Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወንድሜ አብሽር ይሄ አያሳፍርም ከፊል ወንዶች ቤታቸው ውስጥ

ወንድሜ አብሽር ይሄ አያሳፍርም
**************************
ከፊል ወንዶች ቤታቸው ውስጥ
1) ቤትን መጥረግ፣
2) ልጅን ማጠብ፣
3) አትክልት ተራ ሄዶ መግዛት፣
4) ውሃ መቅዳት፣
5) የበሉበትን ማንሳት፣
6)ምግብ ማብሰል፣
ባጠቃላይ ሚስትን ወይንም እናትን ስራ መርዳት እንደ ነውር እና የሚያሳፍር ብሎም የወንዶች ስራ እንዳልሆነ ያዩታል። ሱብሃነላህ የወንዶች ሁሉ ወንድ፣ የነብያት መደምደሚያ፣ የመልክተኞች ኢማም ነብዩ ሙሃመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ሚስቶቻቸውን ቤት ውስጥ ስራ ያግዙ ነበር።
ታድያ ወንድሜ የማህበረሰቡን ትችት እና ማሽሟጠጥ ተወው እና የአላህን ውድ የነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፋና ተከተል እናትህን ተንከባክባ እና አዝና ያሳደገችህን፣ ሚስትህን ገመና ሸፋኝህን፣ የልጆችህን እናት በስራ እርዳቸው።
አላህ ለቤተሰባቸው ጥሩ ከሆኑት ያድርገን።