Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አስገራሚው የኢስላም አሸናፊነት እና ውበት

Sadat Kemal Abu Meryem's photo.
አስገራሚው የኢስላም አሸናፊነት እና ውበት
አላህ ሆይ! ጥራቻ ይገባህ መልክተኛህን ነብዩ ሙሓመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በቅናቻ እና እውነተኛ በሆነ ሃይማኖት ከሃይማኖቶች ሁሉ የበላይ ልታደርገው የላክ፡፡
እየተከሰተ ያለው የምናየው ነገር ለአማኞች በአላህ ላይ መመካታቸው የሚጨምር ነው፡፡ ኢስላምን የውጭም የውስጥም ጠላቶች ገዝግዘው ሊጥሉት ቢሞክሩም የላከው እና የተወረደው ከአላህ ስለሆነ አሸናፊነቱን እየተቀናጀ ቀጥሏል፡፡ ከውጭ ሆነው ኢስላምን መታገል አላዋጣቸው ሲል በሽርክ መንዙማ ህዝቡን የሚያጠሙትን እነ ፈረንሳይ ‹‹የመንዙማ ኮንሰርት›› እያሉ ሙስሊሙን ከእምነት ወደ ክህደት ሊወስዱት (አማርኛ፣ ጉራግኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሃደሪኛ እያሉ መንዙማ ኮንሰርት ቢያዘጋጁም) መንገዱን ቢያመቻቹለትም አላህ በተውሂድ ተጣሪዎች ሰበብ ህዝቡን እያነቃው ነው ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ይሁን፡፡ የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ሆይ እስቲ አስቡት ፈረንሳይ የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ አሳስቧት ነው የሽርክ መንዙማ ሲያቀነቅኑ የምናውቃቸውን ሰዎች ገንዘብ መድባ ኮንሰርት የምታዘጋጀው? በፍፁም፡፡
በሌላ በኩል ሙስሊም አረብ አገራት ላይ ያለውን ሃብት ለመዝረፍ እና ሙስሊሞች በመሪዎቻቸው ስር እንዳይተዳደሩ ብሎም ህውከት አስነስተው እርስ በርስ እንዲተራረዱ በር የሚከፍቱላቸውን ተቃዋሚ ኸዋሪጆች በማሰልጠን ያዘጋጃሉ፡፡ ከዛም አልፎ ሰላማዊ ጥቂት ክርስትያኖችን የሚገድሉ ፅንፈኛ ቡድኖችን መሳርያ በማስታጠቅ፣ በማሰልጠን ያዘጋጁዋቸው እና ከዛም የሙስሊሞችን ንብረት ለመዝረፍ፣ የኢስላምን ስም ለማጥፋት፣ ብሎም እነዛ ወሮበላ ፅንፈኞች በሰሩት ንፁሃኑን ሙስሊም አሁንም ለመግደል፣ እና አገሩን ለመውረር ሰበብ ሲሆን ይታያል፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ አሁንም ኢስላም እያደገ፤ በምዕራብም በምስራቅም ሰዎች የነብያት ሁሉ ሃይማኖት የሆነውን ኢስላም ውበት እየተረዱ እየጎረፉ ሲገቡ ይታያል፡፡
ምዕራባዊያን ሽርክ የሚሰሩ አህባሾችን፣ ሱፍዬችን ሲያበረታቱ ትመለከታለህ፡፡ እንደ አልቃኢዳ፣ አይኤስ ካሉ ኸዋሪጆች ጋር ጠላት ቢመስሉም መሳርያ በማስታጠቅ እነዚሁኑ ቡድኖች በመርዳት አብረው የሚንቀሳቀሱባቸውን ጊዜያትም ተገንዝበናል፡፡
ኢስላም አላህ ጠባቂው የሆነ የበላይ አድርጎ የላከው የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ነው፡፡ ጠላቶች የለፉትን ያህል ቢለፉ አላህ ይጠብቀዋል፡፡