Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለእኔና ለአንች

A user's photo.
ለእኔና ለአንች
ማንነታችን የሚለካው፣ጨዋነታችን የሚመዘነው ኢስላም የሰጠንን የክብር ካባ ስንጎናፀፍ ብቻ መሆኑን አውቀን፣አይናአፈራዊ ዉበታችንን ስንጠቀመው ብቻ ነው።
ያለዚያ ግን በሌለን አቅም ከጉልበተኞች ጋር መገጣጠም እና ራሳችንን እንደ እሳት እራት ለእሳት መማገድ ነው ላንዘልቀው በአቅም ማነስ ተዋርደን አዘቅጥ ውስጥ እንወድቃለን።
በአሸበረቀ መርዝ ውስጥ ላንወጣ እንገባለን።
ፈተናዎች ከበውናል አምረው ተውበው በራችንን አንኴኩተዋል።

ባለትዳርዋም ትዳርሽን አክብረሽ ተንከባከቢ
ያላገባሽውም ትእግስት አድርገሽ ለጌታሽ ህግ ተገዥ በመሆን የርሱን ውሳኔ ጠብቂ።እየውልሽ ደስ የሚለው ብስራትሽ ፣ሳታገቢ ወደ አኺራ ብትሄጅ ለምን አላገባሽም ተብለሽ ጀነትን አትከለከይም ።ይህን ስልሽ ትዳርን እያከላከልኩ አይደለም ።ታገሽ እና የጌታሽን ውሳኔ ጠብቂ ማለቴ ነው።
ብንማር ብንመራመር ፣ብንዶከትር ብንመሀንድስ የትም የሰልጣኔ ጥግ ላይ ብንደርስ፣ እንደዚህ ነው ያለው አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ
{الرِّجَالُ قَوَّامُونَ عَلَى النِّسَاءِ بِمَا فَضَّلَ اللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَا
أَنفَقُوا مِنْ أَمْوَالِهِمْ ۚ فَالصَّالِحَاتُ قَانِتَاتٌ حَافِظَاتٌ لِّلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ اللَّهُ ۚ وَاللَّاتِي تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَاهْجُرُوهُنَّ فِي الْمَضَاجِعِ وَاضْرِبُوهُنَّ ۖ فَإِنْ أَطَعْنَكُمْ فَلَا تَبْغُوا عَلَيْهِنَّ سَبِيلًا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيًّا كَبِيرًا} [النساء : 34]
"ወንዶች የሴቶች አሳዳሪዎች(ደጀኖች)ናቸው።ለአንደኛቸው ከሌላቸው የበለጠ(ጥንካሬን) ስለለገሰው፣እንደውም እነርሱ(ወንዶች)(ሴቶችን)ከገንዘቦቻቸው ስለሚለግሱ ።መልካሞች ሴቶች (እነዚያ)ታዛዦችና አላህ የጠበቀውን (ክብራቸውን)ባሎቻቸው ከአጠገባቸው ባይኖሩም እንኳ የሚጠብቁት ናቸው።እነዚያን አመፃቸውን የምትሰጉትን መጀመሪያ ምከሯቸው፣ከዚያም መኝታችሁን ከነርሱ መኝታ ለዩ።በመጨረሻም ምቷቸው።ግና ከታዘዟችሁ እነርሱን የምትጎዱበትን መንገድ አትፈልጉ።አላህ ልዑልና ታላቅ አምላክ ነው።"
ይህ የአምላካችን ፣የፈጣሪያችን መልዕክት ግን የሚመለከተው ሁላችንንም ነው ሴቶችን ፣የተማረች ያልተማረች፣ሀብታም ደሃ፣ንግስት ተራ ሴት ፣ አሮጊት ወጣት ሳይል ሁላችንንም ያቅፈናል።
ለክብራችን የሚበጀን ለሁለት አገር ክብር የኢስላም ስልጣን ብቻ ነው። ከወንዶች ጋር እኩል እንዳልሆንን
ያ የፈጠረን አምላካችን ነው ያረጋገጠልን። ለእኩለነት ቆመናል የሚሉትም ጠንቅቀው ያውቁታል ይህን ያለአቻነት። ለዚህም እኰ ነው ውድድሮች ሳይቀሩ የሴትና የወንድ መለየታቸው።ይህ ልዩት ደግሞ ውበት ፣አንድ ጋር የሌለለ የተፈጥሮ ለዛ ነው።አይናፋርነት የእኛ ድንቅ የተፈጥሮ ፀጋ ነው እናጣጥመው እናንፀባርቀው።
እንመከር ይልቅስ የእናቶቻችንን ፈለግ የኸዲጃን፣የአይሻን፣የሃፍሳን ፋና እንከተል ።
ዱኒያ አጭር ነች ቤታችንን አናበላሽ
አለህ ያግዘን።አሚን