Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሚከተለው ብዥታ መልስ ሲሰጠው "ሁሌ ቅድሚያ ለተውሂድ ቅድሚያ ለሡና ቆይ ሌላው ዳኢ ቢድአ እና ሽርክ ነው እንዴ የሚያሥተምረው"???

የሚከተለው ብዥታ መልስ ሲሰጠው
"ሁሌ ቅድሚያ ለተውሂድ ቅድሚያ ለሡና ቆይ ሌላው ዳኢ ቢድአ እና ሽርክ ነው እንዴ የሚያሥተምረው"???
ጥቂት መልሶች
*************
1) አላህ እንዲቀደም ያዘዘው ዋና መልክት ተውሂድ ስለሆነ እኛም ዛሬም፣ ነገም በአላህ ፈቃድ ቅድሚያ ለተውሂድ እንላለን፣ ቅድሚያም ለተውሂድ እንሰጣለን።
2) መልክተኞችን ሁሉ አላህ የላከው፣ እነሱም ያስቀደሙት፣ የለፉለት፣ የሞቱለት መንገድ ይሀው ተውሂድ ስለሆነ እኛም በአላህ ፍቃድ የነሱን ፈለግ በመከተል ቅድሚያ ለተውሂድ እና ሱና እንላለን፣ እንሰጣለንም
3) ይህ ተውሂድ እና ሱና ካለተስተካከለ ሌሎች አምልኮዎች ተቀባይነት ስለሌላቸው ስራችን ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ እና ሱና ሰጥተን ስራችንን ለማስተካከል እንሞክራለን
4) አዎን ብዙ ዱአቶች (ዳእዋ አድራጊዎች) ነብያት የጀመሩበትን ተውሂድ አያስቀድሙትም፣ ትኩረት አይሰጡትም፣ ካወሩም ከስንት ዘመናት አንዴ፣ ወይንም ውስጡ ሳይገቡ ዳርዳሩን የሚሉ፣ ሌሎች አርስቶችን የሚያስቀድሙ ስለሆኑ በአላህ ፈቃድ እኛ ቅድሚያ ለተውሂድ ሰጥተን እራሳችንንም ማህበረሰቡንም እንኮተኩታለን
5) ነብያት ሁሉ ያልሄዱበትን ሃቅን በባጢል የሚደበልቁ የስሜት ተከታዬች "ቅድሚያ ለአንድነት እና ለወንድማማችነት" የሚሉ ስላሉ፣ ይህን ቅጥፈታቸውን አንድነትም ይሁን ወንድማማችነት ተውሂድ እና ሱና በሰለፎች አረዳድ የገነባው ብቻ ስለሆነ የነሱን ማታለያ ውድቅ ለማድረግ አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ እና ሱና እንላለን
6) "ሌላው ዳኢ ቢድአ እና ሽርክ ነው ወይ የሚያስተምረው?" ላሉት አዎን ከዳኢ ወደ ሽርክ፣ ኩፍር፣ ቢድአ እና ፍልስፍና የሚጣራ አለ።
የክብር እንግዳ እየተደረጉ ቻናል ላይ የሚቀርቡት የሽርክ መንዙማ ባዬች ወደ ኩፍር እና ሽርክ አይደለምን የተጣሩትን??? ለምሳሌ "ሀቢቢ ሀቢቢ መዲና ና ይበሉኝ" የሚለው ሽርክ መንዙማ ባለቤት?

በድራማ፣ በፊልም እና በመሳሰለው እያሉ ሙስሊሞችን የሚያጠሙት ቻናል ላይ የሚታዩት ወደ ቢድአ አይደለምን የሚጣሩት?
7) ሽርክ ሲሰራ እያዩ "በአካባቢ ሃቅ አንገባም" የሚሉት ተብሊጎች ወዴት ነው የሚጣሩት??
እና የመሳሰለው።
ሃቅን ለፈለገ ጥቆማ ይበቃዋል። በአላህ ፈቃድ እስክንሞት ወደ ተውሂድ እንጣራለን። አላህ ፅናቱን ይስጠን።
እናንተ ይህን አባባል የምትሉና ሰውን ግራ ለማጋባት የምትሞክሩ አላህን ፍሩ። አሁንም አላህ ተውበት ይቀበላል ነብያት ሁሉ ወደተጣሩለት ተውሂድ ሁላችንም በጋራ እንሳተፍበት፣ ነጃ መውጣት ከፈለግን።
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን።