስም የሚነግዱ ሰዎች ካፊሮችን ወንድሜ እያሉ እየጠሩ እነሱ የሚሉትን ጭፍን ሙስሊሙን የሚያስጨርስ አካሄድ ያልተቀበለን ሙስሊም ‹‹ሙናፊቅ፣ ቅጥረኛ እና ሌላም›› እያሉ ሲጠሩ ይስተዋላሉ፡፡ ጥመትን እየተጓዙ እንደሆነ ይሀው ሸሪዓ መልስ ሰጣቸው፡፡

ዮሃንስ መድረክ ላይ ወጥቶ ምን ተናገረ?
1) ‹‹…. እኔ ግጥም አልችልም ግን ሙሃባዬን ለናንተ ያለኝን ለመግለፅ ነው፡፡ 
ግጥም ማለት እንደ ኢስላም ነው በእውነት፡፡ ሙስሊሙ ስለ ገጠመ አሸንፏል፡፡….››

‹‹ግጥም ማለት እንደ ኢስላም ነው››፡፡ 
በፍፁም አቶ ዮሃንስ የማታውቀው ውስጥ አትግባ፡፡ ያዘንክ መስለህ ሙስሊሙን አትቀስቅስ ለአደጋ፡፡
‹‹ሙስሊሙ ስለ ገጠመ አሸንፏል››
እየተደበደቡ መግባት፣ መገደል፣ መሰደድ ማሸነፍ የሆነው ባንተው ‹‹አላማዬ እስኪሳካ ሙስሊሙ ቢያልቅም.....›› በሚለው ሰይጣናዊ አካሄድህ ነውን? 
አላህ ካንተ አይነት ለሙስሊሙ አሳቢ መስለው ሙስሊሙን አስጨራሾች ሙስሊሙን ይጠብቅልን፡፡

2) ‹‹….. ሁሉ ነገር ለበጎ ነው ይባላል በእስልምና፡፡ … እንዳትቀየሙኝ አል ሃበሽን (አህባሽን) በጣም ነው የምወደው፡፡>>
 
‹‹ሁሉም ነገር ለበጎ ነው፣
ሃባሽን ጨምሮ ለበጎ ነው፣
መምጣቱ ባልከፋ በግድ መጫኑ ነው ነገሩን ያመጣ፣ 
………………………………፣
አህባሽ እንኳን ደህና መጣህ፣
ኢትዮጵያን ከፍ አድርጎ እላይ ስላወጣ፣
………………………………፣
………………………………፣
ለኢትዬጵያ ሙስሊም ወገኔ ፍዳ ለበዛበት፣
አይደለም መሰለፍ አይደለም ተክቢራ፣
ነፃነት ካስመጣ ኢትዬጵያን ካዳናት ከወረደው በላ፣
አይደለም መሰለፍ አይደለም ተክቢራ፣
አሽሀዱ ለማለት ማንንም አላፍር ማንንም አልፈረራ››

ምንጭ የራሱ የፈርስት ሂጅራ ቪድዬ

‹‹እንዳትቀየሙኝ አህባሽን በጣም ነው የምወደው›› የሚለውን የዮሀንስ ንግግር አንብቡለት፡፡ እንዲህ አይነት ፖለቲከኞች Opportunist ይባላሉ፡፡ ያለውን ሁኔታ ተጠቅመው አላማቸውን ለማስፈፀም የሚጠቀሙበት፡፡

ሙስሊሞች በአህባሽም ይሁን በሌላ ጥመት መምጣት አይደሰቱም፡፡ እውነተኛ ሙስሊሞች ጋር ሃቅ አንድ ብቻ ናት፣ እሷም የጥንቷ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና የሰሃባዎች መንደድ ናት፡፡
 
አገራችንም ላይ ትግል ከሚሉት ውስጥ ‹‹ከአህባሽ ጋር የአቂዳ (የእምነት) ልዩነት የለንም....›› የሚልም አለ፡፡

አብዛኛው ሙስሊም ሸሪዓዊ እውቀትን ሚዛን አድርጎ ስላልሆነ የሚንቀሳቀሰው እንዲህ የፖለቲከኞች፣ የቢድዐ አራማጆች መጠቀሚያ ይሆናል፡፡ አላህ የተንኮለኞችን ተንኮል የምንረዳበትን እውቀት ይስጠን፡፡

እንደ ዮሃንስ ያሉ ውጭ አገር ተቀማጭ ፖለቲከኞችን ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን (First Hijra Foundation) መድረክ እየጋበዘ ሙስሊሙ የጥይት እራት እንዲሆን ይቀሰቅሱታለታል፡፡
እስቲ እውነት ዩሃንስ ሸሃዳን የሚያክል ነገር ለመያዝ መስፈርት አድርጎ ያስቀመጠውን እንመልከት የኢትዬጵያ ሙስሊም እንቅስቃሴ ‹‹ነፃነት ካስመጣ›› ሱብሃነላህ ሙስሊሞችን ምን ያህል ሞኝ አድርጎ ቢቆጥር ነው?

ዳሩ አይፈረድበትም አሜሪካ እና ዩሮጵ የተቀመጡ በኢስላም ስም የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞች ሙስሊሙን ተክቢር እያሉ አደንዝዘውለት እሱም መድረኩን ጨርሶ ሲወርድ ‹‹ተክቢር›› ብሎ የአላህን ትልቅነት እንደመፈክር አስብሎት ወረደ፡፡
የኢትዬጵያ ሙስሊም ሆይ! እነዚህ ናቸው እንግዲህ አንተን ቀስቅሰው ወደ እሳት የሚመሩህ፡፡ በኢስላም ትክክለኛዋ መስፈርቷን ያሟላች ጀሃድ ፈፅሞ የሞተ ሰው ምንዳው ጀነት ነው፡፡ ታድያ ውጭ ተቀማጮች ይህን ተግባራቸውን ትግል እን ጀሃድ ብለው ከጠሩት ለምን ቦታው ላይ አይጣዱም፣ አይሰለፉም?

ፖለቲከኞች አይንዱህ ከዚህ በፊት ከማን ጋር ሲሰሩ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከማን ጋር ሲሰሩ እንደነበር እራሳቸውም አገርም ያውቀዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ አሜሪካ እና ውጭ ካሉ ፖለቲከኞች ጋር ሆነው አንተን የጥይት እራት ሊያስደርጉህ በሃይማኖት ስም ይጠሩሃል፡፡

እኛ ከአህባሽ ጋር የአቂዳ ልዩነት ነው ያለን፡፡ ከሱፍያም፣ ከአሽአርያም፣ ከሌላም ጋር፡፡ 

ሃቅ አንድ ብቻ ናት፡፡ የኢትዬጵያ ሙስሊም ሆይ! እራስህን ጠብቅ፡፡ 
ፈተናው የሚያልፈው ስሜትን በመከተል እና የማንም መጫወቻ በመሆን ሳይሆን፣ ዲንን በመማር፣ ዱዓ በማድረግ፣ በመታገስ፣ ወደ እውነተኛ የሱና ኡለማዎች በመጠጋት ነው፡፡
ፖለቲከኞች እና የስሜት ባለቤቶች ከከሃዲያን ጋር ሆነው የጥይት እራት ሲያደርጉህ ዝም ብለህ አትመልከት፡፡ 
ማን የማን ቅጥረኛ እንደሆነም አላህ ስለሚያውቅ ሱና ወዳጅ ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! ፍርዱን አላህ እስኪሰጠን እንታገስ፡፡
ይሀው ማንነታቸው ከራሳቸው ቪድዬ ላይ ይህን ይመስላል፡፡

አላህ ሆይ! በሁሉም ነገር ላይ ምስጋና ላንተ ነው እንዲህ አይነት ጥመትን እንዳንቀበል ልባችንን ያፀናህልን፡፡ አላህ ሆይ! የዚህ ጥመት አካሄድ ተንኮል ያልገባቸውን ወንድም እና እህቶቻችንን አንቃቸው፡፡
የአላሀ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚየ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡'
ይህ ለናሙና ያህል እንጂ በጣም ብዙ በማስረጃ የተደገፉ ማቅረብ የምንችላቸው አለን በአላህ ፈቃድ።

የአላሀ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚየ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡