Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአፄ ዮሐንስ ስራ ክርስትናን እንደማይወክለው ሁሉ የIS ሽብርም ፍፁም ኢስላምን አይወክልም!

Mohammed Ibrahim Ali's photo.
የአፄ ዮሐንስ ስራ ክርስትናን እንደማይወክለው ሁሉ የIS ሽብርም ፍፁም ኢስላምን አይወክልም!
እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ1886 ነበር:: በእንግሊዞች ድጋፍ በትረ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ብዙም ያልቆየው አጼ ዩሀንስ(በዝብዝ ካሳ) በወሎና አካባቢው የሚገኙ የእምነት አባቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን "ቦሩ ሜዳ" በምትባለው የወሎ ግዛት እንዲገኙ ሲሉ አዋጅ ያስነገረው::
የአካባቢው ማህበረሰብም (በአብዘሀኛው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች) አዋጁን በማክበር ከቦታው ተገኙ:: በቦታው ከተገኙ በዃላ ግን ነገሩን እንደጠበቁት አልላገኙም::
አፄው ቀጠን ያለ ትዛዝ አስተላለፈ "ከዛሬ ጀምሮ የክርስትና እምነትን ትቀበላላቹ ... አይ የሚል ካለ በሂወት ወደ ቤቱ እንደማይመለስ ሊያውቅ ይገባል!!" በአፄው ትዛዝ በጣም ግራ የተጋቡት ሙስሊሞች የሰሙትን ነገር ማመን ከበዳቸው አፄውም ለሁለተኛና ለመጨረሻ ግዜ የቀድሞውን ትዛዝ አስተላለፈ፤ ሙስሊሞቹም ፈጽሞ ሀይማኖታቸውን ሊቀይሩ እንደማይችሉ ለአፄው አስረግጠው ነገሩት::
በዚ ሰአት ነበር እንኳን ለማድረግ ለማሰብ የሚከብደው ጭካኔ የተሞላበት ትዛዝ ከአፄው አንደበት የወጣው:: አፄው በቦሩ ሜዳ ከተሰበሰቡት ሙስሊሞች አንድም ሰው በህይወት እንዳይተርፍ ሲል ለጦር መሪው አዘዘ::
ቦርቀው ያልጠገቡ ህፃናት፣ አዛውንቶችንና እናቶችን ጨምሮ ከ20,000 በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች በገዛ ወገኖቻቸው ጎራዴ አንገታቸው ተቀላ:: ለማምለጥ የሞከሩት ደግሞ ተይዘው ሁለት መዳፋቸው ተቆርጦ በአንገታቸው ላይ እንዲጠለጠል ተደረገ::
የወሎ ምድር በሀዘን ተዋጠች!! ይሄን ሁሉ እልቂት ያደረሰውን አጼ ዮሀንስ(በዝብዝ ካሳ) ግን በቤተክርስቲያን ነበር ተቀብቶ ነበር የነገሰው። ይህንንም ታሪክ የማይዘነጋው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሲያደርግ አንድ ሀይማኖትን(ክርስትናን) በኢትዮጵያ አሰፍናለሁ በሚል አላማ ነበር። ነገር ግን ይህ ግለሰብ ለሰራው ጥፋት ክርስትና ተጠያቂ አልተደረገም::
በአሁኑ ሰአትም ISIS የተሰኘው አለም አቀፍ የሽብር ቡድን በእስልምና ስም ለሚያደርሳቸው ማናቸውም አይነት ጥፋቶች እስልምና ሊወቀስ አይገባም:: ISIS ለፈጸማቸው እልቂቶች እስልምናን ተጠያቂ ነው ካልን አጼ ዮሀንስ(በዝብዝ ካሳ) ላደረሰው እልቂት
ክርስትናም ተጠያቂ ነው ልንል ነው?
በዚህ ቡድን (ISIS) ሰበብ አጋጣሚውን ተጠቅመው የቆየ የልብ ጥላቻቸውን በኢስላም ላይ እና በሙስሊሞች ላይ ለመዝራት የሚፈልጉም ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡና ሀገራችን በመቻቻል ዘልቃ የቆየችበትን ባህል ከመሸርሸር ሊታቀቡ ይገባል!!
ኢስላም የሰላም ሃይማኖት ነው፡፡ የኢስላምን ስም ይዘው ከኢስላም ውጪ የሆነ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት እራሳቸውን እንጂ ኢስላምን አይወክሉም፡፡
በድርጊታቸውም የሚወገዙት እነርሱ እንጂ የተጠለሉበት ኢስላም አይደለም፡፡ ለችግሮቻችን የጋራ መፍትሄ መፈለግ ሲገባን እርስ በርስ መናቆር ተገቢ አይደለም፡፡
አላህ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትንና ትግስትን ይለግሳቸው፡፡ ሃገራችንንም ሰላም ያድርጋት ዘንድ እንለምናለን፡፡
የኢስላም አስተምህሮ የሆኑት (ቅዱስ ቁርኣንና ሀዲስ ) ብቻ ናቸው እኛን የሚወክሉት፡፡ ኢስላምን በአግባቡ መረዳት የሚፈልግ ሰው ሙስሊሞችን ከማጥናቱ በፊት እነዚህን መረጃዎች ያንብብ!!

Post a Comment

1 Comments

  1. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete