Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የእምነት መሰረቶችን ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ማስገንዘብ (ማስታወስ)::

Sadat Kemal Abu Meryem's photo.
የእምነት መሰረቶችን ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ማስገንዘብ (ማስታወስ)::
አላህ ይባርካችሁ አሉ በሚባሉ ሚድያዎች ለከተማም ለገጠሩም፤ አገር ውስጥም ላለው ውጭ ተቀማጭ ሼር ያርድጉት፡፡
ሃይማኖታዊ እውቀት በወንድም በሴትም ላይ ግዴታ ነው፡፡
تلقين أصول العقيدة العامة
የእምነት መሰረቶችን ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ማስገንዘብ (ማስታወስ)
بسم الله الرحمن الرحيم
እጅግ በጣም ሩህሩህ እና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው አላህ ስም እጀምራለሁ፡፡
إذا قيل لك: من ربك؟
ጌታህ ማን ነው? ከተባል
فقل: ربي الله
ጌታዬ አላህ ነው በል፡፡
فإذا قيل لك: ما معنى الرب؟
ረብ የሚለው የአረብኛ ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው? ከተባልክ
فقل: المعبود المالك المتصرف.
የሚመለክ (ተመላኪ)፤ ገዢ (ንጉስ)፤ አስተናባሪ ማለት ነው በል፡፡
فإذا قيل لك: ما أكبر ما ترى من مخلوقاته؟
ትልቁ ከምታያቸው አላህ ከፈጠራቸው ፍጡራን ምንድን ነው? ከተባል
فقل: السموات والأرض.
ሰማያት እና ምድር ናቸው በል፡፡
فإذا قيل لك: بماذا تعرف ربك؟
(ጌታህን) በምንድን ነው የምታውቀው? ከተባልክ
فقل: أعرفه بآياته ومخلوقاته.
በበርካታ ፍጡራኖቹ እና በበርካታ ተአምራቶቹ (በአንቀፆቹ) አቀዋለሁ፡፡
وإذا قيل لك: ما أعظم ما ترى من آياته؟
ከበርካታ ተአምራቶቹ (ምልከቶቹ) በጣም ትልቁ ምንድን ነው? ከተባልክ
فقل: الليل والنهار،
ለሊት እና ቀን ናቸው በል፡፡
والدليل على ذلك قوله تعالى:
የዚህም ማስረጃችን የላቀ ከፍ ያለው የአላህ ቃል ነው
{إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَى عَلَى الْعَرْشِ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ يَطْلُبُهُ حَثِيثاً وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ أَلا لَهُ الْخَلْقُ وَالأَمْرُ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ}
ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ከአርሽ በላይ ሆነ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡
فإذا قيل لك: ما معنى الله؟
አላህ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው? ከተባልክ
فقل: معناه ذو الألوهية والعبودية على خلقه أجمعين.
የአምላክነት ባለቤት እና ከፍጡራኑ ሁሉ የተመላኪነት ባለቤት የሆነው ነው በል፡፡
فإذا قيل لك: لأي شيء الله خلقك؟
አላህ ለምንድን ነው የፈጠረህ? ከተባልክ
فقل: لعبادته.
እሱን ለማምለክ (ለመገዛት) ነው በል
فإذا قيل لك: أي شيء عبادته؟
እሱን ማምለክ ማለት ምን ማለት (ምንድን) ነው? ብትባል
: فقل توحيده وطاعته.
እሱን በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ እና በጥቅሉ የእሱን ትዕዛዝ ማክበር ነው በል፡፡
فإذا قيل لك: ما هؤ الدليل على ذلك؟
በዚህ ላይ ማስረጃው ምንድን ነው? ከተባልክ
فقل: قوله تعالى "وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالأِنْسَ إِلاَّ لِيَعْبُدُونِ"
‹‹አጋንንትንም ይሁን የሰው ዘርን አልፈጠርኩም እኔን በብቸኝነት ሊያመልኩኝ እንጂ›› የሚለው የላቀው ከፍ ያለው የአላህ ቃል ነው በል፡፡
وإذا قيل لك: أي شيء أول ما فرض الله عليك؟
የመጀመሪያ አላህ ባንተ ላይ ግዴታ ያደረገው ነገር ምንድን ነው? ብትባል
فقل: كفر بالطاغوت وإيمان بالله،
በጣዖት መካድ እና በአላህ ማመን ነው በል፡፡
والدليل على ذلك قوله تعالى
ለዚህም ማስረጃው ከፍ ያለው የላቀው አላህ ቃል ነው
:{لا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ قَدْ تَبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ فَمَنْ يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِنْ بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَى لا انْفِصَامَ لَهَا وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ}.
በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
فإذا قيل: ما هؤ العروة الوثقى؟
ጠንካራዋ ዘለበት ማለት ምን ማለት ናት? ብትባል
فقل: لا إله إلا الله.
ላኢላሃኢለላህ (ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚመለክ የለም) (የተውሂድ ቃል) ናት በል፡፡
ومعنى "لا إله" نفي و " إلا الله " إثبات.
‹‹ላኢላሃ›› የሚለው ትርጉም አምልኮ የሚገባው እንደሌለ ፡፡
‹‹ኢለላህ›› የሚለው ቃል ደግሞ እውነተኛ አምልኮ ለአላህ ብቻ እንደሆነ ማረጋገጥ ነው፡፡
فإذا قيل لك: ما هؤ أنت نافي، وما هؤ أنت مثبت؟
አንተ ውድቅ የምታደርገው ምንድን ነው?
የምታረጋግጠውስ ምንድን ነው? ብትባል
فقل: نافي جميع ما يعبد من دون الله، ومثبت العبادة لله وحده لا شريك له.
ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ነገሮችን ባጠቃላይ ውድቅ አደርጋለሁ፡፡ አጋር ለሌለው እና ብቸኛ ለሆነው አላህ አምልኮን አፀድቃለሁ፡፡
فإذا قيل لك: مالدليل على ذلك؟
በዚህ ላይ ማስረጃው ምንድን ነው? ብትባል
فقل: قوله تعالى
ከፍ ያለው የአላህ ቃል ነው በል
:{وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ لأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ}
(ሙሐመድሆይ!) ኢብራሂም ለአባቱ እና ለህዝቦቹ ያለውን አውሳላቸው፤ እኔ እኮ ከምታመልኩት ነገር ሁሉ የጠራሁኝ ነኝ፡፡
هذا دليل النفي،
ይሄ ውድቅ የማድረግ ማስረጃ ነው
ودليل الإثبات {إِلاَّ الَّذِي فَطَرَنِي}.
(አምልኮን ለአላህ ብቻ) የማፅደቅ ማስረጃው
ያ የፈጠረኝ ጌታ ሲቀር (ብቸኛው ፈጣሪ ብቸኛው ተመላኪ ነው)
فإذا قيل لك: ما هؤ الفرق بين توحيد الربوبية وتوحيد الألوهية؟
(አላህን) በጌትነቱ ብቸኛ ማድረግ እና በአምላክነቱ ብቸኛ ማድረግ ልዩነቱ ምንድን ነው? ብትባል
فقل: توحيد الربوبية إفراد الله بأفعاله، مثل الخلق والرزق، والإحياء، والإماتة، وإنزال المطر وإنبات النبات، وتدبير الأمور...
(አላህን) በጌትነቱ ብቸኛ ማድረግ ማለት ጌታችን በሚሰራቸው ስራዎች ብቸኛ ማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ መፍጠር፤ ሲሳይ መስጠትን፤ ህያው ማድረግን፤ መግደልን፤ ዝናብ ማውረድን፤ ቡቃያ ማብቀልን፤ በጥቅሉ ነገራቶችን ማስተናበርን
وتوحيد الإلهية إفراد الله تعالى بأفعال العباد، مثل الدعاء والخوف والرجاء والتوكل والإنابة والرغبة والرهبة والنذر والاستغاثة، وغير ذلك من أنواع العبادة.
አላህን በአምላክነት ብቸኛ ማድረግ ማለት አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! አምልኮህን በጠቅላላ ለአንድ አላህ ብቻ ማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ ፀሎት (ዱዓ)፣ ፍራቻ፣ ክጃሎት፣ መመካት፣ በንስሃ መመለስ፣ ተስፋ ማድረግ፣ ስጋት፤ ስለት፣ የጭንቅ ግዜ ፀሎት (ረድኤት)፣ እና የመሳሰሉትን የአምልኮ ክፍሎች
فإذا قيل لك ما دينك؟
እምነትህ (ሃይማኖትህ) ምንድን ነው? ከተባልክ
فقل: ديني الإسلام، وأصله وقاعدته أمران:
እምነቴ (ሃይማኖቴ) እስልምና ነው በል፡፡ የእስልምና መሰረቱ እና መርሆዎቹ 2 ናቸው፡፡
الأول: الأمر بعبادة الله وحده لا شريك له، والتحريض على ذلك، والموالاة فيه، وتكفير من تركه،
የመጀመርያው ተጋሪ የሌለው እና ብቸኛ የሆነውን አላህ በማምለክ (ጉዳይ ላይ) ማዘዝ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ማነሳሳትና መቀስቀስ ፣ በሱም ላይ መሰረት አድርጎ መዋደድ ነው፡፡ ይህንን እውነታ የተወን ሰው ማስከፈር፡፡
والإنذار عن الشرك في عبادة الله، والتغليظ في ذلك، والمعاداة فيه، وتكفير من فعله.
በአላህ አምልኮ ላይ ከማጋራት ማስጠንቀቅ፣ ጉዳዩ ከባድ መሆኑን አክብዶ መግለፅ፣ በሱም ጠላት አድርጎ መያዝ፣ የፈፀመውን ሰው ማስከፈር ነው፡፡
وهو مبني على خمسة أركان:
እስልምና በአምስት መዓዘናት የተገነባ ነው፡፡
شهادة أن لا إله إلا الله، وأن محمدا رسول الله، وإقام الصلاة، وإيتاء الزكاة، وصوم رمضان، وحج البيت مع الاستطاعة.
(የእስልምና ማዕዘናት የሚከተሉት ናቸው) ከአላህ መስተቀር በሃቅ የሚመለክ እንደሌለ መመስከር እና ሙሃመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሰላትን ማቋቋም፤ ዘካን መክፈል፣ የረመዳንን ወር መፆም፣ ከአቅም ጋር ሃጅን መፈፀም ናቸው፡፡
ودليل الشهادة قوله تعالى:{شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لا إِلَهَ إِلاَّ هُوَ وَالْمَلائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِماً بِالْقِسْطِ لا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ}
የሁለቱ የምስክርነት ቃል ማስረጃ የላቀው የአላህ ቃል ነው
አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
ودليل أن محمدا رسول الله قوله تعالى:{مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ}
ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአላህ መልክተኛ መሆናቸው ማስረጃው
ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡
والدليل على إخلاص العبادة والصلاة والزكاة قوله تعالى:{وَمَا أُمِرُوا إِلاَّ لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ وَذَلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ}
የበጎ ስራ፤ የስግደት፤ የዘካ ማስረጃው የላቀው አላህ ቃ ነው
አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡
ودليل الصوم قوله تعالى:{يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ}
የፆም ማስረጃው የላቀው አላህ ቃል ነው
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡
ودليل الحج قوله تعالى:{وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلاً وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ}
የሀጅ ማስረጃው የላቀው አላህ ቃል ነው
ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡
وأصول الإيمان ستة: أن تؤمن بالله وملائكته وكتبه ورسله وباليوم الآخر وبالقدر خيره وشره.
የእምነት መሰረቶች (ሙሶሶዎች) 6 ናቸው፡፡
በአላህ፤ በመላእክቶቹ፤ በመፀሃፍቱ፤ በመልክተኞቹ፤ በመጨረሻዋ ቀን፤ ጥሩንም መጥፎንም አላህ ነው የወሰነው ብሎ ማመን ነው፡፡
والإحسان أن تعبد الله كأنك تراه، فإن لم تكن تراه فإنه يراك.
በአምልኮ ላይ ማሳመር ማለት፤ አላህን ልክ እንደምታየው አድርገህ መገዛት፤ የምታየው ባትሆን እሱ ያይሃል፡፡
فإذا قيل: من نبيك؟
ነብይህ ማን ነው? ከተባልክ
فقل: محمد بن عبد الله بن عبد المطلب بن هاشم، وهاشم من قريش وقريش من العرب والعرب من ذرية إسماعيل ابن إبراهيم الخليل على نبينا وعليه أفضل الصلاة والسلام.
ሙሐመድ ኢብን አብደላህ ኢብን አብድል ሙጠሊብ ኢብን ሀሺም፣ ሀሺም ከቁረይሾች ነው፣ ቁረይሾች ከአረቦች ናቸው፣ አረቦች የኢስማኢል ዝርያዎች ናቸው፣ ኢስማኢል ደግሞ አላህ ፍፁም አድርጎ የያዘው የኢብራሂም ልጅ ነው፣ በነብያችን እና በኢብራም ላይ በላጭ የሆነ ሰላት እና አላም ይውረድ፡፡
بلده مكة،
የትውልድ አገራቸው መካ ናት፡፡
وهاجر إلى المدينة.
ወደ መዲና ተሰደዱ
وعمره ثلاث وستون سنة:
እድሜያቸው 63 ነው፡፡
منها أربعون قبل النبوة،
40ው ከነብይነት በፊት
وثلاث وعشرون نبيا رسولا.
23ቱ ነብይ እና መልክተኛ ሆነው ጨረሱ
نُبئ باقرأ،
አንብብ በሚለው ቃል ነብይ ሆኑ
وأرسل بالمدثر.
ሙደሲር በሚለው ምዕራፍ መልክተኛ ሆኑ
فإذا قيل: هل مات أو ما مات؟
ሞተዋል ወይንስ አልሞቱም? ተብለህ ከተጠየቅክ
فقل: مات،
ሞተዋል በል
والدليل قوله تعالى:{إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُمْ مَيِّتُونَ ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ عِنْدَ رَبِّكُمْ تَخْتَصِمُونَ}.
ለዚህም ማስረጃው የላቀው አላህ ቃል ነው
(ሙሃመድ ሆይ! ‹ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም›) አንተ ሟች ነህ፤ እነሱም (ካሃዲያን) ሟቾች ናቸው፡፡
ودينه ما مات (ولن يموت) إلى يوم القيامة،
እሳቸው ይዘውት የመጡት (የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ኢስላም) አልሞተም፤ እስከ ትንሳኤ ድረስም ወደፊትም አይሞትም
وهل الناس إذا ماتوا يبعثون؟
ሰዎች በሞቱ ጊዜ ይቀሰቀሳሉን?
فقل: نعم،
አዎን በል፡፡
والدليل قوله تعالى:{مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَى}
ለዚህም ማስረጃው የላቀው አላህ ቃል ነው
ከእርሷ ከአፈር ፈጠርናችሁ፤ ወደ አፈርም እንመልሳችኋለን፣ በሌላም ጊዜ ከሷም እናወጣችኋለን
والذي ينكر البعث كافر،
ከሞት በኋላ መቀስቀስን የሚያስተባብል ሰው ካፊር ነው፡፡
والدليل قوله تعالى:{زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنْ لَنْ يُبْعَثُوا قُلْ بَلَى وَرَبِّي لَتُبْعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلْتُمْ وَذَلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ}
ለዚህም ማስረጃው የላቀው አላህ ቃል ነው
እነዚያ የካዱትን በፍጹም የማይቀሰሱ መኾናቸውን አሰቡ፡፡ «አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ ከዚያም በሠራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡» በላቸው፡፡
وصلى الله على محمد وآله وصحبه وسلم تسليما كثيرا.
የአላህ ሰላት እና ሰላም እጥፍ ድርብ ሆኖ በነብዩ ሙሃመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይውረድ፡፡