Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በፌስቡክ የሚተላለፍ አደገኛ ቫይረስ!!

በፌስቡክ የሚተላለፍ አደገኛ ቫይረስ!!
በሞባይልም ይሁን በኮምፒተር ፌስቡክ ለምትጠቀሙ ሁሉ!!!
የፌስቡክ ተጠቃሚ ቁጥር ከእለት ወደለት እጅግ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚም እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ያለ ክፉ ቫይረስ አለ፡፡ ይቅርታ ምናልባት አካላዊ ጤናን ስለሚጎዳው ቫይረስ ወይም ስለኮምፒተር ቫይረስ ያሰበ ካለ እሱ አይደለም ርእሴ፡፡ እርግጥ ነው አካላችንን ወይም ኮምፒተራችንን ስለሚጎዳው ቫይረስ የተሻለ ግንዛቤ የተሻለ ጥንቃቄም አለን፡፡ ኢማናችንን ስለሚያጠቃው ቫይረስስ ምን ያህል እናውቃለን ምን ያህልስ እንጠነቀቃለን አላህ ከሃዲዎችን ((ከቅርቢቷ ህይወት(ከዱንያ) ግልፁን ብቻ ያውቃሉ፡፡እነርሱ ግን ከወዳኛዋ ህይወት(አኺራ) የዘነጉ ናቸው)) ይላል፡፡ እኛ ስለየትኛው ህይወት ነው የተሻለ እውቀት የተሻለ ጥንቃቄ ያለን
ቀጥታ ወደ ርእሴ ልግባ፡፡
ውሸት
ውሸት ቆሻሻ ቫይረስ ነው፡፡ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውሸትን ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ ቆጥረውታል፡፡ ኧረ እንዳውም “ሙስሊም አይዋሽም” ሲሉ ቀይ መስመር አስምረዋል!!! ቁርኣናችንም ((እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፣ ከእውነተኞቹም ሁኑ)) ይለናል፡፡
እና ፌስቡክ ምን አጠፋ አትሉኝም ፌስቡክ ከፍተኛ የውሸት ምርት እየተመረተበት ነው፡፡ እናም ፌስቡክ የውሸት አውድማ፣ ፌስቡክ የውሸት መጋዘን፣ ፌስቡክ የውሸት ማጓጓዣ ሆኗል!!! አፍወን .. የሆነ ሹክሹክታ እንዳይሰማ ሰጋሁ፡፡ “እናም ፌስቡክ ሐራም ነው” በለንና እረፍ የሚል፡፡ ኧረ እኔ አልወጣኝም!!! እኔ እያልኩ ያለሁት እውነት እንናገር ከእውነተኞቹም እንሁን ነው፡፡ በቃ!! እኔ እያልኩ ያለሁት ኢቲቪን ከለከፈው በሽታ ከውሸት እንራቅ ነው፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት እውነት ይሁን ውሸት መሆኑን ያልለየነውን ወሬ ከማመን፣ ከማውራት፣ ከማሰራጨት እንቆጠብ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እውነት ይሁን ውሸት ምንም ፍንጩ የሌለንን ነገር ፌስቡክ ላይ ስላገኘነው ብቻ “እንዲህ ተከሰተ”፣ “እንዲህ ሆነ” ብለን ማውራታችን አላህ ዘንድ ያስጠይቀናል ነው፡፡ “መረጃ” አትሉኝም አዎ ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው ዲናችን ደግሞ የመረጃ ዲን፡፡ ይሄውና መረጃዬ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉናል፡፡
- (አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ “ውሸታም” ለመባል በቂው ነው) (አሶሒሓ፡ 2/440)
- (አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ወንጀለኛ ለመሆን በቂው ነው) (ተማሙል ሚናህ፡ 33)