Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቁንጮዎቻችን ሪድዋኑላሂ ዓለይሂም አጅመዒን

A user's photo.
` 💥ቁንጮዎቻችን💥
` ሪድዋኑላሂ ዓለይሂም አጅመዒን
አቡበክር አስ'ስዲቅ እና ዑመር ኢበነል ኸጣብ ረዲየላሁ ዐንሁም ተወዳዳሪ የሌላቸው የሙስሊሞች ቁንጮዎች ናቸው።
በጥቅል ሶሃቦች ባጠቃላይ ከነሱ በኋላ ካለው ሕዝብ በምንም መስፈርት የተሻሉና የበለጡ ጭራሽም የማይወዳደሩ ናቸው።
በሰሂህ ቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበው መሰረት ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሰምቶ አቡሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተረኩልን ☞
رواه البخاري (3673) ومسلم (2541)
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ :
( لَا تَسُبُّوا أَصْحَابِي ، لَا تَسُبُّوا أَصْحَابِي ، فَوَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَوْ أَنَّ أَحَدَكُمْ أَنْفَقَ مِثْلَ أُحُدٍ ذَهَبًا مَا أَدْرَكَ مُدَّ أَحَدِهِمْ وَلَا نَصِيفَهُ )
« ሶሃቦቼን አትሳደቡ ! ሶሃቦቼን አትሳደቡ ! ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ !
አንዳችሁም የዑሁድ ተራራን የሚያህል ወርቅ ብትለግሱ እንኳን፤ የአንዳቸውንም እፍኝ ይቅርና ግማሹንም አይደርስም። » ብለዋል።
ያውም ከሰሃባ ውጭ ካሉት ምርጥ ሙስሊሞች ጋር ነው ብልጫ እንዳላቸው የተገለፀው እንጂ ኒፋቅን አጉልቶ ከሚያሳይ ጋር አይደለም።
ስለሆነም
☞እነሱን የተቸ፣ የተፃረረ፣ የተቃረነ
☞እነዚህን ታላላቅ የኢስላም ዓይኖች በፍቅርና በክብር ያልተቀበለ
~ በምንም ጥሩ ስያሜ ቢሰየም
~ ምንም መልካም ሰራ ቢባል
ሙስሊሞች ዘንድ ቦታ የለውም።
ከነሱ ዒባዳም የሱኒዮች እንቅልፍ ይሻላል።
ለመሆኑ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በተለይ ስለ☞
‪#‎አቡበክርና_ዑመር‬ ረዲየላሁ ዐንሁም ምን ብለው ይሆን
أخرج الطبراني والخطيب في " تاريخ بغداد " (٨ / ٤٥٩ - ٤٦٠)
من طريق عبدالله بن محمد بن عقيل عن جابر بن عبد الله قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
" أبو بكر وعمر من هذا الدين كمنزلة السمع والبصر من الرأس ".
السلسلة الصحيحة للألباني رحمه الله
ኢማም አጥ'ጠበራኒና አልኸጢብ " ታሪኹል በጘዳድ " ላይ እንዳሰፈሩትና ኢማም አል-አልባኒ ረሂመሁሙላህ ሰሂህ ባሉት ዘገባ
በአብደላህ ቢን ሙሀመድ ቢን ዑቀይል በኩል በደረሰን መሰረት ጃቢር ቢን አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰማውን እንዲህ ሲል ተረከልን።
« በዚህ በሃይማኖታችን ውስጥ የአቡበክርና የዑመር ቦታ (ደረጃ) በአናታችን ላይ መስሚያችንና ማያችን ያለውን ቦታ ያህል ነው።» ብለዋል።
‪#‎አስቡት_ከሰሃቦች_መሃል_የአቡበክርና_የዑመር_የዑስማንና_የዓሊይ_ሪድዋኑላሂ_አለይሂም_አጅመዒን‬ ደረጃ ለየት ያለ ነው።
‪#‎ሺዓዎችና_ጓዶቻቸው_እንግዲህ_እነዚህን_ነው_የሚዋጉት_የሚተቹት_የሚጠሉትና_የሚረግሙት_‬
አቅል ያለው ሙስሊም እነዚህን ራፊዳዎች አይደግፍም። አያቅፍምም።
_________
✏Abufewzan
ጁማዱ'ሳኒ 22/1436
ኤፕሪል 12/15

Post a Comment

0 Comments