Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“ተውሒድ፡ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ” የሚለው መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ!!



አስደሳች ዜና ለመላው ሙስሊም ማሕበረሰብ
አሰላሙዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱ  ውድ ውንድሞቼና እሕቶቼ
አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ አክበር
በድንቅ ፅሁፎቹ የምናውቀው እና በሱና ብርሐን ድረ ገፅ ትምሕርት ቤት አስተማሪነቱ ሁላችንም የምናውቀው ወንድማችን እና ውዱ መካሪያችን Ibnu Munewor (ሙሐምድ አሕምድ ሙነወር) አላህ ይጠብቀው ይህን ተውሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ነው የተሰኘ መፅሃፍ አዘጋጅቶ ለመላው የኢትዮ ሙስሊም ማሕበረሰብ ለንባብ አቅርቧል ። አልሃምዱሊላህ
ዉድ ወንድሞቼና እሕቶቼ የወንድማችን ኢብኑ ሙነውር ሃፊዘሁላህ አዲስ መፅሃፍ የትርጉም ስራ ሳይሆን ጊዜውን ለ አላህ ሲል ሰውቶ ያዘጋጀውና ለሙስሊሙ ማሕበረሰብ ያቀረብው የመጀመሪያ ስራው ነው ።
እኛም ከዚህ በኃዋላም ብዙ ዐቂዳ ተኮር ስራዎችን ከሱ የምንጠብቅ ነንና ለ አላህ እንዲህ ስንል ዱዐ እናደርግለታለን
አላህ ሆይ ኢኽላስን ለግሰው
ብዕሩንም ባርክለት 
ባለበት ጠብቀው
ከዕውቀቱም ተጠቃሚዎች አድርገን
አሚን አላሁመ አሚን

የሚገኝበት ቦታ
1. አልኢኽላስ እስቱዲዮ (አሜሪካን ግቢ፣ አልሙሳ የገበያ ማእከል)
2. አልቁድስ መክተባህ
3· በቅርቡ በሌሎችም መክተባዎች ይኖራል ኢንሻአላህ፡፡
በጅምላ መውሰድ ለምትፈልጉ በ 0960 1467 74 እየደወላችሁ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አልሐምዱሊላህ ቢኒዕመቲሂ ተቲሙስሷሊሓት


Post a Comment

0 Comments