Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እስፖንጅ የያዘውን ነው የሚተፋው አነጋጋሪ ወሬዎች ከወደ አሕባሽ መንደር

እስፖንጅ የያዘውን ነው የሚተፋው
አነጋጋሪ ወሬዎች ከወደ አሕባሽ መንደር
1. “አላህ ካፊርን እንዲከፍር ባያግዘው ኖሮ አይከፍርም ነበር፡፡” ከአብደላህ አልሀረሪ (አነህጁሰሊም) ኪታብ የተወሰደ፡፡
ባይመልሱም እንጠይቃቸው፡- አላህ ካፊርን በኩፍሩ ላይ ከረዳው እንዲሁም ባይረዳው ኖሮ መክፈር የማይችል ከሆነ ለምን በኩፍሩ ይቀጣዋል ይሄ አቋማቸው ከአደገኛው የጀበርያ ቡድን ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡
2. ሸይኻቸው ዐብደላህ አልሀረሪ እንደሙዓውያና ዐምር ኢብኑል ዓስ ያሉትን ሶሃቦች ማውገዝ ይቻላል ይላል፡፡ (ሶሪሁል በያንና ኢዝሃሩል ዐቂደቱሱኒያ) ኪታቦቹን ይመልከቱ፡፡ ነብዩ ዐለይሂሰላም እንዲህ ይላሉ፡ (ሶሃቦቼን የተሳደበ የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁን)
3. አህባሾች ከሞተ ሰው ይለምናሉ መለመንን ይፈቅዳሉ! (ቡግየቱጧሊብ፡ 8፤ ሶሪሑልበያን፡ 57-58፤ አደሊሉል ቀዊም፡ 173) ይመልከቱ፡፡
4. አህባሾች ከድንጋይ በረካ ይፈልጋሉ!!(ሶሪሑልበያን፡ 58፤ ኢዝሃሩል ዐቂደቲሱኒያህ፡ 244) “ምን አይነት ድንጋዮች ናቸው” እንዳትሉ ፈራሁ፡፡ ካላችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ለምን ቢባል ድንጋይ እራሱ ይሄን ስህተት አይሰራምና መስደቢያ ልናደርገው አይገባም፡፡
5. ዐብደላህ አልሀረሪ፡ ሒጃብ የሰውነትን ቀለምና ፀጉርን ከሸፈነ ይበቃል ብሏል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 104(አዲሱ እትም፡137))፤ ተማሪው ኒዛር ሐለቢ፡ ሴቶች ወጣቶቻችን በጂንስ ይዋባሉ፤ ምክኒያቱም እኛ ሰውነትን መሸፈንም ፋሺን መከተልም በተመሳሳይ ጊዜ እናስገኛለን ብሏል(አልሙስሊሙን ጋዜጣ ቁጥር፡407፣ 1992)፤ ሴት ሽቶ ተቀብታ መውጣቷን ፈቅዷል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 351(አዲሱ እትም፡446))
6. ዐብደላህ አልሀረሪ፡ ከአጅነቢይ ጋር በእጆቻቸው መካከል የሚለይ ነገር አድርጎ መጨባበጥን ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 144)፤ የሴቶችና የወንዶችን መቀላቀል ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 178-179)፤ በስሜት ካልሆነ ሴትን ለረጅም ጊዜም ቢሆን መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡224፣287፣288(አዲሱ እትም፡280፣266፣267)) እሷ ቲቪ አይደለች ለምንድን ነው ረጂም ጊዜ የሚያፈጠው ቤተሰብ ከሆነች ደግሞ ከእንብርት እስከ ጉልበት ካለው ውጭ መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡290(አዲሱ እትም ላይ ግን አውጥቶታል)፤ ወንድ ወይም ሴት መሆኑ ከማይለይ ፍናፍንት ጋር በረመዷን ግንኙነት ማድረግ ፆም አያበላሽም(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 192(አዲሱ እትም፡243))፤ ብልት ከተሸፈነ በፓንት ሶላት መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 139)
7. የአለምን ቅርፅ በተመለከተ አለምን ያስደመመ ማለቴ ያንከተከተ አዲስ ግኝት አግኝተው ቂብላ ሊቀይሩ ተውተርትረዋል፡፡
8. አንድ በርሜል ውሃ ውስጥ አንዲት ፀጉር ብቻ በመክተትና በመርጨት ለበርካቶች ፈውስ ሊሰጡ “ፀበል” ሲረጩ ነበር፡፡
9. ሸይኻቸው በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል ይላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99-100(አዲሱ እትም፡131-132))፡፡ የትኋንና የቅማል ደም ግን ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው ይላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119))፣ ኢስቲንጃን ከውዱእ በኋላ ማድረግ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡134) ይላል፡፡ “ታጥቦ ጭቃ አሉ” እማማ እንትና፡፡
10. ከወረቀት የብር ኖት ዘካ የለም(ቡግየቱ ጧሊብ፡160፣ 169(አዲሱ እትም፡207)) ይላል፡፡
11. ዐብደላህ አልሀረሪ በርካታ የሙስሊም ምሁራንን በእውር ድንብር ያከፍራል፡፡ የሚገርመው ግን ለማክፈርም ያዳላል፡፡ በተመሳሳይ ነጥብ አንዱን አውግዞ ሌላውን ያልፋል፡፡ ለነገሩ ከአህባሽ የማይጠበቅ ነገር የለም፡፡ “የምታየው ሁሉ አላህ ነው”፣ “ባሪያው ጌታ ነው ጌታው ባሪያ ነው፣ ማነው አስገዳጁ ማነው ተገዳጁ” እያለ በኩፍር ለሚኮፈሰው ኢብኑ ዐረቢ የሚሟገተው ዐብደላህ አልሀረሪ ኢማሙ ዘህቢን “ቆሻሻ” ይላል፤ ኢብኑ ተይሚያን፣ ዳሪሚይን፣ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብን፣ አልባኒን… ያከፍራል፡፡
12. መስከረም(?) ላይ የታተመው የኢትዮጵያ እስልምና ገዳይ (መጁሰል አዕላ) ልሳን የሆነው “ነጃሺ” መፅሄት (“ጃ”ን ጠበቅ ያርጓት) ከአራቱ መዝሀቦች ተከታዮች ውጭ ሙስሊም እንደሌለ አስፍሯል፡፡ ከነዚህም ውስጥ “አላህ ከዐርሹ በላይ ነው” የሚሉ፣ ለኢብኑ ተይሚያ … የሚከላከሉ ይቀነሳሉ፡፡
13. የካፊርን ገንዘብ መስረቅ(ካሴት ቁጥር፡2)፣ በቁማር መብላት ይቻላል(ሶሪሑል በያን፡133-134) ይላሉ፡፡
.
.
.
እንዴ ይሄ ሁሉ ማፈንገጥ ለምን ሰዎቹ የሚፈልጉት በልዩነት መታወቅ ነው እንዴ ሊባል ይችላል፡፡ እናንተ የተረዳችሁትን በሉ፡፡ እኔ ግን የተረዳሁት ይሄ ነው፡፡ ሰዎቹ ያላቸውን የሚያምኑበትን ነው የተናገሩት የፃፉትም፡፡ እናም ያላቸውን አቅርበዋል፡፡ “እስፖንጅ የያዘውን ነው የሚተፋው” ይባላል፡፡ አተላ ያዘለን እስፖንጅ ወተት እየጠበቀ የሚጨምቅ የለም፡፡ እኛንም እነሱንም አላህ ሂዳያ ይስጠን፡፡ ሂዳያ ሂዳያ የሚለው ቃል አንድ ነገር አስታወሰኝ፡፡ በቅርቡ አንድ የታወቀ facebooker “ሂዳያ ይስጥህ” ማለትን ከማክፈር የመነጨ ዱዐ አድርጎት “ጃሎ” ሲል ነበር፡፡ ቆይ እኔ እምለው ቢያንስ በቀን 17 ጊዜ “ኢህዲነሲራጦልሙስተቂም” እያለ ፋቲሐን የሚቀራ ሰው እንዲህ ብሎ ይናገራል እንዴ ሱብሐነላህ! ኧረ ለሁላችንም አላህ ሂዳያ ይስጠን፡፡