Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ፤ ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ” ደቡብ አፍሪካ

Abubeker Siraj's photo.
“ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ፤ ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ”
እንዲሉ ...
ከዚህ በፊት ሱዑዲ ዓረቢያ አዲስ የስደተኞች መተዳደሪያ ህግ ማውጣቷን አስመልክቶ አንዳንድ ሃገሪቱንም ሆነ ኢስላምን ሊወክሉ የማይችሉ የሃገሪቱ ዜጎች ኢትዮጵያውያን ላይ ይህ ነው የማይባል በደል ፈፅመዋል ።
ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ቀድሞውኑ በሸሪዐ ህግ ለምትተዳደረዋ ሱዑዲያ እና ለኢስላም ጥላቻ የነበራቸው አንዳንድ ፀሃፍት ይህን በደል አስታከው ኢስላምን ለማጠልሸት ደፋ ቀና ብለው ነበር ። አልተሳካላቸውም እንጂ!
ጥያቄዬ
ይሀው ዛሬ ቀን ደርሶ እንደምንሰማው አንዳንድ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች አንዳንድ ጋጠ ወጥ ሱዑዲያውያን ከፈፀሙት የማይተናነስ በደል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየፈፀሙት ይገኛሉ ። ታዲያ እስኪ ማነው ባለ ‘ብሩህ ሕሊና’ ፀሃፊ “የደቡብ አፍሪካ ብዙሃኑ ሕዝብ ክርስቲያን ነውና ይህ የሃገራችን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል ከእምነቱ የመነጨ ነው!” የሚል?
ሲጀመር የማይዋጥ ነገር ነው ።
ሱዑዲም ሆነ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከዛም አልፎ አለም ላይ በደል የሚደርስባቸው ስደተኞች ይህ ግፍና በደል የሚደርስባቸው ከበደል አድራሹ ስርአት አልበኝነት እና ጨካኝነት እንጂ ከእምነቱ ጋር ቁርኝት የለውም! በጭራሽ!
አላህ አለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ከስደት ኑሮ በቃችሁ ይበላቸው
ለሃገራቸው፣ ለቤታቸውና ለቤተሰባቸው ያብቃቸው

Post a Comment

0 Comments