Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ISIS ጥቃቱ ማን ላይ ነው ያነጣጠረው?

Sadat Kemal Abu Meryem's photo.
ISIS ጥቃቱ ማን ላይ ነው ያነጣጠረው?
በዚህች አነስተኛ ፅሁፍ ልጠቁም የምፈልገው ISIS ለስሙ ለሙስሊሞ እታገላለሁ ይላል እንጂ በመጀመሪያነት የጥቃቱ ሰለባዎች የ ISIS የጥመት አካሄድ የሚቃወሙ እና የማይቀበሉ ሙስሊሞች ናቸው፡፡
ይህንንም ስንል በማስረጃ ነው፡፡ አይደለም ተራውን ሙስሊም ማህበረሰብ በሃይማኖት እውቀታቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ለምሳሌ ሸይኽ ፈውዛንን (አላህ ይጠብቃቸው) ለማረድ መዛታቸውን ከዚህ በፊት ፖስት አድርገን ነበር፡፡ አንድ ሰው ‹‹ላኢላሃ ኢለላህ ሙሃመዱ ረሱሉላህ›› ቢልም ጥመታቸውን ካልተቀበለ ያርዱታል፡፡ ይሄ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹የጀሃነም (የገሃነም እሳት) ውሻዎች›› ብለው የሰየሟቸው የኸዋሪጆች ባህሪ ነው፡፡
ከዚሁ በፊትም እንዚህ አረመኔዎች ከእስልምና ማዕዘናት አንዱ የሆነውን ሃጅ ለመፈፀም የአለም ህዝብ ወደ ሳውዲ ሙስሊሞች በሚሄዱበት ወቅት ጥቃት እንደሚፈፅም መግለፁን ፖስት አድርገናል፡፡
ነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል እያሉ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ንግግር ለጥመታቸው ጠምዘዝው እና አጣመው ቢያወሩትም የሚከተለው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምሮት እዚህ ተግባር ላይ የተሰማራን አደለም ገነት (ጀነት) ሊወርስ ሽታዋን እንደማያሸት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል
ኢማም ቡኻሪ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:–
« ﻣَﻦْ ﻗَﺘَﻞَ ﻣُﻌَﺎﻫَﺪًﺍ ﻟَﻢْ ﻳَﺮِﺡْ ﺭَﺍﺋِﺤَﺔَ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔِ ، ﻭَﺇِﻥَّ ﺭِﻳﺤَﻬَﺎ ﺗُﻮﺟَﺪُ ﻣِﻦْ ﻣَﺴِﻴﺮَﺓِ ﺃَﺭْﺑَﻌِﻴﻦَ ﻋَﺎﻣًﺎ »
[ ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ]
" አልሙዓሂድ (በቃል ኪዳን በቪዛ በስራ ምክንያት ሙስሊም ሀገር የሚኖር) ሰውን የገደለ የጀነትን ሽታ አያገኝም። ሽታዋ አርባ ዓመት የሚያስኬድ መንገድ ሲቀረው ይገኛል።"
ልብ በሉ የሰሞኑ የ ISIS ተግባር ጀነት ሊያስገባ ቀርቶ አርባ ዓመት የሚያስኬድ መንገድ ሲቀረው የሚገኘው የጀነት ሽታ እንኳ አያስገኝም።
የሚከተለው ፒክቸር የ ISIS አባል ታላቁን የሃይማኖት አስተማሪ ሸይኽ ፈውዛንን አንገት ሳውዲን ተቆጣጥረው እንደሚቀላ በትዌተር አካውንቱ ላይ የፃፈው ነበር፡፡
አረ በጣም ብዙ መጥቀስ ይቻላል…. ግን ለአእምሮ ባለቤቶች ጥቂት በቂ ነው፡፡ ምስጋና ለአለማት ጌታ የተገባ ይሁን ኡለማዎቻችን ISIS ይሁን አል-ቃኢዳ መንገድ የሳቱ ቡድኖች መሆናቸውን ብቅ ሲሉ ገና ነበር ያስተማሩት፡፡ አላህንም እናመሰግነዋለን እነዚህን መጥፎ መንገዶች መጥፎ መንገድ መሆናቸውን ላሳወቀን፣ ትክክለኛዋንም መንገድ ለመራን፡፡
ይህ ነው የ ISIS እውነታ፡፡
ጥቂት ትዝብቶች ስለ ISIS
- ማን ነው እንዲህ አይነት ዩኒፎርም እና መሳርያ ያስታጠቃቸው?
- እንማን ናቸው ይህን አይነት መሳርያ የሚሸጡላቸው?
- ለምንስ ፊታቸውን መሸፈን አስፈለጋቸው?
- ጥርት ያለችዋ እንግሊዝኛ መፈክር እና ማስፈራርያቸው……
መቼም ሁሉም ከእርሱ የማይደበቀው አላህ በመያዣው ይያዛቸው፡፡

Post a Comment

0 Comments