Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ISIS ን ስናወግዝ...

‎Al-wasatiyah   الوسطية والإعتدال  ሚዛናዊ   አቋም‎'s photo.
ISIS ን ስናወግዝ...
www.fb.com/wesetiya
በቅድሚያ የISIS ጥፋትና ጭካኔ ለኛ ሙስሊሞች አዲስ አይደለም፤ ISISሶች በኢስላም ታሪክ ውስጥ መጥፎ አሻራን ያኖሩትና ሙስሊሙን በማወክ ጥቁር ጠባሳ የተውትን የ'ኸዋሪጆች' ርእዮት የወረሱ ርዝራዦቻቸው መሆናቸውን ፍፁም አንጠራጠርም።
ኸዋሪጆች ከመልእክተኛው ሙሐመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ �ወሰለም) በኋላ የመጡ እጅግ አረመኔ ቡድኖች ሲሆኑ መልእክተኛው ቀደም ብለው ከእነኝህ አንጃዎች እና እሳቤያቸው አስጠንቅቀውናል።
قال الإمام أحمد :
الخوارج قوم سوء لا أعلم في الأرض قوما شرا منهم وقال : صح الحديث فيهم عن النبي ومن عشرة وجوه .
السنة للخلال ١٤٥/١
ታላቁ ዓሊም(የኢስላም ምሁር) ኢማሙ አህመድ እንዲህ ብለዋል ፦
«ኸዋሪጆች መጥፎ ሰዎች ናቸው! በምድር ላይ ከነሱ የባሰ እርኩስ አላውቅም!!»
በሌላ ንግግራቸውም...
«እነሱን በተመለከተ (ቡድኑን የሚኮንኑ) ከመልእክተኛው በአስር መንገዶች የተላለፉ ትክክለኛ ዘገባዎች ተገኝተዋል» አል ኸላል 1/145
ነቢዩ ሙሐመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ �ወሰለም) እንደተነበዩት ብዙም ከሳቸው ህልፈት ሳይርቅ እነዚህ ጨካኝ ሰዎች የመጡ ሲሆን በወቅቱ የነብዩ ባልደረቦች የነበሩትን ሰሀባዎችን ተጋድለዋል፤ አራተኛውን ኸሊፋ ዓሊ ቢን አቡ-ጧሊብንም በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል።
በአሁን ሰአት የሚገኙትም እንደ ISIS አይነትና መሰል ቡድኖች ከዚሁ አረመኔ(ኸዋሪጅ) ቡድን እንደሚመደቡ በዘመናችን የሚገኙ የኢስላም ምሁራን ተናግረዋል።
ወደ ርእሳችን ስንመለስ እኛ ሙስሊሞች ISIS ን ስናወግዝ... ISIS የሚፈፅማቸው ተግባራት በእጅጉ የሚወገዙ መሆናቸውን በመረዳት ሲሆን ነገር ግን የምናወግዘው ዲናዊ ወሰኖችን ሳንጥስ፣ ለርካሽ አላማዎችም ፍጆታ ሳንሆን፣ መነሻችንን ዲናዊ ብቻ አድርገን ነው።
ከዚህ ጋር ልናስተውላቸው የሚገቡ ነገሮች
1) ISISን የምናወግዘው ሱናን በመፃረሩ፣ የሱና ሰዎችን ጠላት አድርጎ በመጨፍጨፉ፣ ሙስሊሞችን በማክፈሩ፣ ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት ድንበር በማለፉና የኢስላምን ስም በማጠልሸቱ ነው።
‪#‎ወገኖቻችን‬ ላይ የፈፀመውን ጥቃት የምናወግዘው ከጠንካራ ዲናዊ መነሻ እንጂ ማንንም ለማስደሰት አይደለም።
2) ከሌሎች ወገኖች ጋር ድርጊቱን ለማውገዝ ስንነሳ ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮች አሉ። ከከፎሎቹ ጋር isis ን የምናወግዝበት ምክኒያት እና መነሻ የተለያየ ነውና ጥንቃቄው ሊበረታ ይገባል። በተደጋጋሚ እንደታየው ፀረ-ኢስላም ተልእኮ ያነገቡ ሰርጎ ገቦች ይህን መሰል ተቀውሞዎችን ለተልእኳቸው ማስፈፀሚያ ምቹ አጋጣሚ በማድረግ ኢስላምና ሙስሊሞችን ያጥላላሉ።
ለአብነት ያክል ፈረንሳይ ውስጥ የተደረገውን ሰልፍ ማስታወስ በቂ ነው። በሀገራችንም ቢሆን በአረብ ሀገራት ተፈፀመ የተባለው በደል ለማውገዝ የተጠሩ አንዳነድ ሰልፎች ፀረ ኢስላም እንደነበሩ ሁላችንም አስተውለናል። እንዲህ አይነት መድረኮች ላይ ከአላህ ጠላቶች ጋር ማበር እጅግ ከባድ ዝቅጠት ነው። አላህም ይህ አይነቱን ስብስብ ከመቀላቀል ከልክሎናል።
( وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آَيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّى يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ ) النساء/140 .
{በመጽሐፉ ውስጥ፤ «የአላህ አንቀጾች በነሱ ሲካድባቸውና ሲላገጥባቸው በሰማችሁ ጊዜ፤በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከነርሱ ጋር አትቀመጡ» ማለትን በእናንተ ላይ በእርግጥ አወረደ! እናንተ ያን ጊዜ ቢጤያቸው ናችሁ፤ አላህ መናፍቃንን እና ከሐዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና (ተጠንቀቁ!)} ኒሳእ 140
3) ሀዘን ለማንፀባረቅ ሲባል የሚፈፀሙ ስህተቶችንም መጥቀሳችን የግድ ነው።
✘ ጥቁር ሳምንት የሚለውን መጠቀም፤ ጊዜን በመጥፎ መጥራትና መስደብ ነውና በዲናችን ክልክል ነው።
عن أبي هريرة رضى الله عنه:
عن النبي صلى الله عليه وسلم قال؛
قال الله تعالى:- «يؤذيني ابن آدم، يسب الدهر وأنا الدهر، أقلب الليل والنهار.» [رواه البخاري ومسلم]
አቡ ሁረይራ እንደተናገሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:–
"የበላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል ፦ «የአደም ልጅ ያውከኛል ፣ ጊዜን ይሰድባል! ጊዜ ራሱ እኔ ነኝ! (የክስተቶች ውሳኔ ከኔ ነው) ፣ ለሊትና ቀንን እለዋውጣለሁ» [ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል]
✘ ጥቁርን ቀለም ለሀዘን መግለጫነት መጠቀም የኛ የሙስሊሞቹ ስርአት አይደለም። ለሀዘን ሲባል ፕሮፋይልንም ይሁን ልብስን ማጥቆር አይፈቀድልንም።
قال الشيخ عثيمين
"لبس السواد حداداً على الميت من البدع وإظهار الحزن ، وهو شبيه بشق الجيوب ولطم الخدود الذي تبرأ النبي صلى الله عليه وسلم من فاعله حيث قال : ( ليس منا من شق الجيوب، ولطم الخدود، ودعا بدعوى الجاهلية)" اهـ . مجموع الفتاوى 17/41
ሸይኽ ዑሰይሚን እንዲህ ብለዋል
"በሟች በማዘን ጥቁር መልበስ ከቢድዓ እና ሀዘንን ይፋ ከማድረግ ነው፤ ይህን ማድረግ ልክ በሀዘን ልብስን እንደመቅደድ፣ ጉንጭን እንደመምታት የሚቆጠር ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት ይህንን ከሚሰራ ሰው የጠሩ መሆናቸውን ተናገሩባቸዋል፤
"(በሀዘን ምክንያት) ልብሱን የቀደደ፣ ጉንጩን የመታና በጃሂሊያ ጥሪ (ዋይታ) የተጣራ ከኛ አይደለም" )) መጅሙዕ አልፈታዋ 17/41
✘ ኢስላም ማህበራዊ ስርአታችንን ቀርፆልናል። ሀዘንን ሙሾ በማውረድ መግለፅ ቅድመ ኢስላም የነበሩ የጃሂሊያ ስርአቶች ቅሪት ነውና በዲናችን ተከልክለናል።
عن أبي مالك الأشعري رضى الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:–"أربع في أمتى من أمر الجاهلية لا يتركونهن: الفخر بالأحساب، والطعن في الأنساب، والأستسقاء بالنجوم، والنياحة على الميت." (رواه مسلم)
አቡ ማሊክ አል-አሽዐሪይ (ረድየላሁዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሠለላሁ ዓለይሂ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል :-
«ከተከታዮቼ ውስጥ ከቅድመ ኢስላም ከጃሂሊያ ዘመን የተወረሱ የማይላቀቋቸው አራት ልምዶች አሉ፦ እነርሡም:- በዘር መኩራራት፣ የሌሎችን ዘር (ብሄር) ማንቋሸሽ፣ በከዋክብት ዝናብ መሻትና በሟች ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።» ሙስሊም ዘግበውታል
✘ ሙስሊም ያላልሆኑ ሰዎችን ስናፅናና ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን መመኘትና በጥሩ ቃላት ማፅናናት ችግር ባይኖረውም ለሟቾች ጀነትን መለመንና 'ነብስ ይማር' ማለት ግን አይፈቀድልንም።
«ﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﻟِﻠﻨَّﺒِﻲِّ ﻭَاﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮا ﺃَﻥ ﻳَﺴْﺘَﻐْﻔِﺮُﻭا ﻟِﻠْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ ﻭَﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮا ﺃُﻭﻟِﻲ ﻗُﺮْﺑَﻰٰ ﻣِﻦ ﺑَﻌْﺪِ ﻣَﺎ ﺗَﺒَﻴَّﻦَ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﻧَّﻬُﻢْ ﺃَﺻْﺤَﺎﺏُ اﻟْﺠَﺤِﻴﻢِ» التوبة 113
«ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢኾኑም እንኳ እነሱ የእሳት ጓዶች መኾናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ነቢዩና እነዚያ ያመኑት፤ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም» አል ተውባህ 113
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "استأذنت ربي أن أستغفر لأمي؛ فلم يأذن لي" رواه مسلم
አቡ ሁረይራ ባወሩት ሐዲስ ነቢዩ (ሠለላሁ ዓለይሂ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል "ለእናቴ ምህረት እንድለምንላት ጌታዬን አስፈቀድኩት ነገርግን አልፈቀድለኝም" ሙስሊም ዘግበውታል
እንግዲህ ነቢዩ (ሠለላሁ ዓለይሂ ወሠለም) ለእናታቸው ምህረትን እንዳይለምኑ ከተከለከሉ ቀሪው ህዝብ እንደማይፈቅድለት ግልፅ ነው።
ذكر جمع من فقهاء المذاهب الأربعة تحريم الدعاء للكافر الميت، انظر مثلا: المحيط البرهاني 2/184 في فقه الحنفية، والبيان والتحصيل 2/211 في فقه المالكية، والبيان 3/25 في فقه الشافعية، وشرح المنتهى 2/160 في فقه الحنابلة،
ከአራቱም መዝሀቦች የፊቅህ ጠበብቶች እንደተገኘው፦ "ሙስሊም ላልሆነ ሰው ምህረትን መለመን ሀራም መሆኑን ጠቅሰዋል" ለምሳሌ ... በሀነፊያ አል ሙሂጥ አልቡርሀኒ 2/184 በማሊኪያ አልበያን ወተህሲል 2/211 ተመልከት
በሻፊዒያ አል-በያን 3/25 ተመልከት እንዲሁም ሐንበሊያ ሸርሁል ሙንተሀ 2/160 ላይ ተመልከት
نقل بعض العلماء الإجماع على ذلك، منهم الإمام ابن تيمية، قال: "الاستغفار للكفار لا يجوز بالكتاب والسنة والإجماع". مجموع الفتاوى 12/489.
ብዙዎችም የሙስሊም ሊቃውንቶችን ስምምነት (ኢጅማዕ)ጠቅሰዋል። ከነርሱም መካከል አል-ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል «ለካፊሮች ምህረትን መለመን እንደማይፈቀድ ቁርአናዊ፣ ሀዲሳዊና የኢጅማዕ መረጃዎች አሉ» መጅሙኡል ፈታዋ ቅፅ 12 ገፅ 489
4) ሙእሚኖች እንደ አንድ አካል ናቸውና ብዙ የእምነት ወንድሞቻችን በተመሳሳይ መልኩ ወይም ከዚህ በከፋ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሲያልቁ ተመሳሳይ ውግዘት ማሰማት ይጠበቅብን ነበር።
ጥፋትን ልናወግዝ የሚገባው ከፈፃሚው አንፃር ወይም ጥፋቱ የተፈፀመው በኛ ዜጋ ላይ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በጥፋትነቱ ብቻ ነው ። ስለዚህ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችንም ለሀቅ እንዲቆሙ መምከር፤ በሙስሊሞች ላይ የሚፈፀሙ ሁሉንም አይነት ክፋቶች እንዲያወግዙ መምከርም ተገቢ ነው።
ወልሀምዱሊላሂ ረቢልአለሚን
አልወሰጢያ ወል ኢዕቲዳል
www.fb.com/wesetiya

Post a Comment

0 Comments