Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህን ተመክተሽ ከተረጋጋሽ... ትደርሻለሽ!!

A user's photo.
አላህን ተመክተሽ ከተረጋጋሽ... ትደርሻለሽ!!
ውዷ ሙእሚናህ...
በአላህ ከመታገዝ ጋር በራስ መተማመን ያላት እንስት እና ኩራትና ሰዎችን መናቅን ባህሪዋ ያደረገችው መካከል ከባድ ልዩነት አለ። እንደዚሁ በምሁር ሴት እና በመሀይም ሴት መካከል ከባድ ልዩነት አለ።
አንድ ቁምነገር ሹክ ልበልሽ...
ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ላይ ደርሳ የተመረቀች ሁሉ የተማረች ናት ማለት አይደለም። የእውቀት ጫፍ ማለት የመጠቀ መልካም ስነምግባር፣ የላቀ ስነስርአት፣ ንፁህነትና ጨዋነት ነው።
ሙስሊሟ ሴት፤ ወንጀሎችን የምትዳፈር ፣ የተዋበችበት ሀያእ የተገፈፈ፣ ሀላፊነትና ተጠያቂነት የማይሰማት ግድየለሽ ሆና "የተማረች" ከምትሆን፤ በመልካም ባህሪ የታነፀች፣ ጨዋነቷ ፊቷ ላይ የሚነበብ፣ ስነስርአትን የተላበሰች ጥሩ ሙስሊማህ ሆና ማንበብና መፃፍ የማትችል "መሀይም" ብትሆን
የተሻለ ነው!!
እህቴ... ዋጂባቶችን በቅድሚያ ተማሪ፤ ለዱንያዊ እድገት ከዲንሽ አትንሸራተቺ...በአላህ ትእዛዛት ላይ ከፀናሽ ኢን ሻ አላህ በሁሉም ነገር የተሻልሽ ትሆኛለሽ!!
ሙስሊም ከአቡሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፤
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم:"...احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ وَاسْتَعِنْ بِاللهِ وَلَا تَعْجَزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَرٌّ فَلَا تَقُلْ لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا وَكَذَا قُلْ قَدَّرَ اللهُ وَمَا شَاءَ اللهُ فَعَلَ، فَإِنَّ لَوْ تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَانِ " رَوَاهُ مُسْلِمٌ
«...በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ ደካማና ስልቹ አትሁን፤ አንድ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ‘ይህን ነገር እንዲህ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ፈፀመ’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል
ተንቢሀት
www.facebook.com/tenbihat